first one

Posted: December 5, 2012 in Uncategorized

this is my first blog for trail.

Dear Reader my efforts to join wordpress hasn’t been that much easy until any thing new comes up you can find new posts at my old blog:

http://antiglobalconspiracy.blogspot.com/

or you can find us on Face Book:

https://www.facebook.com/AntiglobalConspiracy

I deeply apologize for any inconvenience which might have occurred.

Read the rest of this entry »

Advertisements


ግደይ ገብረኪዳን
ምንም እንኳ በአሁኑ ግዜ ስለ ቻይና ብዙ መልካም መገሮችን ብንሰማም፣ በአንድ ፓርቲ ጋርዮሻዊ አገዛዝ የምትተዳደር እንደመሆኗ ለማመን የሚከብዱ ክንውኖችም ይካሄዱባታል፡፡ በማኦ ዘመን የባህል አብዮት በታወጀበት ግዜ ከነበረው ጭቆና አሁን ቢሻልም አሁንም ቢሆን ቻይና ከባድ ሃገር ነች፡፡ የፓርቲው አባላት የግዴታ ኢ-አማንያን መሆን ይጠበቅባቸዋል፣ ተቃዋሚሆች ያለህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድባቸዋል፣ ቲቤት ፈተና ውስጥ ነች፣ ፓርቲው አስገዳጅ ፖሊሲዎችን ያወጣል ለምሳሌ አንድ ልጅ ብቻ የመውለድ ፖሊሲ የቻይና ወላጆችን እያሰቃየ ነው – በቻይና ወንድ መውለድ ስለሚፈለግ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መልኩ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች እንዲበልጥ አድርጓል፣ ሴት ስትፀነስ ውርጃ ይካሄዳል – ተወልደውም የሚገደሉ አሉ፡፡ መንግስት በቀጥታ ሚድያውን ሁሉ ይቆጣጠራል፣ መንግስትን የሚወቅሱ ፅሁፎች የማይታሰብ ነው፣ በኢንተርኔት የሚወጡትም ከሰው እንዳይደርሱ ይታገዳሉ፡፡

Read the rest of this entry »


በግደይ ገብኪዳን
ወደ 2000 ዓ.ም ገደማ ጋርዮሻዊቷ ቻይና በአሜሪካ ቴክኖሎጂ እና  ክህሎት የተገነባች “ልእለ ሃያል” ሃገር ትሆናለች፡ ፕሮፌሰር አንቶኒ ሱቶን፡ የአሜሪካ ሚስጥራዊ ተቋም፣ 1984
ወደ 50 ከሚጠጉት ግዙፍ የቻይና መንግስት ካምፓኒ መሪዎች ዴስክ ላይ ከኮምፒተሮቹ፣ ከቤተሰብ ፎቶዎቹ እና ሌላ ቅንጡ ዘመናዊ የዋና ሃላፊ ቢሮ ከሚያስፈልጋቸው ውድ እቃዎች ማሃከል አንዲት ቀይ ስልክ ትኖራለች፡፡ ልክ ስትጠራ ሊያነሷት ከተቀመጡበት የሚወነጨፉት የበላይ ሃላፊዎች “ቀይዋ ማሽን” ብለው ይጠሯታል፡፡ ስልክ ብቻ ማለት በትክክል አይገልፃትም፡፡ ይህች ስትጠራ ያላነሳ አለቃ ወዮለት!
Read the rest of this entry »


በግደይ ገብረኪዳን
 ከአለማችን ትልቋ “ዲሞክራሲ”፡ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በየአራት አመቱ ለምታካሂደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንደተለመደው ለማስተናገድ ሽርጉዱን ተያይዛዋለች፡፡ ይህች በአለም ዙርያ የዲሞክራሲ ፖሊስ መሆን የሚቃጣት ሃገር ይህን አጋጣሚ ተጠቅመን ዲሞክራሲዋን እንገመግምላታለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡

Read the rest of this entry »

በግደይ ገብኪዳን
ብዙ ሰዎች በጋዝ ነዳጅነት ተጠቅመው መኪናቸውን ሲያሽከረክሩ በሃይድሮጅን እያሽከረከሩት እንዳለ ልብ አይሉትም፡፡ እኛ [በውሃ የምትሰራ መኪና የሰራነው] ደሞ እያደረግን ያለነው ሃይድሮጅኑን ከውሃ ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ የብሄራዊ ልኬት (ስታንዳርድ) ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ ውሃ ስትጠቀም የሚለቀቀው ሃይል ጋዝ ተጠቅሞ ከሚገኘው በማጠጋጋት ሁለት ከግማሽ በእጥፍ ይበልጣል፡፡ እናም ውሃ እጅግ ሃያል ነዳጅ ነው፡፡ ስታን መየር (እ.ኤ.አ. 1992)
እንዲህ የገዘፈ ትራጀዲ የሰው ልጅን አልገጠመውም፡፡ ይህ በሰው ልጅ ላይ የደረሰው ከፍተኛው በደል ነው፡፡ ይህ ውድቀት በአራተኛው ክፍለ ዘመን ላይ በአለክሳንደርያ ቤተ መፃህፍት በእሳት ቃጠሎ መውደሙ በሰዎች ስልጣኔን ወደኋላ በመጎተት ከደረሰው ኪሳራ የከፋ ነው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ግኝት ከቤንጃሚን ፍራንክሊን የኤሌክትሪሲቲ ግኝት የበለጠ፣ ከቶማስ ኤዲሰን አለማችንን ለመጨረሻ ግዜ የቀየረው የፐርል ጎዳና ኤሌትክ ማከፋፈያ ስርአት ምስረታ እጅግ የበለጠ ነው፡፡ ሁለተኛውን ኢንዱስትሪያዊ አብዮት በር የከፈተው የኒኮላ ቴስላ ኤሌትሪክ ሃይል በገመድ አርቆ እንዲጓዝ ያስቻለው የአልተርኔቲንግ ከረንት ግኝቱ በላይ የሆነ ፈጠራ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሌሎች ይፋ ያልሆኑ የኒኮላ ቴስላ ፈጠራዎች ይበልጣል ማለቴ አይደለም፡፡ Read the rest of this entry »

በግደይ ገብረኪዳን
በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ስለ ኢሉሚናቲ ማውራት ከአመት በፊት ከነበረው ሁኔታ እንኳ በእጅጉ ተቀይሯል፡፡ አሁን ቢያንስ ስሙን እንኳ የሚያውቀው ሰው ቁጥር እጅግ በዝቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ስለ ኢሉሚናቲ ምንነት የጠራ ወይም በነባራዊው የዓለም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መድረክ ዙርያ ያለውን ወይም የሌለውን ሚና በቅጡ መረዳት ላይ አልተደረሰም፡፡ በዚህ ፅሁፍ በተለይ በሃገራችን ላይ አትኩሮት በማድረግ ትክክለኛ የምርምር መርህ ተጠቅመን ስውሮቹን እጆች ለመዳበስ እንሞክራለን፡፡ Read the rest of this entry »

በግደይ ገብረኪዳን
 “በአንድ ግዜ የአሜሪካ ወዳጅና የሽብር ጠላት መሆን አይቻልም፡፡” ተክሉ አስኳሉ

ከስር ያለው የአንድ ደቂቃ ቪድዮ በመስከረም 11 ጥቃት አውሮፕላኖቹ አፈረሱት የተባለው ህንፃ ኮንክሪቶቹ ተገንድሰው መሬት እንደመውደቅ አየር ላይ እያሉ ወደ አመድ ይቀየራሉ፡፡ ህንፃ ሲፈራርስ ቢያንስ 12 መቶኛ አካሉ በፍርስራሽ መልክ ተከምሮ መገኘት ይኖርበታል፡ የዓለም ንግድ ማእከል ማማዎች እና ህንፃ 7 ሲፈርሱ ይህ ፍርስራሻቸው አልታየም፡፡ ምክንያቱም ገና መሬት ሳይነኩ አየር ላይ ወደ አመድ ተቀይረው በመብነናቸው ነው፤ ቪድዮውን ይመልከቱ፣ እባካችሁን የተደረመሱት ኮንክሪቶች መሬት ላይ እንደመውደቅ ወደአመድ ሲቀየሩ ይመልከቱ፡፡ ህንፃው አልፈረሰም ወደ አመድ ነው የተቀየረው፡