Archive for August, 2012

በግደይ ገብረኪዳን
 “በአንድ ግዜ የአሜሪካ ወዳጅና የሽብር ጠላት መሆን አይቻልም፡፡” ተክሉ አስኳሉ

ከስር ያለው የአንድ ደቂቃ ቪድዮ በመስከረም 11 ጥቃት አውሮፕላኖቹ አፈረሱት የተባለው ህንፃ ኮንክሪቶቹ ተገንድሰው መሬት እንደመውደቅ አየር ላይ እያሉ ወደ አመድ ይቀየራሉ፡፡ ህንፃ ሲፈራርስ ቢያንስ 12 መቶኛ አካሉ በፍርስራሽ መልክ ተከምሮ መገኘት ይኖርበታል፡ የዓለም ንግድ ማእከል ማማዎች እና ህንፃ 7 ሲፈርሱ ይህ ፍርስራሻቸው አልታየም፡፡ ምክንያቱም ገና መሬት ሳይነኩ አየር ላይ ወደ አመድ ተቀይረው በመብነናቸው ነው፤ ቪድዮውን ይመልከቱ፣ እባካችሁን የተደረመሱት ኮንክሪቶች መሬት ላይ እንደመውደቅ ወደአመድ ሲቀየሩ ይመልከቱ፡፡ ህንፃው አልፈረሰም ወደ አመድ ነው የተቀየረው፡
Advertisements
በግደይ ገብረኪዳን
(ካልታተመ መጽሐፍ የተቀነጨበ)
በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ የኦዞን ሽፋን የመሳሳት ፍጥነቱ በፊት ሳይንቲስቶችን ሲያስጨንቅ ከነበረው 5 መቶኛ ወደ 97 መቶኛ ከፍ አለ፡፡ የዚህን ምክንያት ማንም ሊያብራራው አልቻለም፡፡
ኒኮላ ቴስላ ቴክኖሎጂ
ቶማስ ኤዲሰን የተባለው መብራት ሰራ እየተባልን በየቀኑ እሚለፈፍብን ሰው አጋር የነበረና ስሙ የሚገባውን ያህል የማይነሳ ኒኮላ ቴስላ (Nikola Tesla)እሚባል ሳይንቲስት ነበር፡፡ ይህ የፈጠራ ሃብታም የሆነ ተመራማሪ ነበር፡፡ ይህ ሰው በሂወት ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ የፈጠራ መብት ያወጣበት ስራ ነበረው፡፡ ቴስላ ያገኘው ምንድን ነው በምድር ውስጥ የማያባሩ/ቋሚ ሞገዶች ማስነሳት እንደሚቻል ነው፡፡ ይህ በአለቶቹ ያለው የማስተላለፍ እንቅስቃሴ ለሞገዶቹ ተጨማሪ እንቅስቃሴን ያስገኝላቸዋል በዚህም አንድ ሰው ካስጀመረው ሞገድ በላይ ጉልበት በሞገዶቹ ውስጥ ያገኛል፡፡ ይህን ጭብጡን የማጉያ ማስተላለፍያ –magnifying transmitter-አለው፡፡  በ1976 ሶቭየቶች ወደ አዮኖስፌር ሰባት የቴስላ የማጉያ ማስተላለፍያ አመጠቁ፣ እነዚህ 10ኸርዝ መጠን ያለው ጉልበት ወደ አዮኖስፌር በመልቀቅ ከቺሊ እስከ አላስካ ድረስ ቋሚ ሞገዶች እንዲፈጠሩ አድርገዋል፡፡ በዚሁኑ ግዜ ሶስት የሶቭየት ሳተላይቶች የላይኛውን ህዋ/ከባቢ አየር በዚህ ሞገድ መነካቱን ሲያስተባብሩ ነበር፡፡ እኝህ ሞገዶች በመላው አለም መለየት/መታየት ችለው ነበር፤ የራሽያ “ግንደ ቆርቁር” – “Russian Woodpecker”እሚል ስያሜም ወጥቶላቸው ነበር – በራድዮ ሞገድ ተቀባዮች ላይ በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት፡፡ (more…)

በግደይ ገብረኪዳን
“ክፉ ነገር ለማድረግ መጀመርያ የሰው ልጅ እያደረገ ያለው ነገር ጥሩ ነው ብሎ ማመን ይኖርበታል፡፡… ርእዮተ አለም ክፋት ሁሌም የሚፈልገውን ማስተባበያ የሚያቀርብና ለክፋት ሰሪው የሚያስፈልገውን ያለመወላወልንና ቆራጥነትን ይሰጠዋል፡፡ ይህ ማህበራዊ ንድፈ ሃሳብ [ርእዮተ አለም] ነው ድርጊቶቹ በእርሱና በሌሎች አይን ከክፉ ይልቅ መልካም ሁነው እንዲታዩ የሚያደርገው፣ ስለዚህም ከወገዛ እና እርግማኖች ይልቅ ምስጋና እና ክብር ይቀበላል፡፡” ራሽያዊው የማህበረሰባውያኑ ቦልሸቪኮች ሰለባ የሆነው አሌክሳንደር ሶልሰንትሲን ጉላግ ደሴቶች በሚለው መፅሀፉ እንዳሰፈረው Alexander Solzhenitsyn, Gulag Archipelago
ይህ ፅሁፍ ካልታተመ መፅሐፍ ላይ ካበረከትኩት የተወሰደ ሲሆን ቀድመውት ባሉ ምእራፎች የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት የአሜሪካ መንግስት ሆን ብሎ የፈፀመው ነው የሚሉ ማስረጃዎችን ተከትሎ የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም ለምን ይህን ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለውን ትንታኔ ለማቅረብ የተፃፈ ነው፡፡ አሁን አለምን በማሸበር ለመግዛት እየጣሩ ያሉት ምን አይነት ርእዮተ አለም እንደሚከተሉና ያመጣጥ ታሪኩን እናያለን፡፡ በየሰበቡ ብሔራዊ የሀገራት መሪዎችን በስውር እና በግልፅ እየገደሉ የአለምን ህዝብ የሚያሰቃዩበትን ሚስጥር ምላሽ ይሰጠናል፡፡ ይህ የነሱ እምነት ነው፣ ይህም ስህተት መሆኑን እንድናየው የተፃፈ ነው፡፡ ቁንጮዎቹ ለዓላማቸው እንጂ ለየትኛውም ህዝብ፣ መንግስት፣ ሃገር፣ አህጉር ወይም ሃይማኖት አይወግኑም፡፡
በግደይ ገብረኪዳን
የ2012 ኦሎምፒክ መክፈቻና መዝጊያ ስነ ስረአት በአምስቱም ክፍለ ዓለማት አንድ ቢሊዮን ገደማ ሰዎች ለመታየት በቅቷል፡፡ ሁሌም ከፍተኛ ቦታ እንደሚሰጣቸው የሚድያ ክስተቶች ሁሉ የዓለማችን ቁንጮዎች መልእክቶች፣ ምልክቶች እና አጀንዳዎቻቸው የትእይንቱ አካል ነበሩ፡፡ እኚህን በለንደን ኦሎምፒክ እንዳስሳለን፡፡
የኦሎምፒክ ክብረ በዓላት በምድራችን ሰፊ ተመልካች ከሚያገኙት ትእይንቶች አንዱ ነው፡፡ ላስተናጋጅ ሃገሪቱ ታላቅነቷን የምታሳይበት አጋጣሚዋ ነው፡፡ (ወጪውን በግብር መልክ የሚሸፍነው ድሃው ህብረተሰብ ይሸከመዋል፡፡) የለንደን ኦሎምፒክም ከዚሁ የተለየ አልነበረም፡ የእንግሊዝ ታሪክ፣ ባህል፣ እና ስኬቶች በበዓሉ ቀርበው በሚገባ ተሞግሰዋል፡፡ አንዳንድ ክስተቶች እፁብ ነበሩ ሌሎች የሚያስቁም ነበሩ፤ የሚያስፈሩ እና የሚረብሹም ክስተቶች ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ ከፍተኛ ተምሳሌትነት ያላቸውና የቁንጮዎቹን አጀንዳ የሚያንፀባርቁ ነበሩ፡፡ ለንደን የዓለማችን ቁንጮ የስልጣን ማማዎች መገኛ እንደመሆኗ በበዓላቱ የቁንጮዎቹ ምልክቶችና ፍልስፍና ባይንፀባረቅ ኑሮ ይበልጡኑ አስገራሚ ይሆን ነበር፡፡
ሁሉም ነገር ተምሳሌታዊ ነበር ማለት አይደለም፣ ሁሉም ምልእክትም አይን ያወጣ ግልፅነት አልነበረውም፣ በዓሉ በፈጀበት ሰዓቶች ግን ለመላው ዓለም ህዝብ ሰፊ መልእክት ተላልፏል፡፡ እስኪ እንመልከታቸው፡፡ (more…)