Archive for June, 2012

በግደይ ገብኪዳን
“አንዳንድ ሰዎች እኛ ለዩናይትድ ስቴትስ ከሚበጁ ተግባራት ተቃራኒ የምንፈፅም የሚስጥር ቡድን አባሎች ናቸው ብለው ያምናሉ፤ እኔና ቤተሰቤን “ዓለም-አቀፋውያን” እና ከሌሎች ጋር በዓለም ዙርያ የበለጠ የተዋሃደ ሉላዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስርአት -እንደውም ዓንድ አለም ለመገንባት የምናሴር አድርገው ይወነጅሉናል፡፡ ክሱ ይህ ከሆነ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ በዚህም ደሞ እኮራለው፡፡” (ዴቪድ ሮክፌለር፡ “Memoirs of David Rockefeller” ገፅ 405)
የላይኛው ጥቅስ ከበርቴው ስለ ዓለም አቀፋዊ ሴራው ሂወት ታሪኩን በፃፈበት መፅሃፉ ያሰፈረው ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ደረጃዎች ስንል የዓለም መንግስት ለመመስረት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ወይም ፖሊሲዎች ደረጃ በደረጃ በቅደም ተከተል እናያቸዋለን ማለት ነው፡፡ (more…)
Advertisements

በግደይ ገብኪዳን

“አለም የምትገዛው ከትእየቱ በስተጀርባ ያለውን የማያውቁ ሰዎች እንደሚያስቡት ሳይሆን በጣም በተለዩ ግለሰቦች ነው፡፡”
ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ
ከላይ እንደተፃፈው ቤንጃሚን ዲዝራኤሊ የዩናይትድ ኪንግዶም ሁለት ግዜ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረና ታዋቂ ፀሃፊም የሆነው ሰው እንደሚነግረን ዓለም የምትገዛው ተራው ሰው እንደሚያስበው የስልጣን ወንበር በተቆናጠጡት አይደለም፡፡ ዓለም የምትገዛው እነሱን በሚቆጣጠሩትና ያገዛዝ ፍልስፍና ወይም ርእዮተ አለሙን በሚቀርፁ ከትእይንቱ በስተጀርባ ባሉ ሰዎች ነው፡፡
ታሪክን በሁለት መንገድ መገንዘብ እንችላለን፡
አንድ ታሪክ የአጋጣሚ ክስተቶች ውጤት ነው የሚለው፣ ወይም በኦፊሻል ተቀባይነት ያለው የታሪካዊ ክስተቶች አረዳድ ወይም፣
ሁለት ታሪክ የተቀነባበረና የታሰበበት ክንውኖች ውጤት ነው የሚለው የሴራዊ ታሪክ ትንተና መመልከት ይቻላል፡፡
የታሪካዊ ክስተት እውነታ የሚታወቀው፡
·         አሸናፊዎች በሚፅፉት ታሪክ፣
·         ተቀባይነት ወይም የክብር ቦታ ያላቸው እንደዲዝራኤሊ ያሉ ሰዎች በሚናገሩት፣
·         ወይም የሚስጥር ማህበራት አባሎች ስለታሪካቸው በሚፅፉት ለምሳሌ እንደነ ማንሊ ፒ. ሃል፣ እንደነ አልበርት ማኬ የመሳሰሉት በሚፅፉት ብቻ አይደለም፡፡
ተቀባይነት የሌላቸውና የሚናገሩት ለህዝብ እንዳይደርስ የሚደረግ፡
·         አጋላጭ የታሪክ ተመራማሪዎች የሚፅፉትም አለ፡፡
በነዚህ ሁለት አይነት ፀሃፊዎች ማለትም በሚስጥር ማህበር አባል ሁነው ታሪኩን በሚፅፉትና በአጋላጮቹ መሃከል ያለው ልዩነት ስለሚስጥር ማህበሩ ድብቅ አምልኮ ምንነት ላይ ነው፡፡ እዚህም ላይ ቢሆን የሚገርመው ስለምንነቱ ልዩነት የላቸውም፡፡ ሁለቱም የሴጣን አምልኮ መሆኑን ይፅፋሉ፡፡ አባሎቹ ሲፅፉት ጥሩ አድርገው ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ሲፅፉት ደሞ ክፉና አደገኛ ቀኖናውን በማጋለጥ ነው፡፡ (more…)

Giday Gebrekidan

The following is list of the authors followed by their books which are my and most people’s favorites.
መልካም እድል!!! (more…)
በግደይ ገብረኪዳን

ፍዮዶር ሚካየሎቪች ዶስትየቭስኪ (Fyodor Mikhailovich Dostoyevsky) (11 ህዳር 1821  – 9 ጥቅምት 1881)
ውልደት፡ ሩስያ፣ የተለያዩ ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችና መጣጥፎች ፀሃፊ፡፡ 
የዶስትየቭስኪ ስነፅሁፋዊ ስራዎች በ19 ኛው ክ/ዘመን የነበረው የታወከው የራሽያ ህብረተሰብ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ እና መንፈሳዊ ሂወት በመተራስ ከውስጡ የሚገኘውን የሰው ልጅ ስነ ልቦናን የሚመረምሩ ናቸው፡፡ ፅሁፉን የጀመረው በ1850ዎቹ አጋማሽ ቢሆንም በስፋት የሚታወቁለት ምርጥ ስራዎቹ ግን ወደኋላ መጡት ናቸው፡፡ ወንጀልና ቅጣትተብሎ የተተረጎመለት (Crime and Punishment)፣ ደደቡ (The Idiot)እና እነ ካራማዞቭ (The Brothers Karamazov) ይገኙበታል፡፡ በአጠቃላይ ዶስትየቭስኪ 11 ረዣዥም ድርሰቶች፣ 3 መካከለኛ ድርሰቶች እና 3 ኢ–ልበ ወለዳዊ ስራዎች አሉት፡፡ በስነ ፅሁፍ ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ ስነ ልቦናን አብጠርጥሮ በመተንተን የሚስተካከለው አይገኝም፡፡  (more…)
በግደይ ገብረኪዳን
ይህን ፅሁፍ ከተክሉ አስኳሉ ጋር ከሰራሁት ያልታተመ መፅሐፍ የወሰድኩት ሲሆን እጅግ ልብ ሊባል የሚገባና ማንኛውም አዲስ የዓለም ስርአት ሴራዎችን ማወቅና መመከት የሚሻ ችላ ሊለው የማይችል ነጥብ የያዘ እንደመሆኑ ላካትተው መርጫለው፡፡

5
እውነተኛው አዲስ የአለም ስርአት
እስካሁን ያነበብነው ያለዚህ ምእራፍ መረጃ የባዶ ጣሳ ጩኸት ነው እሚሆነው፡፡ የፋይናንስ ባላባቶች በአለም ህዝብ ላይ ሙሉ የበላይነታቸውን ካገኙ በኋላ በሁሉም የሂወት ዘርፍ ህዝቡን ጥገኛ በማድረግ እንደተንቀሳቃሽ ሬሳ ወይም ዞምቢ የፈለጉትን እሚያስደርጉበት ግዜ እየቀረበ ነው፡፡ በዚህ ክፍል እስካሁን ያልዳሰስነውንና ግባቸው የሆነውን አዲስ የአለም ስርአት ሲያሰፍኑ የአለም ህዝብ ላይ ሊጭኑ ያሰቡትን አምልኮ ምንነት በጥቂቱ እናያለን፡፡

  ግደይ ገብረኪዳን
“በመጀመርያዎቹ መዓርጎች ሜሶን የሚሆነው ሰው የእግዚብሄር ስም እንደጠፋ ይነገረዋል፡፡ በምትኩም ማሃቦን(MAHABONE) የሚለውን እንዲጠቀም ይነገረዋል፡፡ በኋላ ግን ከአንድ መዓርግ ወደ ሌላ መዓርግ በሚያደርገው ሽግግር ባለው ስነስርአት ስራ መሰረት የሚነግሩትን ቁሻሻ ሁሉ ካስዋጡት በኋላ፣ የተጣፋበትና በፕሮፖጋንዳ የተጨፈጨፈው ጓድ ማምለክ ያለበት ስሙ ጃህቡህሉን (Jahbuhlun) ነው ይሉታል፣ እናም ከዚህ በኋላ እራሱን እንደ እኔ ታላቁ  ሰው –the great I AM– ብሎ ራሱን ያውጃል፡፡  (more…)

በግደይ ገብረኪዳን

ይህ የሚታየው የአሜሪካን ገንዘብ አንድ ዶላር ሲሆን፣ ገንዘቡ ላይ ከቀኝ በኩል የሚታየው ከ1935 ዓ.ም ጀምሮ የተጨመረው ከአሜሪካ ሃገር ማህተም በስተጀርባ የነበረ ነው፡፡ ማህተም የጀርባ ቅርፅ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ የቀረፁት ያውቁታል፡፡ ይህ አርማ የአዲስ የአለም ስርአትና የኢሉሚናቲ የሀረም/ፒራሚድ ማህተም የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ማህተም የሴራው እቅድ የንድፋዊ መግለጫ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከላይ “Annuit Coeptis—ጅማሪያችንን መርቆታል” ሲል ከስር ደግሞ፣ “Novus Ordo Seclorum—የዘመናቱ አዲስ ጅማሮ” ይላል፡፡ ከሀረሙ ጫፍ ያለችው ዓይን የሆሩስ–የፀሃይ አምላክ ሁሉን ተመልካች ዓይንየሚሉት ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን መልአክ /ሉሲፈር የነበረውን ነው፡፡ በባእድ አምልኮ ዶክትሪን መሰረት እንደሚታመነው በመንፈስ እና ቁስ አካል ውህደት (ሀረሙ ከድንጋይ፣ አለትና አፈር የተሰራው የማያውቀውን (unconscious) አካል ሲወክል ከላይ የምታበራው ዓይን ያለባት ደግሞ ቁሳዊ ባልሆነ አካል –ብርሃን ወይም መንፈስ– የሚወክል ሲሆን አዋቂው (conscious)አካል ነው፡፡ ከስር ጀምሮ ወደ ላይ የደረሰም አዲስ ሁኖ ይፈጠራል፡፡ ሀረሙ የሚያመላክተው ከሚስጥር ማህበራቱ ገብቶ ሚስጥር የሚነገረው ሰው የሚያልፍባቸውን የእድገት መአርጎች ነው፡፡ ሁሉንም ፈተናዎች ያለፈ ወደመጨረሻው መንፈሳዊ አካል ይወሃዳል፡፡ ዶላር ሌሎችም ብዙ ምልክቶች በስውር አሉበት፡፡  (more…)