Archive for May, 2012

በግደይ ገብረኪዳን

 በዚህ ባለንበት የአይምሮ ቁጥጥር ሰለባ የሆነ ማህበረሰብ ውስጥ፡ ግድ የለሽነት፣ ዝንጉ ወይም ነሆለልነት እና ተነሳሽነት ስሜት መጥፋት ምልክቶቹ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ስንኖር የሚስጥር ማህበራቱ እጅግ ሃያልና ድል አድራጊ የሆኑ መስሎ ሊሰማን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ብዙሃኑ መረጃው የሚደርሳቸው ከሆነና በመረጃው ተጠቅመው ከራስ አልፎ አገርና ትውልድን በተናጠልና በህብረት የማዳን እርምጃ ሲወስዱ ሃያል የሚመስሉት የሚስጥር ማህበራት ክፉኛ እንደተመታና እንደፈራ ውሻ ጭራቸውን ከእግራቸው ቀርቅረው እያላዘኑ ማምለጥ ግድ ይላቸዋል፡፡  (more…)
Advertisements

በግደይ ገብኪዳን
ይህ ከተክሉ አስኳሉ ጋር ከሰራነው መፅሃፍ የወሰድኩት ነው፡፡
14
ለአለምአዲስሐይማኖት
የዓለም ህዝቦች በአንድነት ተባብረው በጉልበት ሳይሆን በህግና በእኩልነት የሚገናኙበት መድረክ ቢኖራቸው የሚጠላ የለም፡፡ ሆኖም ግን ተመድ ኢ-ፍትሃዊ አሰራሩ የጭቆና፣ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ መሳርያ፣ የጥቂቶቹ መጠቀምያነቱን አጋልጠውበታል፡፡ በዚህ ምእራፍ የባእድ አምልኮ ፓንተይዝም በተመድ ውስጥ መንገሱን እንመለከታለን፡፡
እዚህ በተባበሩት መንግስታት [ድርጅት] ውስጥ በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት የተመስጦ ክፍለ ግዜ አለን፡፡ የተመስጦው መሪ ስሪ ቺን (Sri Chin)ነው፣ ስለሁኔታውም እንዲህ ነው የሚለው፡ “… የተባበሩት መንግስታት እግዚአብሔር የመረጠው መሳርያ ነው፤ የተመረጠ መሳርያ መሆን ማለት የእግዚአብሔርን የውስጥ ርእይ እና የውጭ መገለጫ የሆነ አርማ የሚይዝ ቅዱስ መልእክተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ አንድ ቀን … ዓለሙ በሞላ የተባበሩት መንግስታትን ነፍስ እንደራሱ አድርጎ በኩሩ መንፈስ ይንከባከበዋል ይጠብቀዋል፣ ይህ ነፍስ ሁሉንም አፍቃሪ፣ ሁሉንም አጥጋቢ፣ እና ሁሉንም እሚሞላ ነውና፡፡” (Donald Keys, “Transformation of Self and Society,”)
ባለፉ ግዚያት ሰዎች ተመድን ዘመናዊ የባቢሎን ግንብ እያሉ ሲጠሩት ፈጣሪ ያስቀየመውን መንፈሳዊ ድንቁርናን ለመጥቀስ ብለው ነበር፡፡ ተመድ አሁን እየጨመረ በመጣ መልኩ የተለያዩ እምነቶች ውህደት የሚንፀባረቅበት የእውን ባቢሎን እየሆነ ይገኛል፡፡ በ1960ዎቹ የተለያዩ እምነት ውህደት ተከታዮች ተብለው ይታወቁ የነበሩት ባእድ አምልኮ ተከታዮች፣ እንስታውያን (ፌሚኒስትስ)፣ ልል (ሊበራል) የሃይማኖት መሪዎች፣ ስነአካባብያውያን (ኢንቫይሮመንታሊስትስ)፣ ካባላ ተከታዮች፣ ሰብአዊ-አቅም-አቀንቃኞች (ሁማን ፖቴንሻሊስትስ) ወዘተ… ናቸው፡፡ የዛሬዎቹ ተከታዮቹ ግን ሳይንቲስቶች፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮርፖሬት ፕሬዚዳንቶች፣ የሃገራት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ባንከኞች፣ እና የትላልቅ “ቤተ ክርስቲያናት” መሪዎች ወዘተ… ናቸው፡፡ (more…)

በግደይ ገብኪዳን

ተጓዦቹ ወይም ፒልግሪም ማለት መንፈሳዊ ተጓዥ ማለት ነው፡፡ የተጓዦቹ ማህበር የአንግሎ-አሜሪካ ባላባቶች አመታዊ የራት መገባበዣ ክለብ ነው፡፡ አብዛኞቹ አባሎቹ ባንከኞች፣ ጠበቆች፣ ዋስትና (ኢንሹራስ) ሰጪዎች፣ እና የኒው ዮርክና ለንደን ከበርቴዎች ናቸው፡፡ በፖለቲካ ሂወት የገቡ አባሎችም ከዋሽንግተን ይመጣሉ፡፡ የክለቡ ቀዳሚ አላማ በዩ.ኤስና በብሪታንያ መሃከል ያለውን ግንኙነት የጠበቀ ማድረግ የሚል ነው፡፡
የፒልግሪሞች ማህበር የለንደን ቻፕተር (ቅርንጫፍ) የተመሰረተው በሐምሌ 11፣ 1902ሲሆን ይህን ተከትሎ የኒው ዮርክ ቻፕተር ደግሞ በጥር 13፣ 1903ተመስርቷል፡፡ የማህበሩ የበላይ ጠባቂ የብሪታንያ ንጉሳዊ ገዢዎች ናቸው፣ በስብሰባዎቹም አይቀሩም፡፡ ማህበሩ የኒው ዮርክና ለንደን የቢስነስና ፖለቲካ ሰዎችን የሚያስተሳስር ነው፡፡ (more…)

በግደይ ገብኪዳን

ፋብያኖች ቀደም ብለው የተመሰረቱ ማህበረሰባዊነትን “በትእግስት” ለማስፋፋት የሚታገሉ የታዋቂ ምሁራን ስብስብ ነው፡፡ ስማቸውን የወረሱት ፋብያን ከተባለ የሮማ ጀኔራል ነው፡፡ ሮም ካርቴጅ ላይ ጦርነት ባወጀችበት ግዜ፣ ፋብያን በወታደራዊ አቅም ከሃኒባል (የካርቴጅ ንጉስ) ያንስ ስለነበር ሃኒባልን ያሸነፈው በመቶዎች በሚቆጠሩ ዘመቻዎች በትእግስት ነበር፤ እኚህም ማህበረሰባውያን በፍልስፍናም በተግባርም ካፒታሊዝም ስለሚበልጣቸው በትእግስትና በመቶዎች በሚቆጠሩ ስልቶች ካፒታሊዝም እንዲወድቅ በማድረግ ድል ለመንሳት ያሰቡ ነበሩ፡፡ ታዋቂ አባላቸው በርናድ ሻው፣ ጆርጅ ዌልስ ወዘተ. ናቸው፡፡ በርናንድ ሻው ድብብቆሹ በጣም ስለተመቸው የማህበሩን ምልክት ከኤሊ ወደ የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አስቀይሮታል፡፡ (more…)

በግደይ ገብኪዳን
ጆን ረስኪን የተባለ ከ1819-1900 የኖረ፣ ለመጀመርያ ግዜ ለሱ ተብሎ በሚመስል መልኩ በአርት… የፕሮፌሰርነትን መአርግ ያገኘ በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ መምህር ነበር፡፡ የዚህ ሰው ትምህርት በማህበረሰባዊነት (socialism)ላይ ያውጠነጠነ ሁኖ እንግሊዛውያን ባላባቶች የተቀረውን የሃገራቸውን ዝቅተኛ መደብና ሌላ ያልሰለጠነውን አለም የማሰልጠን ሃላፊነት እንዳለባቸው፤ ያለዚያ ግን ነገሮች በዚሁ ከቀጠሉ የስልጣኔ ማብቅያው ሩቅ እንደማይሆን ያስተምር ነበር፡፡ በወቅቱም ከዩኒቨርስቲው ብዙ አድናቂ ወጣቶችን ማፍራት ችሎ ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል ዋነኛው ሴሲሊ ሮድስ(Cecil Rhodes) ነበር፡፡ (more…)
በግደይ ገብረኪዳን
ጆርጅ ቡሽ የዩ.ኤስ.ኤ 43ኛ ፕሬዚደንት የየል ዩኒቨርሲቲ ስከልና ቦንስ ባች ምስል  (more…)
በግደይ ገብረኪዳን

ጥቁር መሳፍንት የሚባሉት ከጣልያኖቹ፣ ቬኒስ እና ጄኖአ ገዢ ቤተሰቦች የሚገኙት ናቸው፡፡ ከ1063 እስከ 1123 ድረስ የተደረጉት የመጀመርያዎቹ ሶስቱ የመስቀል ጦርነቶች የቬኒሳውያን ጥቁር መሳፍንት ስልጣንን እንዲያገኙና እንዲጠናከሩ አድርገዋቸዋል፡፡ ቬኒስን ሙሉ ለሙሉ በ1171 ስልጣን ወደ ታላቁ መማክርት ለሚባለው የነጋዴ ባላባቶች ስብስብ ሲተላለፍ ነበር የተቆጣጠሩት፡፡ (more…)