Archive for the ‘ባእድ’ Category

በግደይ ገብረኪዳን
የ2012 ኦሎምፒክ መክፈቻና መዝጊያ ስነ ስረአት በአምስቱም ክፍለ ዓለማት አንድ ቢሊዮን ገደማ ሰዎች ለመታየት በቅቷል፡፡ ሁሌም ከፍተኛ ቦታ እንደሚሰጣቸው የሚድያ ክስተቶች ሁሉ የዓለማችን ቁንጮዎች መልእክቶች፣ ምልክቶች እና አጀንዳዎቻቸው የትእይንቱ አካል ነበሩ፡፡ እኚህን በለንደን ኦሎምፒክ እንዳስሳለን፡፡
የኦሎምፒክ ክብረ በዓላት በምድራችን ሰፊ ተመልካች ከሚያገኙት ትእይንቶች አንዱ ነው፡፡ ላስተናጋጅ ሃገሪቱ ታላቅነቷን የምታሳይበት አጋጣሚዋ ነው፡፡ (ወጪውን በግብር መልክ የሚሸፍነው ድሃው ህብረተሰብ ይሸከመዋል፡፡) የለንደን ኦሎምፒክም ከዚሁ የተለየ አልነበረም፡ የእንግሊዝ ታሪክ፣ ባህል፣ እና ስኬቶች በበዓሉ ቀርበው በሚገባ ተሞግሰዋል፡፡ አንዳንድ ክስተቶች እፁብ ነበሩ ሌሎች የሚያስቁም ነበሩ፤ የሚያስፈሩ እና የሚረብሹም ክስተቶች ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ ከፍተኛ ተምሳሌትነት ያላቸውና የቁንጮዎቹን አጀንዳ የሚያንፀባርቁ ነበሩ፡፡ ለንደን የዓለማችን ቁንጮ የስልጣን ማማዎች መገኛ እንደመሆኗ በበዓላቱ የቁንጮዎቹ ምልክቶችና ፍልስፍና ባይንፀባረቅ ኑሮ ይበልጡኑ አስገራሚ ይሆን ነበር፡፡
ሁሉም ነገር ተምሳሌታዊ ነበር ማለት አይደለም፣ ሁሉም ምልእክትም አይን ያወጣ ግልፅነት አልነበረውም፣ በዓሉ በፈጀበት ሰዓቶች ግን ለመላው ዓለም ህዝብ ሰፊ መልእክት ተላልፏል፡፡ እስኪ እንመልከታቸው፡፡ (more…)
Advertisements
በግደይ ገብረኪዳን
I will not cease from mental fight,
Nor shall my sword sleep in my hand
Till we have built Jerusalem
In England’s green and pleasant land.
ከአይምሯዊ ውግያ ላፍታም አልቆምም
ሰይፌም ቢሆን በጄ አያንቀላፋም
እየሩሳልምን እስክንገነባ
በእንግሊዝ አረንጓዴና አስደሳች ሜዳ

የላይኛው ግጥም በ18ኛው ከ/ዘ የእንግሊዝ ታላቅ ገጣሚ እና በባእድ ሚስጥራት የተዘፈቁ ስራዎቹ የሚታወቀው ሰው: ዊልያም ብሌክ ግጥም የተወሰደ ነው፡፡ ይህ ድብቅ እቅዳቸውን በይፋ የለፈፈበት ፅሁፉ ይሆን፣ ውስጥ አዋቂ እንደነበር የታወቀ ነው፡፡ (more…)

በግደይ ገብኪዳን
ይህ ከተክሉ አስኳሉ ጋር ከሰራነው መፅሃፍ የወሰድኩት ነው፡፡
14
ለአለምአዲስሐይማኖት
የዓለም ህዝቦች በአንድነት ተባብረው በጉልበት ሳይሆን በህግና በእኩልነት የሚገናኙበት መድረክ ቢኖራቸው የሚጠላ የለም፡፡ ሆኖም ግን ተመድ ኢ-ፍትሃዊ አሰራሩ የጭቆና፣ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ መሳርያ፣ የጥቂቶቹ መጠቀምያነቱን አጋልጠውበታል፡፡ በዚህ ምእራፍ የባእድ አምልኮ ፓንተይዝም በተመድ ውስጥ መንገሱን እንመለከታለን፡፡
እዚህ በተባበሩት መንግስታት [ድርጅት] ውስጥ በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት የተመስጦ ክፍለ ግዜ አለን፡፡ የተመስጦው መሪ ስሪ ቺን (Sri Chin)ነው፣ ስለሁኔታውም እንዲህ ነው የሚለው፡ “… የተባበሩት መንግስታት እግዚአብሔር የመረጠው መሳርያ ነው፤ የተመረጠ መሳርያ መሆን ማለት የእግዚአብሔርን የውስጥ ርእይ እና የውጭ መገለጫ የሆነ አርማ የሚይዝ ቅዱስ መልእክተኛ መሆን ማለት ነው፡፡ አንድ ቀን … ዓለሙ በሞላ የተባበሩት መንግስታትን ነፍስ እንደራሱ አድርጎ በኩሩ መንፈስ ይንከባከበዋል ይጠብቀዋል፣ ይህ ነፍስ ሁሉንም አፍቃሪ፣ ሁሉንም አጥጋቢ፣ እና ሁሉንም እሚሞላ ነውና፡፡” (Donald Keys, “Transformation of Self and Society,”)
ባለፉ ግዚያት ሰዎች ተመድን ዘመናዊ የባቢሎን ግንብ እያሉ ሲጠሩት ፈጣሪ ያስቀየመውን መንፈሳዊ ድንቁርናን ለመጥቀስ ብለው ነበር፡፡ ተመድ አሁን እየጨመረ በመጣ መልኩ የተለያዩ እምነቶች ውህደት የሚንፀባረቅበት የእውን ባቢሎን እየሆነ ይገኛል፡፡ በ1960ዎቹ የተለያዩ እምነት ውህደት ተከታዮች ተብለው ይታወቁ የነበሩት ባእድ አምልኮ ተከታዮች፣ እንስታውያን (ፌሚኒስትስ)፣ ልል (ሊበራል) የሃይማኖት መሪዎች፣ ስነአካባብያውያን (ኢንቫይሮመንታሊስትስ)፣ ካባላ ተከታዮች፣ ሰብአዊ-አቅም-አቀንቃኞች (ሁማን ፖቴንሻሊስትስ) ወዘተ… ናቸው፡፡ የዛሬዎቹ ተከታዮቹ ግን ሳይንቲስቶች፣ ዲፕሎማቶች፣ የኮርፖሬት ፕሬዚዳንቶች፣ የሃገራት መሪዎች፣ ዓለም አቀፍ ባንከኞች፣ እና የትላልቅ “ቤተ ክርስቲያናት” መሪዎች ወዘተ… ናቸው፡፡ (more…)

በግደይ ገብረኪዳን

ዝነኛውአሊስተርክራውሊ“666 አውሬው” እና “ከሰዎችሁሉክፉው” መባል የሚመርጠው ይህ ሰው ታራ የሚድያ ጀብደኛ ብቻ አይደለም የነበረው፡፡ ስራዎቹ ከብዙሃኑ ይልቅ በታዋቂ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደሩ፣ ከብሪታን ያደህንነት ተቋማት ጋር የሰራ የ20ኛውና 21ኛውክ/ዘመን ሃያል እንቅስቃሴዎችን አቅጣጫ ያስያዘ ሰው ነው፡፡ እንደቢቢሲ ምርጫ ከሆነ ይህን ሰው ከምን ምግ ዜታላላቅ ብሪታንያውያን መሃከል  73ኛ ደረጃ ሰጥቶታ፡፡

በግደይ ገብረኪዳን
ባለም ዓቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆኑት የሆሊ ዉድ፣ አሜሪካ ዘፈን ቪድዮዎችና ፊልሞች ውስጥ የሚገኙት ስውር መልእክቶች ለሚያውቃቸው ዓይኖች እጅግ ቀላልና ብዙ ናቸው፡፡ ከስር በዝርዝር ሳንገባበት በምስሎቹ እየተመራን አንዳንድ ከጀርባቸው ያለውን ሚስጥር እንመረምራለን፡፡ በአብዛኞቹ ዝነኛ ሰዎች የሚወደደው ምልክት የቢራቢሮ ምስል ነው ይህ የሆነበት ምክንያት ከአእምሮ ቁጥጥር ጋር ስለሚገናኝ ነው፡፡ በቅድሚያ ትንሽ ስለዚህ ጉዳይ ማለት ያስፈልጋል፡፡ (more…)

በግደይ ገብረኪዳን
የአሁኑ ፖፕ ሙዚቃ የወጣቶችን አመለካከት ለመቅረፅ በምልክቶችና መልእክቶች የተሞላ ነው፡፡ ከላይ ከጠቃቀስናቸው የባእድ አምልኮ ምልክቶች በተለየ ሌሎች የቁንጮዎቹ አጀንዳ መልእክቶች በሙዚቃ ቪድዮዎች በኩል ይተላለፋሉ፡፡ በሙዚቃ ከሚተላለፉት አጀንዳዎች ሁለቱ፡ ሰብአዊነት-ሸገር እና የፖሊሳዊ አገዛዝን ማስተዋወቅ ናቸው፡፡ እነዚህን አጀንዳዎች እንደነ ሪሃና፣ ቢዮንሴ፣ ዳዲ ያንኪ፣ ብላክ አይድ ፒስ ያሉዘፋኞች ሲያስተላልፏቸው እንመለከታለን፡፡ 

(more…)

በግደይ ገብረኪዳን

“ሜትሮፖሊስ”፡ የቁንጮዎች ፊልም
የፍሪትዝ ላንግ የ1927 ዓ.ም “ሜትሮፖሊስ” የተሰኘው ፊልም ግዜ ከማይሽራቸው ክላሲካል ስራዎች የሚመደብ ነው፡፡ ከመረሳት ይልቅ ፊልሙ የሚያወሳቸው ጉዳዮች እንደ ትንቢት ከእውነታ ጋር ይበልጥ እየገጠሙ የሚሄዱ ናቸው፡፡ የፊልሙን የባእድ አምልኮ መልእክቶችንና የዛሬዎቹ ዝነኛ ሰዎች እንደነ ማዶና፣ ሌዲ ጋጋ፣ ቢዮንሴ፣ ካይሊ ሚኖግና ሌሎችም በስራዎቻቸው ከፊልሙ የሚዋሱትን ገፅታዎች እንዳስሳለን፣ በዚህም እስካሁን ለማቅረብ እየሞከርን እንዳለነው ከላይ የተቀነባበረ ከብዙሃኑ የተሰወረ ግብ ይዘው የሚሰሩ ቁንጮዎች እንዳሉ ከመዝናኛ ኢንዱስትሪው አንፃር መረዳት እንችላለን፡፡
  leadmetro1
ሜትሮፖሊስ ድምፅ አልባ ሳይንሳዊ ልብ-ወለድ ፊልም ሲሆን የተሰራውም በ1927 በፍሪትዝ ላንግ ነው፡፡ ለወደፊት ለሁለት ቀጠናዎች የተከፈለ የመከራ ዓለም (ዲስቶፕያ) ላይ የሚያጠነጥን ፊልም ነው፡፡ ሃሳባውያኖቹ እና ላብአደሮቹ – ሁለት ተቃራኒዎች በሁለት መደብና ቀጠና ተከፍለው የሚኖሩባት ዓለም – ሜትሮፖሊስ በማህላቸው ያለውን ትግል ያሳያል፡፡ ሜትሮፖሊስ አዲስ የዓለም ስርአት በተግባር የዋለበትን የተመረጡት ቁንጮዎቹ በቅንጦት ሲኖሩ ብዙሃኑ ደሞ ከሰብአዊነት በወጣ ሙሉ ለሙሉ ቁጥጥር ስር ባለ ገሃነም የሚኖሩትን ሂወት ያሳያል፡፡
የዚህ ፊልም ትርኢቶች በዛሬው ዘመናዊ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ በስፋት ተደግመው ይቀርባሉ፡፡ በተለይ ዘፋኞች ማርያ የምትባለዋን ሰው መሰል ሮቦት ገፀ-ባህሪን በተደጋጋሚ መስለው ይቀርባሉ፡፡ ማርያ በቁንጮዎቹ የተሰራችው የላባደሮቹን ሞራል (ግብረገብ) ለመበረዝና የአመፅ መንገድ እንዲከተሉ ለማነሳሳት ሲሆን ይህም ቁንጮዎቹ የሃይል የጭቆና መንገድ እንዲጠቀሙ ማስተባበያ ያስገኝላቸዋል፡፡ ዛሬ ዝነኛ ዘፋኞቹ በዚሁ መንገድ ቁንጮዎቹ እየተጠቀሙባቸው ይሆን?

 የፊልሙ ትንተና

ላባደሮቹ

ፊልሙ ከመሬት ስር በተቆረቆረችው የላባደሮቹን ከተማ በማሳየት ይጀምራል፡፡ አንድ አይነት ለብሰው፣ በሰልፍ ባንድ አይነት አካሄድ አገታቸውን አቀርቅረውና ተስፋ በቆረጠ አኳኋን ሲጓዙ ያሳያል፡፡ በፊልሙ ሙሉ ትእይንት እኚህ ሰዋዊ ከብቶች በአካልና አእምሮ ደክመውና ደንዝዘው ነው የቀረቡት፡፡ እንደ ከብት መንጋ ሰራተኞቹ በአንድ ነው የሚሰማሩት (የሚሄዱት)፡፡ በቀላሉም የሚታለሉ ናቸው፡፡ ይህ አይነት አኳሃናቸው ከፊልሙ መሰራት አምስት አመትቀድሞ አሜሪካዊው ንድፈ ሃሳባዊው ዋልተር ሊፕማን በ Public Opinionፅሁፉ ብዙሃኑን እጣ ፈንታውን መቆጣጠር ከማይችል ከተደናበረ መበንጋ ጋር በማነፃፀር ፅፎ ነበር፡፡ የጀርመን ናዚዎች ፕሮፖጋንዳ ሃላፊው ጆሴፍ ጎቤልስ ፊልሙ ስለ ብዙሃኑ የሚያሳየው አይነት አመለካካት ነበረው፡፡ ሂትለር ከሚታወቁለት ዝነኛ አባባሎቹ አንዱ፡ “መሪዎች እንዴት እድለኛ ናቸው ሰዎች ማሰብ የማይችሉ በመሆናቸው፡፡” ብሎ ነበር፡፡ 

 metro1-e1287692852114
 ላባደሮቹ በስራ መቀያየርያ ሰአት ሰሲወጡና ሲገቡ፡፡

ሰራተኞቹ እጅግ ግዙፍ የሆነ ማሽን ውስጥ ከሰብአዊነት ውጪ የሚያደርግ አንድ ተደጋጋሚ ስራ ብቻ ሲሰሩ ይውላሉ፡፡ በፊልሙ አንድ ትእይንት ላይ ማሽኑን ከሞሎክ ጋር የሚነፃፀርበት አለ፡፡ ሞሎክ በባእድ አምልኮ ልጆች በእሳት መስዋእት የሚቀርቡለት ባእድ አምላክ ነው፡፡   

 ከስር በስተቀኝ፡ ዋናው ገፀ-ባህርይ ፍሬደርሰን ማሽኑ ሞሎክ መስሎ ሲታየው የሚሳይ ትእይንት፡፡ ላባደሮቹ ለአውሬው (ማሽን) እንደ መስዋእት ይሰጣሉ፡፡

 ከላይ፡ ሞሎክ በአል የተባለው አምላክ፣ የፀሃይ ኮርማው በጥንት መካከለኛው ምስራቅ እና የካርቴጅ ስልጣኔ በተሰራፋበት ቦታ ሁሉ ይመለክ ነበር፡፡ በአል ሞሎክ ጥጃ ወይም በሬ ወይም ደሞ የኮርማ ራስ ያለው ሰው ተደርጎ ነበር የሚቀረፀው፡፡ መስዋእት የሚደረግለትም በከርሱ እንዲያልፍ ይደረጋል፡፡ ሰራተኞቹ የሚሰሩት ስራ ሙሉለሙሉ የማይቀየር እንቅስቃሴ (ሜካኒካል) ነው፣ ምንም የጭንቅላት ስራ የለውም፣ ይህም ሰዎቹን የማሽኑ ቅጥያ አካሎች የሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

 ሃሳባውያኑ

ላባደሮቹ ገሃነም የሆነ የምድር ስር ዲስቶፕያ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ሃሳባውያኑ ደመሞ ከሚያንፀባርቅ ገነታዊ ዩቶፕያ ላይ ይኖራሉ፡፡ ይህች የምታንፀባርቅ ከተማ ግን ያለ ማሽኑ (ሞሎክ) እና የሰራተኞች መንጋ ህልውና አይኖራትም፡፡በሌላ በኩል ደሞ እንዲህ ያለ ከተማን ለማቆም ባይሆን ኑሮ ማሽኑ አያስፈልግም ነበር፡፡ በዚህ እይታ ሁለት ተቃራኒ ህልውናዎች እርስ በራሳቸው ላይ ጥገኛ የሆኑበትን ሁኔታ እናገኛለን፡ ይህ ጭብጥ የሚስጥር አምልኮ አስተምህሮቶች ቃና ያለው ነው፡፡   3

4

 አንፀባራቂው የሃሳባውያኑ ከተማ፡፡ ፊልሙ ላባደሮቹና ሃሳባውያኑ የሚኖሩበትን ተቃራኒ ሀሁኔታ በሚስጥራዊ አስተምህሮ አገላለፅ፡- “ከላይ እንደሆነው፣ እንዲሁም ደሞ ከስር ይሆናል፡፡” የሚለው ሚስጥራዊ አስተምህሮን በስሱ በማጣቀስ ሁኔታቸውን ያሳየናል፡፡

5

“ከላይ እንደሆነው፣ እንዲሁም ደሞ ከስር ይሆናል፡፡” የሚለውን ጭብጣቸውን የሚያሳዩበት አንደኛው ምልክት፡- ተቃራኒ የሆኑ ጉልበቶች በእኩል ተቃራኒ በመቆም በማህላቸው ሚዛን እንዲኖር ያደርጋሉ፡፡ የፊልሙ ሰሪ ፍሪትዝ ላንግ ዓለም ይህን ጭብጥ በሚገባ ለማብራራት የሚከረ ነው፡፡

 ጆ ፍሬደርሰን

ከተማዋ የተመሰረተችው፣ የተገነባችውና የምትተዳደረው በአምባገነኑ ጆ ፍሬደርሰን ነው፡፡ የሜትሮፖሊስ ብቸኛ ሰሪና አስተዳዳሪ እንደመሆኑ ፍሬደርሰን ከግኖስቲሳውያውን አምላክ ዲሙርግ የቁሳዊ አለም ፈጣሪና ገዢ ከሚሉት ጋር ይመሳሰላል፡፡

  6 7
 ከላይ፡ ጆ ፍሬደርሰን ቀጣይ ስራውን ሲያስብ፡፡ በእጁ ኮምፓስ ይዟል፣ ይህ ለተመልካቾች የሜትሮፖሊስ “ታላቁ ገንቢ” ሚናነቱን እንዲያስታውሱ ያደርጋል፡፡ ከጎኑ እንግሊዛዊው ገጣሚ ዊልያም ብሌክ ያቀረበው የግኖስቲሳውያኑ አምላክ ዲሙርግ ፍፁም ያልሆነው ሃጥያትና ስቃይ የበዛበት የታችኛው ዓለም ፈጣሪ ነው የሚሉት ሲሆን ኮምፓስ በእጁ ይዟል፡፡ በፍሪሜሶንም አምላክን “የዩኒቨርስ ታላቁ ገንቢ” ነው የሚሉት፡፡

ፍሬደር የተባለው የጆ ልጅ እንደሁሉም የቁንጮዎች ልጆች የቅንጦት ሂወት ሲመራ ነበር ከምድር ስር እየማቀቁ ያሉትን የላባደሮቹን ስቃይ ማወቅ የጀመረው፡፡ ስቃያቸውን በራሱ ልምድ ለመረዳት ወደ ታች በመውረድ ከአንድ ላባደር ጋር ሂወት ተቀያይረው መኖር ይጀምራል፡፡ ታች ወርዶ ፍሬደር ማር ከተባለች የላባደሮቹ አፅናኝ ጋር ተዋወቀ፡፡

 ማሪያ

 8

 ማሪያ ሰራተኞቹን ስትሰብክ፡፡ ማሪያ ሰራተኞቹ ሁሉ የሚወዷት አጋራቸው ነች፡፡ ስቃያቸውን በመረዳትና እየገነፈለ ያለውን የአመፅ ስሜታቸውን በማጤን አስታራቂ ይመጣል እያለች ሰላምና መቻቻል ታስተምራቸዋለች፡፡ “በጭንቅላት (ሃሳባውያኑ) እና በእጅ (ላባደሮቹ) መሃል ልብ የሚሆን፡፡” አንድ ትእይንት ላይ ማርያ ስለ ባቢሎን ግንብ ትነግራቸዋለች፣ በግንቡ ላይም፡ “ዓለምና ሰሪዋ ታላቅ ነው! ሰውም ታላቅ ነው!” የሚል ይፃፍበታል ትላቸዋለች፡፡ ይህ ዓ.ነገር ከሚስጥር አስተምህሮቶች ጋር ከፍተኘዝምድና አለው፣ ሰዎች እውቀታቸውን ከፍ በማድረግና አብርሆት በማግኘት እንደ አማልክት መሆን ይችላሉ ብለው ስለሚያስተምሩ፡፡ በዘመናት ታሪክ፣በሃውልቶችና ሌሎች ስራዎች እኚህ የሚስጥር መርሆችን ለማሸጋገርና የሰው አይምሮ ታላቅነትን ለማሰብ ብዙ ተሰርተዋል፡፡ በከፊልም በዚህ ምክንያት ነው በፍሪሜሶንና በባቢሎን ግንብ መሀከል ግንኙነቱ ይታያል የሚባለው፡፡

ማርያ ቀጥላም “ያንዱ ሰው ውደሳ የሌላው ሰው መርገም ሆነ፡፡” ትላለች፡፡ በሌላ አነጋገር የሰውን ታላቅነት የሚያወድሰው ግንባታ የተሰራው ስለ ሃሳባውያኑ ታላቅ ርእይ ምንም ግንዛቤ ባልነበራቸው ላባደሮች ደምና ላብ ነው ማለት ነው፡፡ በፊልሙም እንዲህ አይነት ሁኔታ ተደግሞ እየተተገበረ ይታያል፡፡ ይህ እንደ አማልክት የሆነው ጆ ፍሬደርሰን የመኖርያው ህንፃ ስም አዲሱ የባቢሎን ግንብ ነው፡፡

 9

የጆ ፍሬደርሰን ዋና ፅህፈት ቤት ስም አዲሱ የባቢሎን ግንብ ነው፡፡

 ሮትዋንግ

ሰራተኞቹ አመፅ እያሰቡ እንዳለ ባወቀ ግዜ ጆ ፍሬደርሰን ለምክር ወደፈጠራ ሙያተኛውና እብዱ ሳይንቲስት ሮትዋንግ ዳር ይሄዳል፡፡

 10

 ከጎን፡ ሳንቲስቱ ሮትዋንግ ከሚታወቅበት የብረት ቀኝ እጁ ጋር፡፡ ይህ ብረት ሙከራ በሚያደርግበት ግዜ ላጣው እጁ ያደረገው ነው፡፡ ይህ ማለት ሮትዋንግ የግራ አስማትን ነው የሚከተለው ለማለት ይሆን?
ይህ ሰው ስራዎቹ ምርጥ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም መሆኑን ቢያሳዩም ለፈጠራ ስራዎቹ ከጥንታዊ ባእድ አምልኮ እውቀቶች እንደሚጠቀም በፊልሙ ብዙ ቦታዎች ላይ ፍንጮች ተቀምጠዋል፡፡ መኖርያው ይላል ፊልሙ፡ “በዘመናት የተዘነጋ ትንሽ ቤት” ነው ይላል፡፡ የዚህም ተምሳሌትነቱ የሳይንቲስቱ እውቀት በዘመናት ለጥቂቶች ብቻ ሲስተላለፍ የኖረ መሆኑን ያሳያል፡፡ የመኖርያው ምድር ቤቱ 2000 ዓመታትን ያስቆጠረ የዋሻ መቃብር ውስጥ የሚወስድ የሚስጥር መተላለፍያ አለው፣ ይህም በተጨማሪ ስለ ሮትዋንግ ጥንታዊና ሚስጥራዊ ምንጭ የሚያመላክት ፍንጭ ነው፡፡ በተጨማሪም የፊት በሩ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ (ፔንታግራም) አርማ አለው፣ ይህም ከፓይታጎረሳውያን፣ ባእድ አምልኮና ፍሪሜሶን ጋር ያለውን ትስስር ያሳያል፡፡
 11

ከጎን፡ የሮትዋን በር ላይ ፔንታግራም ይታያል፡፡

የፓይታጎራስ ተማሪዎች በራቸው ላይ ይህን ምልክት ያደርጉ ነበር፡፡ በአሁኑ ግዜ ይህ ኮከብ በስፋ ጥቅም ላይ የዋለ ቢሆንም ሚስጥራዊ ትርጉሙ ግን አይታወቅም፡፡ ከፓይታጎራስ ሚስጥር የተማሩ ብቻ በትክክል አድርገው ሊስሉትና ጂኦሜትሪያዊ ፍቺውን ሊረዱት ይችላሉ፡፡ እንደ ጆ ፍሬደርሰንና ሮትዋንግ ያሉ የመሪ እና ጠንቋይ ትስስር ያላቸው ሰዋች ከታሪክ ብናጣቅስ አናጣም፡፡ የፈጠራ ሙያተኛው ሮትዋንግ የሰራውን ስራ ለፍሬደርሰን ይሰጠዋል፡- ማሽን ሁኖ ሰው የሆነ፣ የወደፊቱን ሰው የሚወክል የፈጠራ ስራውን፡፡ ይህ ግማሽ ሰው ግማሽ ማሽን የሆነው ሮቦት የማንኛውንም ሰው ቅርፅ መያዝ ይችላል፡፡ ሮትዋንም እንዲህ ይላል፡- “ማንም ሰው ይህ የማሽን ሰውን ከትክክለኛ ሟች መለየት አይቻለውም፡፡” ይገርማል የዘመናዊዎቹ ሰብአዊ-ሸገሮች (transhumanist) ህልም በ1920ዎቹም ነበር ማለት ነው፡፡ ሰብአዊ-ሸገሮች በቴክኖሎጂ የሚያምኑና በዚህም የሰውን ልጅ እንደ አማልክት የማይታመም የማይሞት ለማድረግ እንችላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡ ይህን ሲሰማ ፍሬደርሰን ለሮትዋንግ ማሽኑን ማሪያን አስመስሎ እንዲሰራ ይነግረዋል፣ የታማኝነቷንና ተወዳጅነቷን ተጠቅሞ በሰራተኞቹ ውስጥ ብክነት ሊያሥፋፋ፡፡

 12

 ማሪያ ተኝታ አምሳያዋን ለማሽኑ ሲሰጥ፡፡ ከኋላ ከማሽናዊው ሰው በላይ የተፈጠፈውን የተገለበጠ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ ልብ በሉት፡፡ አንድ ጫፉ ወደ ላይ የሆነው ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ መዳንን፣ የሂሳብ ስሌት ፍፁማዊነትን እና አምስቱን ባህርያት ከወከለ የተገለበጠው ኮከብ ደግሞ የነዚህን ማዛባትና ጥቁር አስማትን ይወክላል፡፡

እና የዛሬዎቹ ኮከቦች በቁንጮዎቹ በሳይንስና ባእድ አምልኮ ቅልቅል አይምሯቸው ተሞልቶ (ፕሮግራምድ ተደርገው) ከዚህች ማሽን ሰው ጋር የሚያገናኝ ነገር ይኖራቸው ይሆን? በእርግጥም አላቸው፡፡ ከስር ኮከቦቹ እንደሮቦቷ ሁነው ይታያሉ፡

 13

ቢዮንሴ

14    ካይሊ ሚኖግ

 15

      ሌዲ ጋጋ፡፡

16

  የኲዊን ባንድ አባል ፍሬዲ ሜርኩሪ ራድዮ ጋጋ በሚለው ዘፈን ፊቱ በማሪያ ቦታ ገብቶ፡፡ የሌዲ ጋጋ ስም መነሻ ሃሳቡን ያገኘው ከዚሁ ዘፈን ነው፣ ይህ ዘፈንም ብዙ ትእይንቶችን በቀጥታ ከሜትሮፖሊስ ፊልም ላይ ያሳያል፡፡

17

ጃኔሌ ሞኔ

 18

 ከላይ፡ በፋሽን መፅሄቶችም ላይ ሜትሮፖሊስ ገኗል፡፡

19

ከጎን፡ ሌዲ ጋጋ በከፍተኛ መጠን ሜትሮፖሊስን መሰረት አድርጎ በተነሳ ፎቶዋ፡፡

ወደ ፊልሙ ስንመለስ የማሽን ሰዋ ተሰርታ ካለቀች በኋላ ሮትዋንግ የሚከተለውን ይላል፡ “ባምሳያዋ የተፈጠርሽባትን ሴትዮ ስራ እንድታጠፊ፣ ከታች ያሉትን ሰዎች እንድትጎነኛቸው እፈልጋለው፡፡”

ሮቦት ማሪያ በበኩልያ የሚከተለውን መልስ ትሰጠዋለች፡-

20

አንድ አይን መጨፈን ትልቅ ትርጉም አለው፣ የሚወክለውም ፒራሚዱ ጫፍ ላይ የሚስሉት ሁሉን ተመልካች የሆሩስ አይን ነው፡፡ ይህን ምልክት ብዙ አርቲስቶች ይጠቀሙበታል፡፡

ማሪያ ወደ ታች ተልካ ዮሺዋራ የተባለ የወንዶች ክለብ ውስጥ በመሄድ ወሲብ ቀስቃስ ዳንስ ታሳያቸዋለች፡፡ በአደኛው ተውኔቷ እንደ ባቢሎን ታላቂቱ ጋለሞታ ተደርጋ ትቀርባለች፡፡ ስእሉን ከስር ይመልከቱት፡፡ ራዕይ 17፣ 4 ፡ “ሴቲቱም በቀይና በሐምራዊ ልብስ ተጎናፅፋ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቆችም ተሸልማ ነበር፣ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገር የዝሙትዋም ርኩሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ያዘች፤…” ይላል፡፡ የተሸከሟት ራሶች እና ቀንዶች ጠቅላላ ከራዕይ ትርጓሜ ጋር የሚነፃፀሩ ናቸው፡፡

21
ከጎን፡ በሜትሮፖሊስ ፊልም ላይ ሮቦቷ ማሪያ የባቢሎን ታላቂቱ ጋለሞታ ሁና ስትጨፍር፡፡

22

ከላይ ማዶና በተመሳሳይ ሁኔታ ማተሪያል ገርል የሚለው ዘፈኗ ላል፡፡ የተሞላችው /ፕሮግራምድ የተደረገችው/ ሮቦቷ ማሪያ የሚያፈዝ ዳንሷን ለህዝብ በማቅረብ፣ ሰዎች እንዲጣሉ፣ እንዲመኙ፣ እንዲቀናኑና ሃጥያቶችን እንዲሰሩ ታደርጋቸዋለች፡፡ ከስራ አጋሮቿ ጋር ስትሆን ጆ ፍሬደርሰን ጉልበት ለመጠቀም ምክንያት እንዲያገኝ ማሪያ ለአመፅ እንዲነሳሱ አሳሳች ኤጀንት ሁና ትሰራለች፡፡ በስውር የህዝቡን ጥቅም የሚጎዳና የቁንጮዎቹን የሚያስጠብቅ ተግባራት ላይ ትውላለች፡፡ በራሳቸው ማሰብ ስለማይችሉ በተቆጣጣሪያቸው እርዳታ ላባደሮቹ መጨረሻ ላይ በሮቦቷ ማሪያ መታለላቸውን ይገነዘባሉ፡፡ መተተኛ ነች በማለት እንጨት ላይ ሮቦቷን ማሪያን አቃጠሏት፡፡ እያለ ይቀጥልና ፊልሙ የሚከተለውን በማስነበብ ይፈፀማል፡

23

ከጎን፡ ፍቺው በጭንቅላትና በእጆች መሃከል አስታራቂው ልብ መሆን ይኖርበታል፡፡

ይህ የታሪኩ መልእክት ለቁንጮዎቹ የተለገሰ ምክር ነው፣ ብዙሃኑን ከእይታቸው እንዳያወጡ፡- ጭቁኖቹ ሳያማርሩ እንደረኩ እንዲኖሩ ልባቸውን መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ዛሬ ሚድያው የሚፈፅመው ተግባርም ይህንኑ ነው፡፡ አንድ የማዶና ዘፈንም ሲያልቅ ይህንኑ መልእክት ያስተጋባል፡  ኤክስፕረስ ዩርሰልፍ የሚለው ዘፈኗ በስፋት ትእይንት አፈጣተሩን ከሜትሮፖሊስ ይዋሳል፡፡

24

በሌላ በኩልም የክርስቲና አጉሌራ ኖት ማይሰልፍ ቱናይት የሚለው ዘፈኗ ከዚህኛው የማዶና ዘፈን ይዋሳል፡፡

የፊልሙ ዋና መልእክት

የሜትሮፖሊስ ታሪክ መልእክቱ “ያለፈውን ነገር ሁሉንም አጥፍተን እንደአዲስ ሁሉም እኩል የሆነበትን አዲስ ዓለም እንገንባ፡፡” የሚል አይደለም፡፡ “ዲሞክራሲያዊ እንሁንና እንዲመራን የምንፈልገውን ሁላችንም እንምረጥ፡፡” የሚልም አይደለም፡፡ ይበልጥ የፊልሙ መልእክት የሚሆነው “ላባደሮቹን ከሚገባቸው ከምድር ስር መልሰን እንላካቸውና በነሱና በሃሳባውያኑ መሃከል ግን አስታራቂ የሚሆን ነገር መፍጠር ይኖርብናል፡፡” የሚል ነው፡፡ በዛም ወጣ በዚም ወረደ ፊልፉ የቁንጮዎች ነው፡- ሁሉንም የህብት ምንጭ በቁጥጥሩ የሚያደርግና የላባደሮቹን ስራ የሚያስተዳድር ቁኝጮ አካ እንዲኖር ጥሪውን ያቀርባልና፡፡ በስተመጨረሻ ላባደሮቹና ፍሬደር ተታለዋል፡- ሁኔታችን ይስተካከላል ብለው ሲያስቡ፡፡ አንድም የተቀየረ ነገር አልነበረም፣ እንዲያውም ጆ ገራገር ልጁ ቁንጮዎች የዋህ ናቸው የሚል ምስል በላባደሮቹ እንዲቀረፅ ተጠቅሞበታል፣ በሌላ በኩል ከስር የሚደረገውን ሁሉንም ነገር መረጃ ለማግኘት ችሎበታ፡፡ የዛሬው ሰራተኛ መደብ ፍሬደር ማን ነው? መልስ፡ ሚድያው፡፡ ሚድያ አስታራቂ ነው፡፡ ዋናው ስራው ማታለል ነው፡፡

25

ፍሬደር፣ “በእጅ እና በጭንቅላት” መሃከል ያለው አገናኝ፣ ላባደሮቹና ሃሳባውያኑ፡፡ ይህ ሚና ዛሬ በሚድያው የተያዘ ነው፡፡

መገናኛ ብዙሃን በእለት ተእለት የብዙሃኑን  ሃሳብ ይጠመዝዛሉ፣ ጭቆናቸውን እንዲወዱ ያታልሏቸዋል፡፡ ተወዳጅነት የሚያተርፉ ባህሎች/ልማዶች የመገናኛ ብዙሃን የመዝናኛ ቅርጫፋቸው ነው፣ ሙዚቃ ደሞ የቁንጮዎቹን መልእክት በሚያዝናና መልኩ የሚተላለፍበት መንገድ ነው፡፡ በሙዚቃዎች ሜትሮፖሊስን መጠቀም ለውስጥ አዋቂዎቹ ተግባራቸውን እንደዋዛ በኮድ የሚግባቡት መንገዳቸው ነው፡፡ ለውስጥ አዋቂዎቹ ይህ ኮከብ ለኛ ነው እየሰራ ያለው እንደማለት ነው፡፡ ቪድዮዎቹ እንደሚያሳዩት ሞራሉ የወረደ፣ ፉዞና ቁሳዊ መሆን በነሱ  እንደመውደቅ ማለት ነው፡፡

 በዛሬው ዘመናዊ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ እና ሜትሮፖሊስ መሃከል ያለ ዝምድና

ለምንድን ነው ሜትሮፖሊስ የኢሉሚናቲ ቅጥረኛ ኮከቦች ኮድ የሆነው? ፊልሙ የዛሬ የኢሉሚናቲ አጀንዳዎችን በሙሉ ይነካል፡- ሰብአዊነት-ሸገር፣ አይምሮ ቁጥጥር፣ ጥቁር መተት፣ የሞራል መውደቅ፣ ፖሊሳዊ አገዛዝ፣ ሁሉን ተመልካች መንግስት የመሳሰሉትን፡፡ ሜትሮፖሊስ ለህዝብ ቁጥጥር የንድፍ ወረቀት ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንደ ማሪያ የዛሬዎቹ ኮከቦች ከሰራተኛው መደብ ይገኛሉ፣ ቀጥለውም በቀጥተኛ የቃሉ ፍቺ መሰረት ይሞላሉ ((አይምሯቸው ፕሮግራምድ ይደረጋል፡፡) ቀጥለውም የተደበቁት ገዚዎች ቃል አቀባዮች ይሆናሉ፡፡ ኮከብ ዘፋኞቹ አብዛኞቹ የራሱስምና ስብእና ያለው ሌላ ምንነት (አልተር-ኢጎ) አላቸው፡፡ ይህ የአይምሮ ሙሊት የተሰራባቸው የአይምሮ ቁጥጥር ሰለቦች ዋናው ምልክት ነው፡፡ የዝነኞቹ ሚና የቁንጮዎቹ አጀንዳ ሳቢ፣ ማራኪ ወይም ጥሩ እንደሆነ አድርጎ ማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህን ስራቸውን ከስር እናየዋለን፡፡

 መደምደምያ

ሜትሮፖሊስ ያለ ጥርጥር ለቁንጮዎች የተሰራ የቁንጮዎች ፊልም ነው፡፡ አለምን እያስተዳደሯት ያሉ ሰዎችን ጭንቀት የሚዳስስ ሲሆን ያለው ሁኔታ (ስታተስኮው) ሳይቀየር የሚቀጥልበትን መፍትሄም ይለግሳቸዋል፡፡ በተጨማሪም ፊልሙ በሜሶኖች ምልክቶችና በጥንታዊ ሚስጥራት ምልክቶች የተሞላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ፊልሙ ከመጀመርያው ሚስጥራቸውን የሚያውቁ ሰዎችን ለማነጋገር የተሰራ ነው፡፡

ታድያ ለምንድን ነው ዘፋኞች ሁሉ የሚወዱት? በርግጥ ከትእይንቱ በስተጀርባ ያሉት ሰዎች፣ ዳይሬክተሮቹ፣ ገፅታ ፈጣሪዎቹ፣ የሙዚቃ ቢዝነስ ተቆጣጣሪዎቹ የሚወዱትን ያህል ላይወዱት ይችላሉ፡፡ እነሱ ናቸው ከዋክብቱ ምን መወከል እነዳለባቸውና ምን መምሰል እንዳለባቸው የሚወስኑላቸው፡፡ የዛሬው የብዙሃኑ ባህል ደሞ ቁንጮአዊ እና የኢሉሚናቲ ምልክቶች የነገሱበት እና ባህላዊ እሴቶች የሚበሻቀጡበት የባህል ዘመን ነው፡፡ ኮከቦቹ በተግባሮቻቸው የማሪያን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፣ ተመሳሳይ ውጠየትም እያስገኙ ናቸው፡፡ ሐቁ እንዲህ ካሆነ ለምንድን ነው እንደእሷ የሚለብሱት? አርቲስቶቹ ሁሌም ፍፁም ነፃነትንና ፈጠራን ተከትለው የሚሰሩ ከሆነ፣ ለምድን ነው በአይምሮ ቁጥጥር ስር እንዳለ ማሽን-ሰው ሚናን ተላብሰው መጫወት የሚወዱት? እውነቱ እራሳቸው እንደዚሁ ስለሆኑ ነው የሚለው ትክክለኛ መልሱ ይሆነዋል፡፡ በእርግጥ ሜትሮፖሊስ ታላቅ ፊልም ነው፡፡ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ እንድያውም ከተሰራ ከ 80 ዓመት በኋላ ይበልጥ እውነታዊ እየሆነ ነው፡፡ በቁንጮዎቹ መንገድ መሄድ ከቀጠልን ለወደፊቱ ደሞ ሙሉ ለሙሉ እውን ይሆናል፡፡