Archive for the ‘ሽብር’ Category

በግደይ ገብረኪዳን
 “በአንድ ግዜ የአሜሪካ ወዳጅና የሽብር ጠላት መሆን አይቻልም፡፡” ተክሉ አስኳሉ

ከስር ያለው የአንድ ደቂቃ ቪድዮ በመስከረም 11 ጥቃት አውሮፕላኖቹ አፈረሱት የተባለው ህንፃ ኮንክሪቶቹ ተገንድሰው መሬት እንደመውደቅ አየር ላይ እያሉ ወደ አመድ ይቀየራሉ፡፡ ህንፃ ሲፈራርስ ቢያንስ 12 መቶኛ አካሉ በፍርስራሽ መልክ ተከምሮ መገኘት ይኖርበታል፡ የዓለም ንግድ ማእከል ማማዎች እና ህንፃ 7 ሲፈርሱ ይህ ፍርስራሻቸው አልታየም፡፡ ምክንያቱም ገና መሬት ሳይነኩ አየር ላይ ወደ አመድ ተቀይረው በመብነናቸው ነው፤ ቪድዮውን ይመልከቱ፣ እባካችሁን የተደረመሱት ኮንክሪቶች መሬት ላይ እንደመውደቅ ወደአመድ ሲቀየሩ ይመልከቱ፡፡ ህንፃው አልፈረሰም ወደ አመድ ነው የተቀየረው፡
Advertisements

በግደይ ገብረኪዳን
 ይህ ፅሁፍ ካልታተመ መፅሃፍ ላይ የተወደ ሲሆን በዚህ ርእስ ለማቅረብ የፈለኩት እኔም ከሁለትዮሽ ወጉ ልቋደስ ብዬ ነው፡፡ እድሜ ለቻርለስ ዲከንስ የሁለት ከተሞች ወግ ተብሎ በተተረጎመለት ስራው ሃረጓን ካስተዋወቀን ወዲህ የአማርኛ አንባቢውም ፀሐፊውም በአባባሏ የተማለለ ይመስላል፡፡ ለኔ ይህች ፅሁፍ የሌላ ሰፊ እቅድ መጀመርያዬ ነች፣ እድሜ፣ ጤናና ብሎግስፖት አይንሳን እንጂ እስከዚያው ብሎግ እናረጋለን፡፡
በዚች አጭር ፅሁፍ እኚህ ሁለት ፅንፈኞች ከሚያለያያቸው አንድ የሚያደርጋቸው ግቦች እንዳላቸውና ከአንድ መአድ እንደሚቋደሱ እናያለን፡፡
ይህ የማይታመን ግን እውን የሆነ ጥምረት ነው፡፡ እስራኤል ለሃማስ ካደረገችለት ድጋፍ ተጠቃሹ፡ ፅንፈኝነቱ እየታወቀ ለሚያንቀሳቅሳቸው ምግብ ቤቶች፣ ክሊኒኮች፣ ት/ቤቶች፣ መዋእለ ህፃናት እውቅና በመስጠት የፋታህን አማራጭ አስተዳደር ስርአትን እንዲፎካከር ይደረግ ነበር፡፡ እነዚህ “የመንደር ሊጎች” – ‘Village Leagues’ በመባል ይታወቁ ነበር፣ የታወቁ የሃማስ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ አንቀሳቃሽ ሰዎች መሰረታቸውም ነበሩ፡፡ (more…)

በግደይ ገብረኪዳን

የሰሜን ኮርያ ገዥዎች ደጋግመው አለምን እንደሚያጠፉ በመዛት ይታወቃሉ፡፡ ሰሜን ኮርያ በጋርዮሻውያን ስርወ መንግስት የምትገዛ አገር ነች፡፡ ሰ.ኮርያ አንድ ሚሊዮን ሰራዊት፣ በሌሎች ግምት ደሞ 4 ሚሊዮን አላት የምትባል አገር ስትሆን፣ ገዢዎቿ ህዝቡን በማስራብና በሰፋፊ ማጎርያ ካምፖች በማከማቸት የስታሊን አርአያን የሚከተሉ ናቸው፡፡ የኢራቅ ገዢዎች ሰብአዊ መብት ጥሰትና ሌሎችም ጉዳዮች ተወንጅለው ሰራዊት ተዘምቶ ተወግደዋል፡፡ ከሰ.ኮርያ ጋር ሲነፃፀሩ ኢራቆቹ የመዋእለ ህፃናት ተማሪዎች ነው የሚሆኑት፡፡ ለሰ.ኮርያ ገዢዎች እንኳን ሊነኩ ቀርቶ በአሜሪካ የኒኩለር አቅማቸው እየተገነባላቸው ነው፡፡ በ1994 በክሊንተን አስተዳደር ስር በተደረገ ስምምነት አሜሪካ የሰ.ኮርያን የኒኩሌር ማብሰልሰያን ወደ ቀላል የውሃ ኒኩሌር ማብሰልሰያ ለመቀየር ተስማማታለች፡፡ መንግስት የከፈላቸው ሙያተኞች ይህ የውሃ ኒኩለር ማብሰልሰያ መሳርያ ለመስራት እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡ ይህ አባባል የኒኩለር መሳርያ ያለማልማት ስምምነት ፖሊሲ ትምህርት ማእከል በዋሽንግተን ሃላፊ የሆነው ሄነሪ ሶኮልስኪ አይስማማበትም፡፡ (more…)

ናዚዎችን ፋይናንስ ማድረግ እና ሁለተኛው የአለም ጦርነት
“ከስፓርታከስ ዉሻፕት [ኢሉሚናቲ መስራች] ግዜ እስከ ካርል ማርክስ፣ እስከ ሊዮን ትሮትስኪ፣ ቤላ ኩን፣ ሮዛ ሉግዘምበርግ፣ እና ኤማ ጎልድማን ድረስ …. ይህ አለም ዓቀፍ ሴራ ያለማቋረጥ እያደገ ነው…”
ዊንስተን ቸርችል በጥቅምት 8፣ 1920 Illustrated Sunday Herald ለተባለ ጋዜጣ ከፃፈው የተወሰደ፡፡
ይህን ክፍል ካልታተመው መፀሀፋችን ከገፅ 207 በወሰድነው ጥቅስ ብንጀምረው ነገሮችን ሁላ ያሳጥርልናል፡- “የሄግሊያዊ ዲያሌክቲክ ማርክሲስት አተረጓጎሙ ፋይናንሻል ካፒታሊዝምን እንደ ተሲስ ማርክሲስታዊ አብዮትን እንደ አንቲተሲስ አርጎ ያስቀምጣል፡፡ ግልፅ የሆነው እንቆቅልሽ በዚህ ማርክሲስታዊ አባባል በነዚህ ሁለት ተቃራኒዎች ግጭት ማለትም ፋይናንሻል ካፒታሊዝም እና አብዮታዊ ማርክሲዝም ግጭት ሳቢያ ይፈጠራል ተብሎ እሚታሰበው ሲንተሲስ ባህርያት ምንድን ነው ተብሎ ነው፡፡ (more…)

የቦልሸቪክ አብዮት
ራሽያና ነገስታቶቿ ሁሌም የኢሉሚናቲዎችን የበላይነት ህልምን እንዳከሸፉ ነው፡፡ እናም የገንዘብ ባላባቶቹ በራሽያ አብዮት እንዲነሳ ገንዘብ ከማፍሰስ ተቆጥበው አያውቁም፡፡ በአንደኛ አለም ጦርነት ተወጥራ እያለች ቦልሸቪኮችን፣እንደ አብዮተኛነት እንኳ ሰፊ ተቀባይነት ያልነበራቸውን ፅንፈኞችን-ይሄ በመጀመርያው የራሽያ “ዱማ” ምርጫ ባገኙት ድምፅ (ባላገኙት ቢባል ይሻላል) በግልፅ የታየ ነው፣ እነዚህን አናሳ ተደማጭነት የነበራቸውን ሲደጉሙ ነበር፡፡
በ1917 ተከታታይ አመፆች በውኋላ ዛር ኒኮላስ ከስልጣኑ እንዲወርድ ተደረገ፡፡ ስልጣኑንም ሊበራል ዲሞክራት የሆነው መስፍን ጆርጅ ልቮቭ ለጥቂት ግዜ ይዞ ለዲሞክራት ሶሻሊስት ለሆነው ኪረንስኪ አስረከበ፡፡ ኪረንስኪም ከጀርመን ጦርነቱን ሳያስቆም ለሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ምህረት ሰጠ፡፡ (more…)
13
የሽብርውሎው ትንተና
በዚህ ምእራፍ አሁን የአሜሪካን ፖለቲካ የተቆጣጠሩት ቁንጮ ጥቂቶች ይህን የሽብር ዘመቻቸውን የሚያካሂዱበት መንስኤ እምነታቸው ነው ብለን የተቀበልነውን ትንተና እንዳስሳለን፡፡ የመጀመርያ ክፍል ርእስ ገፅ ላይ የፃፍነው የአሌክሳደር ሶልዘንትሲን ጥቅስ ርእዮተ አለም ክፋት የሚፈልገውን ሰበብ እንደሚሰጥ አሳይቶና፡፡ አሁን አለምን በማሸበር ለመግዛት እየጣሩ ያሉት ምን አይነት ርእዮተ አለም እንደሚከተሉና ያመጣጥ ታሪኩን እናያለን፡፡

12
9/11፡የሽብራዊ አገዛዝ ውሎ
በመስከረም 11፣ 2001 አራት አውሮፕላኖች ውስብስብ በሆነ አኳኋን በተሳፋሪዎች፣ በማንሃታን ቀጠና እንዲሁም ፔንታጎን ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ ግዜውን፣ የጥቃት አላማውን እና ግጭቱን ተከትሎ ለህንፃው ውድመት የተሰጠው ማብራሪያ ያስከተለው የኢንጂነሪግ ህጎች ጥሰት ኦፊሻላዊው መግለጫ ጥያቄ ውስጥ አስገብተውታል፡፡ በዚህ ምእራፍም ጥቃቱ ዋሻ ፅፈት ቤታቸውን ያደረጉ ፅንፈኞች ሳይሆኑ ውስጥ አዋቂዎች ያቀነባበሩት ውስብስብ ዘመቻ መሆኑን እንፈትሻለን፡፡ (more…)