Archive for the ‘ሳይንሳዊ አምባገነንነትና ፍልስፍና’ Category


ግደይ ገብረኪዳን
ምንም እንኳ በአሁኑ ግዜ ስለ ቻይና ብዙ መልካም መገሮችን ብንሰማም፣ በአንድ ፓርቲ ጋርዮሻዊ አገዛዝ የምትተዳደር እንደመሆኗ ለማመን የሚከብዱ ክንውኖችም ይካሄዱባታል፡፡ በማኦ ዘመን የባህል አብዮት በታወጀበት ግዜ ከነበረው ጭቆና አሁን ቢሻልም አሁንም ቢሆን ቻይና ከባድ ሃገር ነች፡፡ የፓርቲው አባላት የግዴታ ኢ-አማንያን መሆን ይጠበቅባቸዋል፣ ተቃዋሚሆች ያለህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድባቸዋል፣ ቲቤት ፈተና ውስጥ ነች፣ ፓርቲው አስገዳጅ ፖሊሲዎችን ያወጣል ለምሳሌ አንድ ልጅ ብቻ የመውለድ ፖሊሲ የቻይና ወላጆችን እያሰቃየ ነው – በቻይና ወንድ መውለድ ስለሚፈለግ ተፈጥሯዊ ባልሆነ መልኩ የወንዶች ቁጥር ከሴቶች እንዲበልጥ አድርጓል፣ ሴት ስትፀነስ ውርጃ ይካሄዳል – ተወልደውም የሚገደሉ አሉ፡፡ መንግስት በቀጥታ ሚድያውን ሁሉ ይቆጣጠራል፣ መንግስትን የሚወቅሱ ፅሁፎች የማይታሰብ ነው፣ በኢንተርኔት የሚወጡትም ከሰው እንዳይደርሱ ይታገዳሉ፡፡

(more…)

Advertisements


በግደይ ገብኪዳን
ወደ 2000 ዓ.ም ገደማ ጋርዮሻዊቷ ቻይና በአሜሪካ ቴክኖሎጂ እና  ክህሎት የተገነባች “ልእለ ሃያል” ሃገር ትሆናለች፡ ፕሮፌሰር አንቶኒ ሱቶን፡ የአሜሪካ ሚስጥራዊ ተቋም፣ 1984
ወደ 50 ከሚጠጉት ግዙፍ የቻይና መንግስት ካምፓኒ መሪዎች ዴስክ ላይ ከኮምፒተሮቹ፣ ከቤተሰብ ፎቶዎቹ እና ሌላ ቅንጡ ዘመናዊ የዋና ሃላፊ ቢሮ ከሚያስፈልጋቸው ውድ እቃዎች ማሃከል አንዲት ቀይ ስልክ ትኖራለች፡፡ ልክ ስትጠራ ሊያነሷት ከተቀመጡበት የሚወነጨፉት የበላይ ሃላፊዎች “ቀይዋ ማሽን” ብለው ይጠሯታል፡፡ ስልክ ብቻ ማለት በትክክል አይገልፃትም፡፡ ይህች ስትጠራ ያላነሳ አለቃ ወዮለት!
(more…)


በግደይ ገብረኪዳን
 ከአለማችን ትልቋ “ዲሞክራሲ”፡ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ በየአራት አመቱ ለምታካሂደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንደተለመደው ለማስተናገድ ሽርጉዱን ተያይዛዋለች፡፡ ይህች በአለም ዙርያ የዲሞክራሲ ፖሊስ መሆን የሚቃጣት ሃገር ይህን አጋጣሚ ተጠቅመን ዲሞክራሲዋን እንገመግምላታለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡

(more…)

በግደይ ገብኪዳን
ብዙ ሰዎች በጋዝ ነዳጅነት ተጠቅመው መኪናቸውን ሲያሽከረክሩ በሃይድሮጅን እያሽከረከሩት እንዳለ ልብ አይሉትም፡፡ እኛ [በውሃ የምትሰራ መኪና የሰራነው] ደሞ እያደረግን ያለነው ሃይድሮጅኑን ከውሃ ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ የብሄራዊ ልኬት (ስታንዳርድ) ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ ውሃ ስትጠቀም የሚለቀቀው ሃይል ጋዝ ተጠቅሞ ከሚገኘው በማጠጋጋት ሁለት ከግማሽ በእጥፍ ይበልጣል፡፡ እናም ውሃ እጅግ ሃያል ነዳጅ ነው፡፡ ስታን መየር (እ.ኤ.አ. 1992)
እንዲህ የገዘፈ ትራጀዲ የሰው ልጅን አልገጠመውም፡፡ ይህ በሰው ልጅ ላይ የደረሰው ከፍተኛው በደል ነው፡፡ ይህ ውድቀት በአራተኛው ክፍለ ዘመን ላይ በአለክሳንደርያ ቤተ መፃህፍት በእሳት ቃጠሎ መውደሙ በሰዎች ስልጣኔን ወደኋላ በመጎተት ከደረሰው ኪሳራ የከፋ ነው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ግኝት ከቤንጃሚን ፍራንክሊን የኤሌክትሪሲቲ ግኝት የበለጠ፣ ከቶማስ ኤዲሰን አለማችንን ለመጨረሻ ግዜ የቀየረው የፐርል ጎዳና ኤሌትክ ማከፋፈያ ስርአት ምስረታ እጅግ የበለጠ ነው፡፡ ሁለተኛውን ኢንዱስትሪያዊ አብዮት በር የከፈተው የኒኮላ ቴስላ ኤሌትሪክ ሃይል በገመድ አርቆ እንዲጓዝ ያስቻለው የአልተርኔቲንግ ከረንት ግኝቱ በላይ የሆነ ፈጠራ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሌሎች ይፋ ያልሆኑ የኒኮላ ቴስላ ፈጠራዎች ይበልጣል ማለቴ አይደለም፡፡ (more…)
በግደይ ገብረኪዳን
(ካልታተመ መጽሐፍ የተቀነጨበ)
በ1980ዎቹ መጨረሻ ላይ የኦዞን ሽፋን የመሳሳት ፍጥነቱ በፊት ሳይንቲስቶችን ሲያስጨንቅ ከነበረው 5 መቶኛ ወደ 97 መቶኛ ከፍ አለ፡፡ የዚህን ምክንያት ማንም ሊያብራራው አልቻለም፡፡
ኒኮላ ቴስላ ቴክኖሎጂ
ቶማስ ኤዲሰን የተባለው መብራት ሰራ እየተባልን በየቀኑ እሚለፈፍብን ሰው አጋር የነበረና ስሙ የሚገባውን ያህል የማይነሳ ኒኮላ ቴስላ (Nikola Tesla)እሚባል ሳይንቲስት ነበር፡፡ ይህ የፈጠራ ሃብታም የሆነ ተመራማሪ ነበር፡፡ ይህ ሰው በሂወት ዘመኑ መጨረሻ አካባቢ የፈጠራ መብት ያወጣበት ስራ ነበረው፡፡ ቴስላ ያገኘው ምንድን ነው በምድር ውስጥ የማያባሩ/ቋሚ ሞገዶች ማስነሳት እንደሚቻል ነው፡፡ ይህ በአለቶቹ ያለው የማስተላለፍ እንቅስቃሴ ለሞገዶቹ ተጨማሪ እንቅስቃሴን ያስገኝላቸዋል በዚህም አንድ ሰው ካስጀመረው ሞገድ በላይ ጉልበት በሞገዶቹ ውስጥ ያገኛል፡፡ ይህን ጭብጡን የማጉያ ማስተላለፍያ –magnifying transmitter-አለው፡፡  በ1976 ሶቭየቶች ወደ አዮኖስፌር ሰባት የቴስላ የማጉያ ማስተላለፍያ አመጠቁ፣ እነዚህ 10ኸርዝ መጠን ያለው ጉልበት ወደ አዮኖስፌር በመልቀቅ ከቺሊ እስከ አላስካ ድረስ ቋሚ ሞገዶች እንዲፈጠሩ አድርገዋል፡፡ በዚሁኑ ግዜ ሶስት የሶቭየት ሳተላይቶች የላይኛውን ህዋ/ከባቢ አየር በዚህ ሞገድ መነካቱን ሲያስተባብሩ ነበር፡፡ እኝህ ሞገዶች በመላው አለም መለየት/መታየት ችለው ነበር፤ የራሽያ “ግንደ ቆርቁር” – “Russian Woodpecker”እሚል ስያሜም ወጥቶላቸው ነበር – በራድዮ ሞገድ ተቀባዮች ላይ በፈጠሩት ረብሻ ምክንያት፡፡ (more…)

በግደይ ገብረኪዳን
“ክፉ ነገር ለማድረግ መጀመርያ የሰው ልጅ እያደረገ ያለው ነገር ጥሩ ነው ብሎ ማመን ይኖርበታል፡፡… ርእዮተ አለም ክፋት ሁሌም የሚፈልገውን ማስተባበያ የሚያቀርብና ለክፋት ሰሪው የሚያስፈልገውን ያለመወላወልንና ቆራጥነትን ይሰጠዋል፡፡ ይህ ማህበራዊ ንድፈ ሃሳብ [ርእዮተ አለም] ነው ድርጊቶቹ በእርሱና በሌሎች አይን ከክፉ ይልቅ መልካም ሁነው እንዲታዩ የሚያደርገው፣ ስለዚህም ከወገዛ እና እርግማኖች ይልቅ ምስጋና እና ክብር ይቀበላል፡፡” ራሽያዊው የማህበረሰባውያኑ ቦልሸቪኮች ሰለባ የሆነው አሌክሳንደር ሶልሰንትሲን ጉላግ ደሴቶች በሚለው መፅሀፉ እንዳሰፈረው Alexander Solzhenitsyn, Gulag Archipelago
ይህ ፅሁፍ ካልታተመ መፅሐፍ ላይ ካበረከትኩት የተወሰደ ሲሆን ቀድመውት ባሉ ምእራፎች የመስከረም 11 የሽብር ጥቃት የአሜሪካ መንግስት ሆን ብሎ የፈፀመው ነው የሚሉ ማስረጃዎችን ተከትሎ የቀረበ ነው፡፡ በመሆኑም ለምን ይህን ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለውን ትንታኔ ለማቅረብ የተፃፈ ነው፡፡ አሁን አለምን በማሸበር ለመግዛት እየጣሩ ያሉት ምን አይነት ርእዮተ አለም እንደሚከተሉና ያመጣጥ ታሪኩን እናያለን፡፡ በየሰበቡ ብሔራዊ የሀገራት መሪዎችን በስውር እና በግልፅ እየገደሉ የአለምን ህዝብ የሚያሰቃዩበትን ሚስጥር ምላሽ ይሰጠናል፡፡ ይህ የነሱ እምነት ነው፣ ይህም ስህተት መሆኑን እንድናየው የተፃፈ ነው፡፡ ቁንጮዎቹ ለዓላማቸው እንጂ ለየትኛውም ህዝብ፣ መንግስት፣ ሃገር፣ አህጉር ወይም ሃይማኖት አይወግኑም፡፡

በግደይ ገብኪዳን
“አንዳንድ ሰዎች እኛ ለዩናይትድ ስቴትስ ከሚበጁ ተግባራት ተቃራኒ የምንፈፅም የሚስጥር ቡድን አባሎች ናቸው ብለው ያምናሉ፤ እኔና ቤተሰቤን “ዓለም-አቀፋውያን” እና ከሌሎች ጋር በዓለም ዙርያ የበለጠ የተዋሃደ ሉላዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስርአት -እንደውም ዓንድ አለም ለመገንባት የምናሴር አድርገው ይወነጅሉናል፡፡ ክሱ ይህ ከሆነ፣ ጥፋተኛ ነኝ፣ በዚህም ደሞ እኮራለው፡፡” (ዴቪድ ሮክፌለር፡ “Memoirs of David Rockefeller” ገፅ 405)
የላይኛው ጥቅስ ከበርቴው ስለ ዓለም አቀፋዊ ሴራው ሂወት ታሪኩን በፃፈበት መፅሃፉ ያሰፈረው ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ደረጃዎች ስንል የዓለም መንግስት ለመመስረት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ወይም ፖሊሲዎች ደረጃ በደረጃ በቅደም ተከተል እናያቸዋለን ማለት ነው፡፡ (more…)