Archive for the ‘መጣጥፍ’ Category

በግደይ ገብረኪዳን
በአሁኑ ወቅት በሃገራችን ስለ ኢሉሚናቲ ማውራት ከአመት በፊት ከነበረው ሁኔታ እንኳ በእጅጉ ተቀይሯል፡፡ አሁን ቢያንስ ስሙን እንኳ የሚያውቀው ሰው ቁጥር እጅግ በዝቷል፡፡ ሆኖም ግን አሁንም ስለ ኢሉሚናቲ ምንነት የጠራ ወይም በነባራዊው የዓለም ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ መድረክ ዙርያ ያለውን ወይም የሌለውን ሚና በቅጡ መረዳት ላይ አልተደረሰም፡፡ በዚህ ፅሁፍ በተለይ በሃገራችን ላይ አትኩሮት በማድረግ ትክክለኛ የምርምር መርህ ተጠቅመን ስውሮቹን እጆች ለመዳበስ እንሞክራለን፡፡ (more…)
Advertisements
በግደይ ገብረኪዳን

ፍዮዶር ሚካየሎቪች ዶስትየቭስኪ (Fyodor Mikhailovich Dostoyevsky) (11 ህዳር 1821  – 9 ጥቅምት 1881)
ውልደት፡ ሩስያ፣ የተለያዩ ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችና መጣጥፎች ፀሃፊ፡፡ 
የዶስትየቭስኪ ስነፅሁፋዊ ስራዎች በ19 ኛው ክ/ዘመን የነበረው የታወከው የራሽያ ህብረተሰብ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ እና መንፈሳዊ ሂወት በመተራስ ከውስጡ የሚገኘውን የሰው ልጅ ስነ ልቦናን የሚመረምሩ ናቸው፡፡ ፅሁፉን የጀመረው በ1850ዎቹ አጋማሽ ቢሆንም በስፋት የሚታወቁለት ምርጥ ስራዎቹ ግን ወደኋላ መጡት ናቸው፡፡ ወንጀልና ቅጣትተብሎ የተተረጎመለት (Crime and Punishment)፣ ደደቡ (The Idiot)እና እነ ካራማዞቭ (The Brothers Karamazov) ይገኙበታል፡፡ በአጠቃላይ ዶስትየቭስኪ 11 ረዣዥም ድርሰቶች፣ 3 መካከለኛ ድርሰቶች እና 3 ኢ–ልበ ወለዳዊ ስራዎች አሉት፡፡ በስነ ፅሁፍ ዓለም ውስጥ የሰው ልጅ ስነ ልቦናን አብጠርጥሮ በመተንተን የሚስተካከለው አይገኝም፡፡  (more…)
Giday Gebrekidan

አሁን ይህን በእግሊዘኛ ከዚህ በፊት ከፌስቡክ ወንድሞቼ ጋር በግሩፓችን (Illuminati conspiracy study group) የተወያየንበት ፅሁፍ ከሚጠፋ እዚህ ገልብጬ ያመጣሁት ሲሆን አሁን ግን በአማርኛ በጠራ መልኩ ሰፋ ብሎ እና ቀሎ ዳግም ስለተሰራ ፅሁፉን እዚህ መስመር ማግኘት ይቻላል፡ ኢሉሚናቲ በኢትዮጵያ፡ ተረት እና እውነት የሚለውን ያንብቡ፡፡
since we don’t have enough information concerning the possible connection between the illuminati and the violent revolutions in Ethiopia i like to present this dialogue i had on facebook with my facebook friends so it will be some use for some one instead of being lost just as facebook chat.
read it, it will make you think for sure…. in order to encourage you to read in the middle of your reading you will find this picture you always see on ETV so discover it’s mystry keep on reading…
good reading….

ይህን ፅሁፍ ከተክሉ ጋር አዘጋጅቼው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣ ቆይቷል፡፡ አሁን ማስታወስ የፈለኩት አለም ላይ ላለው የፋይናንስ ቀውስ ካፒታሊዝም ያመጣው ጣጣ ለሚመስላቸው ያላነበቡት ሰዎች እንዲያነቡት በማለት ነው፡፡ ታሪኩ እንዲህ በቀላሉ የስርአት ክስረት አይደለም ሶሻሊዝምማ በተግባር ተፈትኖ የከሰመ ነው፡፡ ካፒታሊዝም ላይ ግን የተከፈተውን ጦርነት ማንም አላወቀውም፡፡ እንግዲያውስ ያንብቡት፡፡
Like · ·

በግደይ ገብረኪዳን

ይህ ለማከብረው ጓደኛዬና የምርምር አጋሬ ተክሉ አስኳሉ ፌስ ቡክ ላይ ስለ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በፃፈው ፅሁፍ ላይ የሰጠሁት አስተያየት ሲሆን እራሱን የቻለ መጣጥፍም ሊሆን ይቸላል በማለት ልለጥፈው ወስኛለው፡፡
ተክሉ የተሰማኝን እንድነግርህ እንደምትፈልግ በመገንዘብ ስሜቴን ላጋራህ እሻለው፡፡ ስብሃት ክፉ ነገር ነው የሰበከው ላልከው አልቃወምህም፡፡ ሆኖም ግን በዚህ አስመሳይና አድር ባይ ህብረተሰብ ባጥለቀለቀው አገር ውስጥ አቋም ይዞ የተገኘ በመሆኑ እጅግ ሊደነቅ የሚገባው ሰው መሆኑ ግን ሊረሳ አይገባውም፡፡ በከንቱ አድናቂው ነን የሚሉት የሰዶም መልእክተኛ መሆኑን ቢያጤኑ ኖሮ ቀልባቸው እንደሚገፈፍ እርግጠኛ ነኝ፡፡ (more…)