የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ድብቁ ታሪክ

Posted: November 7, 2012 in ሳይንሳዊ አምባገነንነትና ፍልስፍና


በግደይ ገብኪዳን
ወደ 2000 ዓ.ም ገደማ ጋርዮሻዊቷ ቻይና በአሜሪካ ቴክኖሎጂ እና  ክህሎት የተገነባች “ልእለ ሃያል” ሃገር ትሆናለች፡ ፕሮፌሰር አንቶኒ ሱቶን፡ የአሜሪካ ሚስጥራዊ ተቋም፣ 1984
ወደ 50 ከሚጠጉት ግዙፍ የቻይና መንግስት ካምፓኒ መሪዎች ዴስክ ላይ ከኮምፒተሮቹ፣ ከቤተሰብ ፎቶዎቹ እና ሌላ ቅንጡ ዘመናዊ የዋና ሃላፊ ቢሮ ከሚያስፈልጋቸው ውድ እቃዎች ማሃከል አንዲት ቀይ ስልክ ትኖራለች፡፡ ልክ ስትጠራ ሊያነሷት ከተቀመጡበት የሚወነጨፉት የበላይ ሃላፊዎች “ቀይዋ ማሽን” ብለው ይጠሯታል፡፡ ስልክ ብቻ ማለት በትክክል አይገልፃትም፡፡ ይህች ስትጠራ ያላነሳ አለቃ ወዮለት!
ቀዩ ማሽን እንደማንኛውም ስልክ አይደለም፡፡ እያንዳንዷ ባለ አራት አሃዝ ቁጥር ባለቤት ናት፡፡ የምታገናኘውም በአንድ መስመር ላይ ላሉ በተመሳሳይ መልኩ የራሳቸው ባለ አራት አሃዝ ቁጥር ካላቸው ስልኮች ጋር ነው፡፡ የሆኑ ሁኖ የሚቀናባቸው ማሽኖች ናቸው፡፡ ሁሉ ዓይነት ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ ከጣታቸው ስር ለሆኑ አንድ ወይም አንዲት ሊቀ መንበር ይህን ስልክ አገኙ ማለት ከፓርቲው እና ከመንግስት ስልጣን ተዋረድ ውስጥ ከጫፍ ደረሱ ማለት ነው፡፡ የሚሰጡት በምክትል ሚኒስቴር መዓርግ በላይ ላሉ ሰዎች በፓርቲ እና በመንግስት ትእዛዝ ነውና ማሽኑ የመጨረሻው የፖለቲካዊ መደብ ማሳያ ነው፡፡
ስልኮቹ እንዲህ ጥብቅ ሚስጥራዊ በሆነ መስመር እንዲሆኑ የተደረገው የፓርቲ እና መንግስት መረጃ ልውውጥን ከውጭ ስለላ ድርጅቶች ለመጠበቅ ብቻ አይደለም፡፡ ከፓርቲው ውጭ ያለ የትኛውም ቻይናዊ ከማያገባው አፍንጫውን እንዳይከት ለመከላከልም ጭምር ነው፡፡ ቀይ ቀፎው ደረሰህ ማለት ሃሪቱን እያስተዳደራት ካለው ጥብቅ የሆነው ቡድን ውስጥ ደረስክ ማለት ነው፣ ይህ ቡድን ከ 300 ሰዎች አይበልጥም፣ በብዛት ወንዶች ሲሆን የኣለም አንድ አምስተኛን ህዝብ ያሥተዳድራሉ፡፡
ይሕ እንደ መግቢያ የተጠቀምኩበት የማይደበቀውና ዋል ስትሪት የዘገበው የቻይና ገፅታዋ ነው፡፡ አሁን የዓለም ቁንጮዎች አለሙን በጠቅላላ በዚህ ሞዴል ለመግዛት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሲጀመርም ቻይና እንዲህ እንድትገዛ የሆነችው በነሱ ድጋፍ ነው፡፡ ይህን ድብቅ ታሪክ ከስር እናየዋለን፡፡

ተማሪ ማኦ ዚዶንግ እና የል ዩኒቨርሲቲ በቻይና

በተባበሩት መንግስታት እና ቀድመውት በታወጁ ሰብአዊ መብት አዋጆች መሃከል ያለው ግዙፍ ልዩነት ስለ መብቶች ምንጭ ላይ ያላቸው አቋም ነው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካው የነፃነት አዋጁ ላይ የሰው ልጅ የማይገረሰሱ ከፈጣሪ የተሰጡት መብቶች ባለቤት መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ግን ይህን ባለማካተት መብት ከሰው ልጅ ለሰው ልጅ እንደተሰጡ አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህ ማለት እኚህ መብቶች በሰው ልጅ መገርሰስ ይችላሉ ማለት ነው፡፡
ይህ ጭብጥ ግራ ዘመም ወይም ሶሣሊስት እና ኮሚኒስት የሆኑ መንግስታት የሚያወጡት ህገ መንግስት የሚመሰረትበት መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
ስከልና ቦንስ የማይደርስበት ሃገር የለም፡፡ የስከልና ቦንስ አባል የሆነው ቡሽ ለቻይና የነበረው ጠንካራ ድጋፍ ከዚህ የሚመነጭ ነበር፡፡
ስከልና ቦንስ ማለት በአሜሪካ በኮኔክቲከት የሚገኘው የየል ዩኒቨርስቲ ውስጥ የሚገኝ የሚስጥር ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ እ.ኤ.አ. በ1832 ዓ.ም በጀነራ ዊልያም ራስል የተመሰረተ ሲሆን መስራቹ በኋላ ላይ በቻይና የኦፕየም (አደንዛዥ እፅ) ንግድን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ሲያተርፍበት የነበረ ሰው ነው፡፡ የል ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተው በኢላይ የል ሲሆን ይህም ሰው ሃብቱን ያካበተው በብሪቲሽ ኢስት ኢንድያ ካፓኒ ኦፕየም በኮንትሮባንድ በመሸጥ ነበር፡፡  
ስከልና ቦንስ ማህበር በኒው-ኢንግላንድ ከሰፈሩ ቁንጮ ቤተሰቦች መመልመያ መድረክ ሁኖ ነበር ሲያገለግል የነበረው፣ እኚህ አብዛኞቹ ቤተሰቦች ሃታቸውን ያካበቱት በአደዛዥ እፅ ንግድ ነው፡፡ እኚህ ልጆቻቸው ስከልና ቦንስን የተቀላቀሉ ቤተሰቦች ስም ከማይታወቁት እስከ ስመ ጥር የሆኑት፡ እንደነ ኮፊን፣ ስሎኤን፣ ታፍት፣ በንዲ፣ ፓይኔ፣ ዊትኒ ቤተሰቦች ይገኙበታል፡፡ እስከዚህኛው ዘመናዊው የመረጃ ዘመን ድረስ እኚህ ቤተሰቦች የዩናይትስ ስቴትስን “ምስራቃዊ ተቋም” የሚባለውን በቁጥጥራቸው ስር አድርገውት ይገኛል፡፡ ምስራቃዊ ተቋም የሚባለው በዩ.ኤስ.ኤ. ሰሜናዊ ምስራቅ ዳርቻ የሚገኙ ግዙፍ የፋይናንስ እና ዩኒቨርሲቲ ተቋማትን ነው፡፡ እኚህ ተቋማት በዩ.ኤስ.ኤ. ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሂወት መሪ ሚናን ይጫወታሉ፡፡ የቡሽ ቤተሰብ በነዚህ ቁጥጥር ስር ያለ ዝቅተኛ ደረጃ ቤተሰብ ነው፡፡
የስከልና ቦንስ አባል የሆነው ጆርጅ ቡሽ እ.ኤ.አ. በ1973 በቻይና ህዝባዊት ሪፐብሊክ ወይም ቻይና የአሜሪካ የመጀመርያው ዲፕሎማሲያዊ ወኪል ነበር፡፡ አባቱ፣ ወንድሙ፣ ልጁ፣ አጎቱ፣ የወንድሙ ልጅ እና የአጎቱ እና የአክስቱ ልጆች ወዘተ. የስከልና ቦንስ አባል ናቸው፡፡  በሬጋን-ቡሽ አስተዳደር ዘመን የቻይና አባሳደር የነበረው ዊንስተን ሎርድ የስከልና ቦንስ አባል ነው፣ ወንድሙም አባል ነው፡፡  ከ89 እስከ 91 አምባሳደር የመነረው ጄምስ ላይሌ ስከልና ቦንስ አባ ነበር፣ የዚህም አባቱ እና ብዙ ዘመዶቹ አባሎች ነበሩ፡፡ ኪሲንጀር ከማኦ ዚዶንግ ጋር ስምምነት ከፈረሙ ወዲህ ያሉት አምባሳደሮች በጠቅላላ ከካርተር አስተዳደር ዘመን ውጪ ሁሉም የስከልና ቦንስ አባል ናቸው፣ ስለ ቸባልነታቸው ቀጥተኛ መረጃ እንኳ ቢጠፋ የየል ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ናቸው፡፡

ዩኒየን ስነ መለኮት ጉባኤ

እ.ኤ.አ በ1903 የል የመለኮት ት/ቤት በመላው ቻይና “የል በቻይና” እየተባለ በሚታወቅ ዘመቻው ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን መገንባት ጀመረ፡፡ ከዛ ግዜ ጀምሮ “የል በቻይና” እንቅስቃሴ የሰና ያት ሰን ሪፐብሊካዊ ንቅናቄን ለማጨናገፍ የተሰራ ስራ መሆኑ የታወቀ ነበር፡፡ የአንግሎ-አሜሪካ ተቋም የሰን ያት ሰንን ጠላት ነበር፡፡ ምክንያቱም ቻይናን ማበልጸግ መፈለጉ ነበር፡፡ በሌላ በኩል የቻይና ኮሚውኒስቶችን ይወዷቸው ነበር፣ ምክንያቱም ኮሚውኒስቶቹ ቻይናን ኋላ ቀር አድርገው ያስቀሩላቸዋልና፡፡ አደንዛዥ እፅ በማምረትም የታወቁ ናቸው፡፡ “የል በቻይና” ካፈራቸው ታዋቂ ተማሪዎች አንዱ ማኦ ዚዶንግ ነው፡፡
በሁለተኛ የዓለም ጦርነት ግዜ “የል በቻይና” እንቅስቃሴ በአሜሪካና አዲሱ ደህንነት ተቋሟ ኦ.ኤስ.ኤስ (በኋላ ሲ.አይ.ኤ. የሆነው) በኩል ማኦውያኑ ወደ መንበረ ስልጣን እንዲመጡ የተጠቀሙበት ክንፋቸው ነበር፡፡ “የል በቻይና” ሲንቀሳቀስ የነበረው በደህንነት ተቋሙ በኦ.ኤስ.ኤስ. ቅጥረኛ ሩበን ሆልደን ነበር፣ ሩበን ሆልደን የቡሽ ዘመን ባለቤት ነው፣ በተጨማሪም የስከልና ቦንስ አባል ነው፡፡ ማኦውያኑ ቻይናን በወቅቱ በአለም ትልቋ የኦፕየም አምራች አድርገዋት ነበር፡፡  “የል በቻይና” በተጨማሪም ኒው ዮርክ መቀመጫው ካደረገው ዩኒየን ስነ መለኮት ጉባኤ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ነበረው፡፡ ይህ ጉባኤ አሜሪካ በቻይና ለምታደርገው ሰርጎ ገብ እንቅስቃሴ የምትጠቀምበት ነበር፣ ልክ እንደ ቃሉ ይህ ጉባኤ በውነቱም የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ነበር፡፡ አሁን በኮርያ የሚንቀሳቀስ እያንዳንዱ ፅንፈኛ በዚሁ ጉባኤ ዩኒየን ስነ መለኮት ጉባኤ የሰለጠነ ነው፡፡ ዩኒየን ስነ መለኮት ለሃያ ዓመታት በበላይነት ሲመራው የነበረው ደሞ ሄነሪ ስሎየን ኮፊን ሲሆን ይህ ሰው የሁለት ቁኝጮ ቤተሰቦች ዘር ግን ያለው፡ የስሎየን እና ኮፊን በደህንነቱ መስክ የገነኑት የተገኘ ነው፡፡ አው በተጨማሪም እራሱም የስከልና ቦንስ አባል ነው፣ ልክ እንደ ዘመዶቹ ሁላ ማለት ነው፡፡
አቨሬል ሃሪማንም መረሳት የለበትም፣ የቀድሞ የሞስኮ አምባሳደር፣ ሶቭየት ህብረትን ለመገንባት እጅግ ብዙ አስተዋፅኦ ያበረከተው የስከልና ቦንስ አባል ነበር፡፡ በተጨማሪም ሃሪማን ከፕሪስኮት ቡሽ ማለትም የቡሽ ትልቁ አባት ወይም የቡሽ ትንሹ አያት ጋር  የቢዝነስ ሸሪኮች ነበሩ፡፡ የአንቶኒ ሱቶን ምርጥ የምርምር ውጤት የሆኑ ስራዎች እንደሚያስረዱን ስከልና ቦንስ በቻይና ኮምኒስ እንቅስቃሴን ብቻ ሳይሆን ሲደጉም የነበረው ሶቭየት ህብረትንም ጭምር ነበር፡፡ ይህ የቀደመ የስልጣን አምልኮ ማህበር “ማህከለኛው ላይ ሁለት ጭፎችን የመጫን” ጨዋታን ሲጫወት የነበረ ነው፣ በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ አሜሪካን በአንድ ጫፍ (ተሲስ) ሩስያ በሌላ ጫፍ (አንቲ ተሲስ) እና ሌሎች ሃገሮችን እና እንቅስቃሴዎችን እርስ በርስ በማጋጨት የዓለም ህዝብን በውንብድ እና የተደናገረ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ ሲጫወትባቸው ኑሯል (አሁንም እንዲሁ ያደርጋል)፡፡  የዚህ መጨረሻ የዓለም ህዝብ ተስፋ በመቁረጥ አዲስ የዓለም ስርአትን (ሲንተሲስ) እንዲቀበል ማድረግ ነው፡፡   
የል እና የሮክፌለር ቤተሰቦችም በጥምረት በቻይና የኮሚኒስት አይዶሎጂን ሲያስፋፉ ነበር፡፡ የፓፓ ጎድፍረይ ወይም ጎድፍረይ ስቲልማ ሮከፌለር የስከልና ቦንስ አባል የሆነው የአጎቱ ልጅ የሆነችው ኢዛቤል በጆርጅ ቡሽ ወላጆች ሰርግ ሚዜ ነበረች ፡፡ አጎቱ ፐርሲ ሮክፌለር የሃሪማን ባንክን ከጆርጅ ቡሽ ቤተሰቦች ጋር ሁነው መስርተዋል፣ በተጨማሪም የናዚ ጀርመን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲደግፉ ነበር፡፡  

የሉ አካዳሚ

የሉ አካዳሚ በ976 ዓ.ም በሶንግ ስርወ መንግስት የተቋቋመ ት/ቤት ሲሆነ በ 1127 ዓ.ም በጦርነት ወድሞ መልሶ በ1165 ዓ.ም በደቡባዊው የሶንግ ስርወ መንግስት መልሶ የተገነባ ነው፡፡ ዝነኛው ዙ ዚ የተባለው ፈላስፋ በ1165 በአካዳሚው አስተምሯል፡፡ መልሶ በመንጎሎቹ ወረራ የወደመ ቢሆንም ቆይቶ በ15ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ በሚንግ ስርወ መንግስት ዳግም ተገንብቷል፡፡ በ1903 ሁናን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሆነ፡፡ አሁን ዘመናዊው የሁናን ዩኒቨርስቲ የዚህ ውጤት ነው፡፡ የትምህርት ቤቱ ንድፍ (አርክቴክቸር) በሶንግ ስርወመንግስት ንድፍ መሰረት በማለት በ1981-86 ድረስ ዳግም ግንባታ ተካሂዶለታል፡፡  
በ1903 በቻይና እና ጃፓን መሃከል በተደረገው የሻንጋይ ስምምነት ከተማይቱን ለውጭ ንግድ በሯን እንድትከፍት አድርጓታል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ፋብሪካዎች፣ አብያተ ክርስትያን፣ ት.ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ በየል ዩኒቨርሲቲ  ምሩቃን አንድ ኮሌጅ የተከፈተ ሲሆን በኋላ ላይ ዝያንያ ጤና ማእከል እና የሊ ት/ቤት ሁኗል፡፡  
የቻይና ህዝባዊት ሪፐብሊክ መስራች ማኦ ዚዶንግ ፖለቲካዊ ሂወቱን የጀመረው በቻንግሻ ነው፡፡ ከ1913 – 18 ድረስ በሁናን ቁጥር አንድ መምህራን ማሰልጠኛ ት/ቤት ተማሪ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ተመልሶ ከ1920 – 22 ድረስ መምህር እና ፕሪንሲፓል (ሃላፊ) በመሆን አገልግሏል፡፡ ት/ቤቱ በእርስ በርስ ጦርነቱ ግዜ የወደመ ቢሆንም መልሶ ተገንብቷል፡፡ የቀድሞ የሁናን ኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ቢሮ ማኦ ይኖርበት የነበረው በአሁኑ ሰዓት ሙዝየም ሁኖ ይገኛል፡፡

የል ካምፐስ በቻይና

የየል ካፐስ በቻይና መከፈት ረዥምና ከባድ ሂደት አልፎ እውን የተደረገ ነበር፣ ይህም የሆነው በህዝባዊ አመፅ እና በቻይናዎች የውጭ ተፅእኖ ላይ ያለው ከባድ ጥርጣሬ ሂደቱ እንዲቆራረጥ ያደርገው ስለነበር ነው፡፡ ሲበሪ እና ተርስቶን መስዋእትነቱን የከፈሉት ናቸው፡፡ ተርስቶን በ1903 ለፕሮግራሙ መሬት በማፈላለግ ላይ እያለ በሳምባ ምች ሞተ፣ ሲበሪ ደሞ ከአራት ዓመት በኋላ እየዋኘ እያለ በአደጋ ምክንያት ሰምጦ ሞተ፡፡
የየሊ አካዳሚ በኋላ ላይ የሊ መካከለኛ ት/ቤት የተባለው ለቻይናውያን ተማሪዎቹ በሩን የከፈተው በ1906 ዓ.ም ነበር፣ በጥንታዊቷ በግምበ በታጠረችው ቻንግሻ ከተማ፡፡ በት/ቤቱ ተማሪዎች ስለምእራቡ እና ስለ ቻይና ጉዳዮች እውቀት ይሸምቱ ነበር፡፡ ወድያውኑ የየል ዩኒቨርስቲ ምሩቃን፣ “ባችለሮች” እየተባሉ የሚታወቁ፣ ለአጭር ግዜ አስተማሪነት እየተመለመሉ ወዲህ መላክ ጀመሩ፡፡ በ1918 በኤድዋርድ ሃርክነስ (የሮክፌለር ሸሪክ) ለጋስነት ምክንያት ደረጃውን የጠበቀ ህክምና ኮሌጅ፣ ሆስፒታል እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሊገነቡ ችለዋል፡፡
ዘመነ አብርሆት
ከጅምሩ ጀምሮ በቻይና መንግስት፣ ተማሪዎቹ እና የየል ስታፎች መሃከል የነበረው ግንኙነት እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ነበር፡፡ ምንም እንኳን የል በቻይና ሃይማኖታዊ ስራውን ወድያው ቢቀንስም መጀመርያ በካምፓሱ የተዋቸው የሚሽነሪዎቹ ዓላማ እና አመለካከቶች አልጠፉም ነበር፣ ለአመታትም የውጥረት ምክንያት ነበሩ፡፡
ከጅምሮ ጀምሮ ቻይናዎቹ ትምህርትንና ክርስትናን ማስተሳሰሩን በቅርበት ነበር የሚከታተሉት፣ ሃኪም ወይም ነርስ መሆን ከፈለክ ለምን ክርስትና ማጥናት ያስፈልግሃል? ይሉ ነበር፡፡  በዓመፃው ግዜ በ1910 እና እንደገና በ1927 የሻንጋይ ሼክ ብሄራዊ ፓርቲ ስልጣን በሚይዝበት ግዜ ለውጭ ሰዎች እየጨመረ የመጣው ጥላቻ ያሌ አስተዳደር ውስጥ የነበሩ ሰዎች አገር ለቀው እንዲወጡ አስገድዷቸዋል፡፡   
ከመስራቾቹ መሃከል የሆነው ብሮኔል ጋጄ በፃፈው ደብዳቤ የሚከተለውን ብሎ ነበር፡ “በምስራቁ እና በምእራቡ መሃከል ያለውን መጨረሻ የሌለው ኩራት፣ አድልዎ እና አለመረዳዳት እንድናውቅ አድርጎናል፡፡” ብሎ ነበር፡፡
ፖለቲካዊ ውጥረት በሌለበት ግዜ እንኳ ተማሪዎቹ እና የቻንግሻ ነዋሪዎች የአሜሪካ የበላይነትን ይቃወሙ ነበር፡፡ የየል ዩኒቨርሲቲ ሰዎች የሚቆጣጠሩት የል በቻይና እንቅስቃሴ፣ የመማማር ፕሮግራም አልነበረም አሜሪካውያኑ ለቻይናውያን አብርሆትን ሊሰጡ ነበር የሄዱት፡፡
በ1950ዎቹም እንኳን ፕሮግራሙ ከ 20 ዓመት በኋላ ወደ ዝቅተኛ የአሜሪካ ተሳትፎ ከወረደም በኋላ ቢሆንም በፕሮግራሙ ቻይናውያንን ተጠቃሚ እያደረጉ እንዳለ አድርገው ነበር የሚያዩት፡፡
የየል ደይሊ ኒውስ በ1951 በየል በቻይና 50 ዓመት ክብረ በዓል ግዜ እንዲህ ሲል ዘግቦ ነበር፡ “[የል በቻይና] ለአዲሱ ትውልድ ያበረከተው የአብርሆት አስተዋፅኦ ላለፉት ትውልዶችም ያደረገውን አስተዋፅኦ ያህል የሚደርስ ነው…” ብሎ ነበር፡፡
በ1950 የኮርያ ጦርነት ከተከፈተ በኋላ እና ቻይና እና አሜሪካ ጠላቶች ከሆኑ በኋላ የል ያሉት ሰዎች ግን ተስፋ አልቆረጡም ነበር፡፡ ዘ ኒውስ በፌብርዋሪ 12፣ 1951 ላይ ከመጀመርያ መስራቾቹ አንዱ የሆነው አንሶን ስቶክስ የል በቻይና “በየል ክርስትያናዊ እምነት እና ርእዮት ላይ የተመሰረቱትን ተቋማት ለቻይና እንደሚያተርፍላት፡፡” ተስፋው እንደሆነ ተናግሮ ነበር፡፡  

እናት አገርን መልቀቅ

የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ስቃይና እጦት እና የማኦ ዚዶንግን የባህል አብዮት እና የቻይና ህዝባዊት ሪፐብሊክ ምስረታን ችለው ካለፉ በኋላ የል በቻይና እንቅስቃሴ ሲሰሩ የነበሩት አሜሪካውያን ሁላ በ1951 ካገር ተባረሩ፡፡
የስታፎቹ መባረርን ተከትሎ የየልበቻይና የነበረው ጣልቃ ገብነት ከ30 ዓመት ገደማ በኋላ አበቃለት፡፡ ሆኖም ግን በ1980 ቻይና መልሳ በሯን ከከፈተች በኋላ የል ወደ ቻንግሻ ተመለሰ፡፡

ቻይናን መገንባት

አሁን በኮምኒስታዊ አገዛዝ ስር ከገቡ በኋላ ለቁንጮዎች እቅድ እንቅፋት ስለማይሆኑ እድገት ይፈቀድላቸዋል፡፡

በቡሽ አስተዳደር ግዜ ለብሄራዊ ደህንነት አስፈላጊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ሲያሸጋግሩላት ነበሩ፡፡ ብቸኛ ጥቅሙ የኒኩሌር ጦር መሳርያ መስራት የሆነ የኮምፒውተር ፕሮግራም ቻይና ተሰጧታል፡፡ (‘High-Tech Transfers To China Continue’ – Zoli Simon – Insight Magazine – July 8 2002) ለቻይና የሚደረግላት ድጋፍ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ ከስር ካልታተመው የአሜሪካ የሚስጥር ተቋም የትርጉም መፅሃፋችን የወስደነውን እናንብ፡-
ልክ የቡሽ ቤተሰቦች በመጀመርያ አካባቢ ሶቭየት ህብረትን ሲገነቡ፣ ከዛም ናዚዎችን ፋይናንስ ሲያረጉ፣ በብዥታ ደሞ ከአንጎላ በስተጀርባ እንዳገኘናቸው፣ አሁን ደሞ ቡሽ የሚለው ስም አዲስ ዲያሌክቲክ ክንድ ሲገነባ እናገኘዋለን፡ ኮሚውኒስት ቻይናን፡፡
ሚር. ኒክሰን ጆርጅ በ1971 “ፖፒ” (“Poppy”)  ቡሽን (ከኦርደሩ 1948) በተ.መ.ድ. የዩ.ኤስ. አምባደር አርጎ ሾመ፣ ከዛ በፊት ምንም የዲፐሎማሲያዊ ስራ ልምድ ባይኖረውም’ኳ፡፡ እንደዋና የዩ.ኤስ መልእክተኛነቱ ቡሽ የቻይና ሪፐብሊክን (መጀመርያ ነፃ የተ.መ.ድ. አባል የነበረችውን) ከኮሚውኒስት ቻይና ጥቃት መከላከል ይጠበቅበት ነበር፡፡ መጠቀም የሚችለውን ሰፊ የአሜሪካን ጉልበት ይዞ ቡሽ በሚያሳዝን አኳኋን ወድቋል፡፡ ሪፓብሊኳ ተባራ ኮሚውኒስት ቻይና ቦታዋን ተረከበች፡፡ ከዚህ ግዙፍ ውድቀት በውኋላ ቡሽ የተባበሩት መንግስታትን ትቶ የሪፐብሊካን ብሄራዊ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆነ፡፡
ይህ የአሜሪካ እጅ በቻይና ያለውን ጠቅላላ ታሪክ እሚነገርበት ቦታ አይደለም፡፡ የተጀመረው ዎል ስትሪት በ1911 የሰን ያት ሰን (Sun Yat Sen) አብዮት ጣልቃ ሲገባ ነው – እስካሁን ህዝብ በሚያውቀው መልኩ ያልተመዘገበ ታሪክ፡፡
በ2ዓ.ጦ. ግዜ ዩ. ኤስ. የቻይና ኮሚውኒስቶች ወደስልጣን እንዲመጡ ረዳቻቸው፡፡ አንድ የቻይና ጥናት ላይ በሚያተኩር ቺን-ተንግ ሊያንግ (Chin-tung Liang) የተባለ ስለ ጀነራል ጆሴፍ ደብሊው. ስቲልዌል (General Joseph W. Stilwell) ከ1942-1944 የዩ.ኤስ. ተወካይ በቻይና ስለሆነው እንደፃፈው ከሆነ፡ “ኮሚውኒዝምን ከመታገል አኳያ ከታየ…(ስቲልዌል) ለቻይና ታላቅ ኢ-አገልግሎትን አድርጎላታል፡፡” ይላል፡፡ (Chin-Tun Liang, General Stilwell In Chino, 1942-1944: The Full Story. St. John’s University 1972, p. 12.)
ስቲልዌል ከጀነራል ጆርጅ ሲ. ማርሻል ከዋሽንግተን የተላከለትን ትእዛዝ ብቻ ነበር የሚያንፀባርቀው፡፡ አድማይራል ኩክ ለኮንግረስ እንደተናገረው ከሆነ፣ “…በ1946 ጀነራል ማርሻል በስውር መልኩ ቻይናዎችን ትጥቅ አልባ ለማድረግ የጥይት መጓጓዝን እንዲቆም አድርጓል፡፡” ብሏል (Ibid., p. 278.)
ወደ ጀነራል ማርሻል ስንደርስ ግን ማወቅ ያለብን በዩ.ኤስ. የሲቪል ባለ ስልጣኑ በወታደራዊ ጉዳይ የመጨረሻው ቃል ያለው መሆኑንና ይህ ደሞ ወደጦር ሹሙ (ሚ/ሩ) ሄነሪ ስቲምሰን (Henry L. Stimson) ይወስደናል-የማርሻል የበላይና የኦርደሩ አባል (ከኦርደሩ 1888)፡፡ በሚገርም መገጣጠም በ1911 በሰን ያት ሰን አብዮት ግዜ የጦር ሹም የነበረው እራሱ ስቲምሰን ነበር፡፡
ቻይናን የመካድ ታሪክና የኦርደሩ ሚና ሌላ ቅፅ መጠበቅ ሊኖርበት ነው፡፡ ለአሁን ግን የኮሚውኒስት ቻይናን እንደአዲስ የዲያሌክቲኩ ክንድ ለመገንባት የተወሰደውን ውሳኔ ብቻ ለማስመዝገብ እንፈልጋለን – በፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን የተወሰደ እርምጃና ወደትግበራ የተገባው በሄነሪ ኪሲንጀር (ቼዝ ማንሃተን ባንክ) እና ጆርጅ “ፖፒ” ቡሽ (ከኦርደሩ) ነው፡፡
ይህ ስራ ወደ ህትመት እየተሄደ እያለ (በ1984 መጀመርያ) ባችቴል ኮርፖሬሽን አዲስ ባችቴል ቻይና ኢንክ. (Bechtel China, Inc.) የተባለ ካምፓኒን መስርቷል -ልማትን፣ ኢንጂነሪንግንና ኮንስትራክሽን ኮትራቶችን ለቻይና መንግስት ሊይዝ፡፡ የባችቴል ቻይና ኢንክ. አዲሱ ፕሬዚደንት ሲድኒ ቢ. ፎርድ ነው፣ ቀድሞ የባችቴል ሲቪልና ሚነራል ኢንክ. ማርኬቲንግ ማናጀር የነበረ፡፡ አሁን ባችቴል እየሰራ የሚገኘው ለቻይና ብሄራዊ ከሰል ልማት ኮርፖሬሽንና ለቻይና ኦፍሾር ኦይል ኮርፖሬሽን ጥናትን ነው- ያው ሁለቱም የቻይና ኮሚውኒስት ድርጅቶች ናቸው፡፡
ይህ እንግዲ የሚመስለው ምንድን ነው ዲትሮይት ከነበረው አልበርት ካን ኢንክ. (Albert Kahn, Inc) የተጫወተውን ሚና ሊጫወት ነው ማለት ነው – አልበርት ካን በ1928 ለሶቭየት ህብረት የመጀመርያውን አምስት አመት እቅድ ቅድመ ጥናት ያካሄደው ድርጅት ነው፡፡
በ2000 ዓ.ም. ኮሚውኒስት ቻይና “ልእለ-ሃያል” ሃገር ትሆናለች ማለት ነው፣ በአሜሪካ ቴክኖሎጂና ሙያ ተገንብታ፡፡ [ይህን ሲፅፍ 1984 ላይ ሁኖ ነበር፣ በውነትም የኦርደሩን እንቅስቃሴ መተንበይ ችሏል፣ ዛሬ ቻይና ምን ላይ እንደምትገኝ እናውቃለንና፡፡] የኦርደሩ አላማ ነው ተብሎ አንደሚገመተው ይህን ሃይል ከሶቭየት ህብረት ጋር በግጭት መስመር ውስጥ እንደሚያስገባ ነው፡፡
ባችቴል ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም፡፡ የቀድሞ የሲ.አይ.ኤ. ዳይሬክተር ሪቻርድ ሄልምስ ለባችቴል ይሰራል፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበረው ጆርጅ ሹልትዝና (George Shultz) መከላከያ ሚኒስቴር የነበረው ካስፓር ዌንበርገርም (Caspar Weinberger) ቢሆኑ ለባችቴል እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ አንዱ ከዋሽንግተን ያለ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር የተያያዘ እቅድ አውጪ ከመስመር ወጥቶ ቢቃወም ይህ በቂ ሃይለኛ ተፅእኖ አድራጊ ጥምረት ይገጥመዋል፡፡
ሆኖም ግን አሁንም ቢሆን ኦርደሩ የተሳሳተ ስሌት አድርጓል፡፡ ለዚህ ዲያሌክቲክ ለውጥ የሞስኮ ምላሽ ምን ሊሆን ይችላል? ከተለመደው የራሽያ የጥርጣሬ በሽታ ውጪም ቢሆን እዚህ ላይ ትንሽ ጭንቀት ቢያሳዩ ይቅር ሊባሉ ይገባል፡፡ ማን ነው የቻይና ኮሚውኒስቶች ከ2000 በውኋላ ከሞስኮ ጋር ሰላም ፈጥረው ልእለ-ልእለ-ሃያል የሆነች ዩ.ኤስ.ን ለማስወገድ አይጣመሩም ያለው?
ምንጭ፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s