ሳይንሳዊ ፊውዳሊዝም፡ የአይረን ተራራ ሪፖርት (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

Posted: March 9, 2012 in ሳይንሳዊ አምባገነንነትና ፍልስፍና
23
ሳይንሳዊ ፊውዳሊዝም፡ የአይረን ተራራ ሪፖርት
እስከ አሁን ባነበብነው ዓለም በምን እንዳለፈችና በምን ላይ እንዳለች አጮልቀን ለመመልከት ሞክረናል፡፡ አንባቢውም ወዴት እየተሄደ እንዳለ ለመገመት አያዳግተውም፡፡ አሁን ወደ ፊት በመዞር እየመጣ ያለውን ሳይንሳዊው አምባገነንነት ስርአት እንመለከተዋለን፡፡
ጦርነት የሉላውያን ተመራጭ መሳርያቸው ነው፡፡ እስከአሁን ሉላውያን ጦርነቶችን ቀርፀው ሲተገብሩ አይተናል፡፡ ይህም የተፈጥሮ የግብረገብ (ሞራል) ስርአትን በራሳቸው ጦርነትን የሚያጠፋ ነው በሚሉት አዲስ የአለም ስርአት ለመተካት በመሳርያነት ለመጠቀም ነው፡፡ ይህ የገበያ ስርአት የሚቆጣጠረው የከበሩ መአድናት (ማለትም ወርቅ፣ ብር ወዘተ.) ወይም ሌላ የመገበያያ መንገዶችን ምንም ዋስትና በሌለው በወረቀት ገንዘብ አታሚ ማእከላዊ ባንኮች በመቀየር ጡንቻቸውን አፈርጥመው እቅዳቸውን በማሳካት ላይ ይገኛሉ፡፡ ካላቸው ንቀት የተነሳም እቅዳቸውን ባደባባይ ለህዝብ ውይይት እንዲቀርብ እያደረጉት ነው፡፡
በ1961 የኬነዲ አስተዳደር ሚስጥራዊ ጥናት እንዲደረግ ትእዛዝ ይሰጣል፣ ጥናቱ ዓለም ወደ ሰላም የሰፈነበት ዘመን ብትገባ ዩናይትድ ስቴትስ ሊገጥማት የሚችለውን መመርመር ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር አሜሪካን እንዴት ወደ አዲስ የዓለም ስርአት እናስገባ የሚል ማለት ነው፡፡ በ1963 የጥናት ቡድኑ አባል የሚሆኑ ሙያተኞች ምርጫ ያለቀበት ግዜ ነው፡፡ ቡድኑ 15 ከየዘርፋቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ሙያተኞችን የያዘ ነበር፡፡ የመጀመርያውና የመጨረሻው ስብሰባቸው አይረን ተራራ ከሚባል የኒኩሌር ጥቃት ማምለጫ የምድር ስር ተቋም ውስጥ ነበር፡፡ ይህ በከፍተኛ ሚስጥር የተጠራው ቡድን መሰባሰብ በተጀመረበት በ1961 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ቢሮ ህትመት (#7277)– “ከጦርነት መላቀቅ፣ የዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይና ሙሉ ትጥቅ መፍታት በሰላማዊ ዓለም” /”Freedom From War, The United States Program for a General and Complete Disarmament in a Peaceful World”/የተሰኘ በሚወጣበት ግዜ ነው፡፡ ይህ ሰነድ የአሜሪካ መንግስት ትጥቅ የሚፈታበትንና አንድ ወታደራዊ ተቋም በተባበሩት መንግስታት ስር የሚደረግበትን ባለ ሶስት ደረጃ ፕሮግራም የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህ “ወታደራዊ ተቋም” በዓለም አቀፍ ደረጃ “በሰላም አስከባሪነት” የሚሰራ ይሆናል፡፡ እቅዱ “ለተ.መ.ድ. ከሚያስፈልገው ውጪ… ሁሉም አውዳሚ የጦር መሳርያዎች” እሚወገዱበትን ሁኔታ ያካትታል፡፡(ገፅ 12) “ሰላሙን ለማስጠበቅ ሁሉም ሃገራት በተመድ መመርያ መሰረት ማንኛውንም የጦር ሃይል እንደማይጠቀሙ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡” (ገፅ 16) የተመድን መመርያ ለመደገፍ ተራው ዜጋ ትጥቅ መፍታት ይኖርበታል፡፡ ይህ ዛሬ ላይ በስፋት የምንመከተው ነው፡፡ ከዚህ በኋላ በስልሳዎቹ አጋማሽ በኮሌጅ ወጣቶች የሚመራው የፀረ-ወታደራዊ እንቅስቃሴ የመጀመሩን መገጣጠምም ልብ ልንል ይገባል፡፡ በህዳር 13፣ 1963 ፕሬዚደንት ኬነዲ በኮሎምበስ ዩኒቨርሲቲ የአሜሪካን ነፃነት ለማጥፋት የአሜሪካ ፕሬዚደንት ኦፊስ ውስጥ የክህደት አድማ እየተሰራ እንዳለና ኦፊስ ከመልቀቁ በፊት አሜሪካውያን የገቡበትን መአት እንደሚያሳውቅ ተናግሮ ነበር ከአስር ቀን በኋላ ተገደለ፡፡ ይህ መገጣጠምም ልብ ሊባል ይገባል፡፡
ከሁለትአመትተኩልምርምርበኋላበ1966 ቡድኑግኝቱንለመንግስትአቀረበ፣የአይረንተራራሪፖርትየሰላምእውንመሆንናተፈላጊነትጉዳይላይ”Report from Iron Mountain on the Possibility and Desirability of Peace”-በሚልርእስ፡፡ ጥናቱ በደረሰበት ድምዳሜዎች ሳብያ ለህዝብ ይፋ እንዳይሆን ከኬነዲ ሞት በኋላ የተኩት ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን አዘዙ፡፡ የዚህ ሪፖርት አላማ አሜሪካን ወደ አዲስ የአለም ስርአት ለማምጣት የሚያስፈልገውን ነገር ማየት ነበር፡፡ የሪፖርቱ ፀሃፊዎች መሸኛ ደብዳቤው ላይ እንዳስቀመጡት፡-
“የዚህ ቡድን አመሰራረትን በተመለከተ ባለው ያልተለመደ ሂደት ምክንያትና በግኝቶች ባህርያት ሳቢያ ይህ ሪፖርት እንዲታተም አንደግፍም፡፡…በህዝብ ዘንድ የደረስንበት ድምዳሜና የሰጠነው አስተያየት ለውይይት ማቅረቡ ካለው እርግጠኛ ያልሆነው ጥቅም፣ በአመለካከታችን፣ ግዜውን ያልጠበቀ የሪፖርቱ መታተም እርግጥ የሆነው እና መገመት እሚቻል በህዝብ ዘንድ የእምነት መውረድ/ቀውስ አደጋ የማስከተሉ ጉዳይ ሚዛን ደፍቶ አግኝተነዋል፡፡
በከፍተኛ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ሃላፊነት ውስጥ ላለው አጣዳፊ ግዴታዎች ላልተጋለጠው ተራው አንባቢ፣ የዚህን ፕሮጀክት አላማ እና የተሳታፊዎቹን ሃሳብ በተሳሳተ መልኩ እንደሚረዳው ግልፅ ነው፡፡ የዚህ ሪፖርት ይዞታን እንዲያውቁ ሃላፊነታቸው እሚያስገድዳቸው ሰዎች መሃከል ብቻ ይህ ሪፖርት እንዲዛወር አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡” [ጉላት በፀሃፊዎቹ]
የሙያተኞቹ ቡድን አባል የነበረ አንዱ ሪፖርቱን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ወሰነ፡፡ ሙያተኞቹ እንዳሉት ሳይሆን “ወርቃማ የሰላም ዘመን” እሚመጣ ከሆነ ሌሎች መቅረት ያለባቸው ነገሮች ይቀሩ ዘንድ የአሜሪካ ህዝብ በራሱ መወሰን ይችላል ብሎ ስላመነ ነበር ሪፖርቱን የለቀቀው፡፡ እራሱን ሳያሳውቅ በሌላ መጠርያ ጆን ዶ በማለት ነበር ያወጣው፡፡ በማሳተም የረዳው ጓደኛው ብቻ ነበር ማንነቱን ያልደበቀው፡፡ ጆን ዶ መረጃውን ከለቀቀው በኋላ የመንግስት ሃላፊዎች የሃሰት ነው በማለት አጣጣሉት፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው አላማው ከመሸኛ ደብዳቤው ላይ እንደሚከተለው ነው፡-
“እዚህ የተያያዘው የልዩ የጥናት ቡድን ሪፖርት ነው በነሃሴ፣ 1963 የመሰረቱት፤ 1) ወደ አጠቃላይ ሰላም በሚደረገው ሽግግር ግዜ ሊገጥሙ ስለሚችሉ ችግሮች እንድናስብበት እና 2) ከዚህ ሁኔታ ውስጥ ብንገባ መከተል ያለብንን አካሄድ እንድንጠቁም በጠየቁን መሰረት፡፡” ይላል፡፡
በዚህ ምእራፍ የሪፖርቱን መልእክት ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ ሪፖርቱ ባጠቃላይ “የጦርነትን ሚና” እና እኚህ ሚናዎቹን በምን አይነት አማራጭ መተካት እንደሚቻል የሚያትት ነው፡፡ ይህም ሰላም እንዲወርድና የሰው ዘር በሰላም ምክንያት እንዳይጠፋ በሚል ነው፡፡ ከሁለትአመትተኩልምርምርበኋላበ1966ቡድኑግኝቱንለመንግስትአቀረበ፡፡ ያሳተመው ሊዮናርድ ሌዊን (Leonard Lewin)ከብዙ ውዝግብ በኋላበ1967 ያለውን በማጠፍ በ1972 እራሴው ነኝ የፃፍኩት አለ፡፡ ታዋቂው ኢኮኖሚስት ፕሮፌሰር ጆን ኬኔዝ ጋልብረይዝ (John Kenneth Galbraith) የቡድኑ አባል ባይሆንም በተለያዩ ግዚያት ለምክር እንደተጠየቀ በህዳር 26፣ 1967 ዋሽንግተን ፖስት ላይ ፃፈ፡፡ በመጨመርም ከሪፖርቱ ድምዳሜዎች እንደሚስማማና ለህዝብ መለቀቁን እንደሚቃወምም ገልፅዋል፡፡ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ከለንደን ለተላከ የአሶሽኤትድ ፕሬስ እንደቀልድ አድርጎ “የሴራው አባል” መሆኑን አጫወተው፡፡ በነጋታው እንዲህ እንዳልወጣውና የታይም መፅሄት ከቻርለስ ሁለተኛ ዘመን ወዲህ ለመጀመርያ ግዜ የተሳሳተ መረጃ እንደሰጠ ተናግሮ ያለ ጥርጥር የሪፖርቱ ፀሃፊዎች ዲን ረስክ(Dean Rusk)ወይም ክሌር ቡዝ(Mrs. Clare Booth Luce)እንደሆኑ ተናግሯል፡፡(G.E. Griffin, The Creature from Jekyll Island)ይኸው ያጣቀስነውየግሪፍንመፅሐፍእንደሚለው ሪፖርቱ የተፃፈውየተለያዩፍንጮችንበማገናዘብየመከላከያሚኒስትር(Department of Defense)በሚኒስትሩ(Defense Secretary)ሮበርትማክናማራ(Robert S. McNamara)ስርኮንትራትተሰቷቸውየሰሩትመሆኑአያጠያይቅምይላል፡፡የተሰጣቸውኸርማንካን(Herman Kahn) የመሰረተውናየሚመራውአይረንተራራአካባቢኒውዩርክየሚገኘውየሃድሰንኢንስትዩት(Hudson Institute) ነው፡፡  ሁለቱም ካን እና ማክናማራ የውጭ ግንኙነት መማክርት (ሲ.ኤፍ.አር.) አባሎች ናቸው፡፡
ማንም ቢፅፈው፣ የተጭበረበረ ቢሆን፣ ባይሆን በውስጡ የሰፈሩት አንድ በአንድ እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ሪፖርቱ ሰላም በነገሰበት አለም ውስጥ (ወይም ያለ ጦርነትና የጦር ዘርፍ) ማህበራዊ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ ህዝብን ማስተዳደር ይቻላል ወይ?የሚለውን ጥያቄ የሚመረምር ነው፡፡ ሰላም ለሚለው ቃልም እስከወቅቱ ይደረግ ከነበረው የሰላም ምርምሮች የተለየ ትርጓሜ ይሰጠዋል፡-
“ሰላም እሚለው ቃል በሚከተሉት ገፆች ላይ እንደተጠቀምንበት እሚገልፀው፣ ጦርነት እየተባለ እሚታወቀው በሃገር ደረጃ እሚደረግ እንቅስቃሴ ወይም ይህን የማድረግ ሃሳብ የሆነው የተደራጀ ማህበራዊ አመፅ ወይም የዚህ ስጋት የሌለበት ቋሚ ወይም ከፊል-ቋሚ የሆነ ሁኔታን ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉና አጠቃላይ ትጥቅ መፍታትን የሚያመለክት ነው፡፡ “ቀዝቃዛ ጦርነት” ወይም “የታጠቀ ሰላም”–“armed peace”–ወይምሌሎችን ረዥም ወይም አጭር ከጦርነት እሚገኝ እረፍት ለመግለፅ አይደለም፡፡ አለምአቀፋዊ ልዩነቶችን በፖለቲካዊ መንገድ ለሚያገኙት መፍትሄንም ለመግለፅ ተብሎ አይደለም፡፡”
አጠቃላይ ትጥቅ መፍታትን ያሟላ ሁኔታን እንጂ ውጊያ የሌለበትን ማህበረሰብ ለማለት ፈልገው አይደለም፡፡ አሁን በጦርነት እያመሷት ያለችው አለም እነሱ በሚፈጥሩት ሰላም የነገሰበት አዲስ የአለም ስርአት ስለምትተካ ይህን ዓይነት ማህበረሰብ እንዴት በቁጥጥር ስር እንደሚያደርጉት በእርግጥም ያሳስባቸዋል፡፡ ጦርነትንም ቢሆን የተለመደው የሃገሮች ሽኩቻ አድርገው አይደለም የሚመለከቱት ይልቁኑስ አሁን ያለው የሉአላዊ ሃገሮች ስርአት/ተፈጥሮ አካል አድርገው ነው፡-
“ጦርነት በስፋት እንደሚታሰበው ሃገሮች ፖለቲካዊ እሴቶቻቸውን ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥቅማቸውን ለመከላከል ወይም ለማስፋፋት የሚጠቀሙበት የፖሊሲያቸው መሳርያ አይደለም፡፡ በአንፃሩ  እራሱ [ጦርነት] ሁሉም ዘመናዊ ማሕበረሰቦች የታነፁበት አደረጃጀት መሰረት ነው፡፡” [ጉላት በፀሃፊዎቹ]
ስለዚህ ጦርነት ፖሊሲ ማስፈፀምያ መሳርያ ሳይሆን እራሱን የቻለ ለማህበረሰቡ አስፈላጊ የሆነ የህልውና መሰረት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ጦርነት ከተለመደው ሉአላዊነት ማስጠበቅ አገልግሎቱ ውጪ ብዙ ማህበረሰባዊ ፋይዳዎች ይኖሩታል፣ ጦርነት ከተወገደ እኚህ ማህበረሰባዊ ፋይዳዎቹ የግድ በሌላ አማራጭ መተካት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ማህበራዊ ሚናውን/ፋይዳውን መተካት ካልተቻለ ሃገር ወይም መንግስት ወይም የበላይ ተቆጣጣሪ መኖር አይችልም፡፡ ስለዚህም ሪፖርቱ መንግስት ቁጥጥሩን መቀጠል ከፈለገ የጦርነትን ማህበራዊ ፋይዳ በሌላ አማራጭ መንገድ/መንገዶች መተካት ይኖርበታል፡፡ ይህን የሪፖርቱን የጦርነት ሚና ወይም ጥቅም እና ጦርነት ባይኖር ተቆጣጣሪነትን/ የበላይነትን ላለማጣት ይህን ጥቅሙን በምን ማካካስ ይቻላል የሚለውን ምርምር ከሪፖርቱ ቀንጭበን እንመለከታለን፡፡
የአይረን ተራራ ሪፖርት
በሪፖርቱ መግቢያ ላይ የዓለም ሰላም ቢመጣ ብዙ ማሕበረሰባዊ ለውጦች እንደሚከተሉ ይገልፃል፡፡ ለንፅፅር/ለማስተያየት እንኳ እሚሆን እስከ አሁን ድረስ እንዲህ የገጠመበት ግዜ የለም፡፡ ሰላም ቢወርድ እራሱን የቻለ መዘዝ ይኖረዋል፡፡ ኢኮኖሚው ብቻ ሳይሆን ሁሉም የሂወት መስመር ይነካል፡፡ ፖለቲካዊ፣ ስነ-ማሕበረሰባዊ(sociological)፣ባሕላዊና ስነ-ምህዳራዊ(ecological) ተፅእኖዎች ይኖሩታል፡፡ እነዚህ ዘርፎችን የነኩበት ምክንያት ሪፖርቱ በሚፃፍበት ግዜ በእነዚህ ዘርፎች ላይ ሰላም የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለማስተናገድ ዓለም ዝግጁ አይደለችም ከሚለው ነጥባቸው ነው፡፡ ገና ከጅምሩ አካሄዳቸው ዓላማ-ተኮር(objective) እንደሆነ ያሳውቃሉ፡- በሙሉ አቅማቸው “መልካም” እና “ክፉ” ከሚባሉ የሕብረተሰቡ መመዘኛዎች እራሳቸውን ነፃ አድርገው ነበር የሰሩት፡-
“አስቀድመን የቀረፅናቸው እሴታዊ (ግብረገባዊ) መመዘኛዎችን ለማስወገድ አስቀድመን ተስማምተንበታል ይህ ደሞ እንዲያውም ይባሱኑ እራስን የማታለል አካሄድን ሊያስከትል ይችላል፡፡ እንደ ግለሰቦች ከየትኛውም አይነት አድልዎ የፀዳን ነን ማለት አንችልም፣ ሆኖም ግን የሰላም ችግሮችን ስናጤን ያለማቋረጥ የሰላም መስፈን “ጥሩ” ነው ወይስ “መጥፎ” እሚለውን ከመገምገም ተቆጥበናል፡፡ ይህ ቀላል ነገር አልነበረም ግድ ግዴታ ነበር፣ እስከምናውቀው ድረስ ከአሁን በፊት እንደዚህ አልተደረገም፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች ሰላምን፣ የሰውልጅ ህይወት የበላይነትን፣ የዲሞክራሲያዊ ተቋማት የበላይነትን፣ ለብዙሃኑ ብዙ “ጥሩ ነገር”ን፣ የግለሰቡ ክቡርነትን፣ የጤና ሰፊ ተደራሽነትና እድሜ ጣርያ ማራዘምን፣ እና ሌሎችም በእምነት እምንቀበላቸውን እሴቶችን (axiomatic values) እንደ ጥሩ /ተፈላጊ/ አድርገው ነው የሚወስዱት፡፡ እኛ ግን እንዲህ ሁኖ አላገኘነውም፡፡ እኛ በአስተሳሰባችን የቁሳዊ ሳይንስ መመዘኛዎችን ለመጠቀም ሞክረናል፣ የዚህም ቀዳሚ ባህርያቱ ደግሞ በአብዛሃው ዘንድ እንደሚታመነው ቁጥር ሳይሆን በዋይትሄድ [አሜሪካዊ ገጣሚ] ቃላት ለመጠቀም፡- “…የእሴቶችን መመዘኛ ከቁጥር አያስገባም፣ ለምሳሌ፣ ሁሉንም አይነት ስነውበት(aesthetic) እና ግብረገብ (ሞራል) መመዘኛዎችን፡፡” የሆነ ሁኖ የትኛውም አይነት ቁምነገር ያዘለ ምርምር የፈለገውን “ንፁህ” ቢሆን የሆነ የተለምዶ ቢሆንም መመዘኛ ያስፈልገዋል፡፡ በዚህ በኛ ጥያቄ (ኬዝ) የተያዘው መመዘኛ፡- አጠቃላይ የሰውልጆች ማህበረሰብ በሂወት የመኖር (survival) ፍላጎት እሚለው እሴት ነው፣ በተለይም ደሞ የአሜሪካ ማህበረሰብና ከዚህ በሂወት መቆየትጋ አብሮ እሚሄደው፡- የዚህ ማህበረሰብ መረጋጋት (stability) እሚሉት ናቸው፡፡”
ከፊት ገፆች ስለ ሰብአዊነት የሚዳስሰውን ምእራፎች ያነበበ ፍልስፍናቸው እንዴት እንደሚገናኝ ማነፃፀር ይችላል፡፡ ስለ ነፃነትና መብት፣ የሰው ልጅ ሂወት ክቡርነት ከግምት አይስገቡም፡፡ የተሰጣቸውን ስራ ወስደው እየሰሩ እያለ የሚሰራላቸው ሰዎችን ግን ዘንግተዋል፡፡ ሰዋችን ከከብት መንጋ ተርታ ነው ያሰለፉት፡፡ በሪፖርቱ አራተኛ ክፍል ላይ ስለ ጦርነትና ሰላም ማሕበራዊ ስርአትነት ይዳስሳል፡፡ ጦርነቶች በጥቅም ግጭት ምክንያት ብቻ አይደለም የሚከሰቱት ይላል፡፡ ይህን የመሳሰሉና ሌሎች ነጥቦችን የጦርነትን ሚና በሚዳስሱበት ግዜ በስፋት ተመልክተውታል፡፡ በዚህም መሰረት ጦርነት በሌለበት ሁኔታ አስተዋፅኦዎች ተቆንፅለው እንዳይቀሩ ምትክ ሊሆኑ የሚችሉትን ይጠቁማሉ፡፡
የጦርነት ሚና / የጦርነት ሚናን ሊተኩ የሚችሉ አማራጮች
የጦርነት ሚናን መተክያ በዝርዝር ያስረዳሉ፡፡ እኚህ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ-ማሕበረሰባዊ (sociological) እና፣ ስነ-ምሕዳራዊ (ecological) እና ባሕላዊና ሳይንሳዊ በሚል በዝርዝር ተመልክተውታል፡፡ እኚህ መስኮች በጠቅላላ ከጦርነት ጋር የተቆራኙና ልዩ አስተዋፅኦ የሚያደርግላቸው ናቸው፡፡ ጦርነት ከጠፋ ይህን ሚናውን የሚተካ አማራጭ መገኘት አለበት፡፡
ኢኮኖሚያዊ
አንዱ የጦርነት ሚና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ ነው፡፡ ሌላው ዋነኛ ተግባሩ ማባከን መቻሉ ነው፡፡ ይህ ብክነት ትርፍ ምርትን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡ የስራ እድልና ኢንዱስትሪያዊ እድገትም ይፈጥራል፡፡ ጦርነት ኢኮኖሚውን ያነቃቃል፡፡ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ሚዛን መጠበቅያ ነው፡፡ ጦርነት ይላል ሪፖርቱ ለኢኮኖሚው በጣም ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ ቀጣይነቱ መቋረጥ የለበትም፡-
“ጦርነት ለጥንታዊውም ሆነ ለዘመናዊው ስልጣኔ ሃገራዊ ኢኮኖሚን ለማረጋጋትና ለመቆጣጠር አስተማማኝ ዘዴ ሁኗቸዋል፡፡ እስከአሁን ምትክ የሚሆን አስተማማኝ ዘዴ አልተገኘም፡፡”
ይህን ሚናውን ለመተካት አማራጮችን ያስቀምጣሉ፡፡ ሁለት መመዘኛዎችን የግድ ማሟላት ይኖርበታል፡- አንድ አባካኝ መሆን ሁለት ከተለመደው የፍላጎትና አቅርቦት መስመር ውጪ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለዚህም “የሰላም መዓት” ቢወርድ እኚህ ተመራማሪዎች መንግስት ቁጥጥሩን እና ህልውናውን ለማስጠበቅ ማድረግ ያለበትን ምክር ይለግሳሉ፡፡ ለምሳሌ እጅግ ውድ የሆኑ (ብዙ ወጪ የሚጠይቁ) ተቋማትን በመመስረት የጦርነት ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦን ለመተካት ይቻላል፡-
“(ሀ) የሰው ሂወትን አጠቃላይ ሁኔታ እጅግ የሚያሻሽል፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ማህበራዊ ፕሮግራም [መመስረት]፡፡ (ለ) የማይደረስበት ዒላማ ላይ ያነጣጠረ ግዙፍ፣ ገደብ የሌለው የጠፈር ምርምር ፕሮግራም [መመስረት]፡፡ (ሐ) ቋሚ፣ እንደአምልኮ ስነስርአት የመሰለ፣ እጅግ የተጋነነ ትጥቅ የማስፈታት ቁጥጥር ስርአት እና እንዲህ የመሰሉ ሌሎች ስርአቶች [መመስረት]፡፡
በዚህም መሰረት የተለያዩ ማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራሞችን ይዘረዝራሉ ይህ እንደወተሃደራዊው ተቋም የሚካሄዱ ተደርገው ማለት ነው፡፡ ይህ ቁጥጥር ለምሳሌ በግንባታ (የህዝብ መኖርያና–ሕክምና ማእከላት) እንደተፈላጊነቱ በማፋጠንና በማቀዝቀዝ ማሰራት ይቻላል፡፡ ሌላኛው አማራጭ ግዙፍ የጠፈር የምርምር ፕሮግራሞች ነው፡፡
ፖለቲካዊ
ፖለቲካዊ አስተዋፅኦው ደግሞ ጦርነት ከብሄራዊነት ጋር መቆራኘቱ ነው፡፡ ስለዚህ ሰላም ቢወርድ ሃገራት ሉአላዊነታቸውን ያጣሉ፡፡ ይህን የጦርነት የማዋሃድ ሚና የሚተካው አማራጭ ደግሞ ከብሄራዊነት የፀዳ መሆን ይኖርበታል፡፡ ሃገራት በአስተዳደራዊ እይታ ህልውና ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የዓለም ፍርድ ቤት እና የተባበሩት መንግስታት የመሳሰሉ ተቋማት ያስፈልጋሉ፡፡
የማዋሃድ ሚና የሚለውን ይህን ፖለቲካዊ መመዘኛ የሚያሟላ አማራጭ ከጠፈር የመጡ ጠላቶች የሚለውን ማስፋፋትን የሚያስረዳ ነው፡፡ እጅግ ግዙፍ የሆነ የጠፈር ፕሮጅክት በራሱ ብቻውን ታማኝነት ያለው ፍርሃትን አይፈጥርም ብለው ያምናሉ፡፡ “በራሪ ሳህኖች” “flying saucer” ወይም ያልታወቁ በራሪ ቁሶች “unknown flying objects” (UFO-ዩፎ) ክስተቶች ከሌላ ዓለማት የመጡ ፍጡራን ጥቃት ስጋትን እንኳ መፍጠር አልቻሉም ይላል ሪፖርቱ፡፡ ዛሬ ከብዙ ፕሮፖጋንዳ በኋላ በዩፎ የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር እጅግ እንደተበራከተ ልብ የምንለው ጉዳይ ነው፡፡
ጦርነትን ሊተካ የሚችል ቅያሪ “አማራጭ ባላንጣ/ጠላት” ያካተተ መሆን ያስፈልገዋል፡፡ የአካባቢ በስፋት መበከል፣ በኒኩለር ጦርነት የመጥፋት ስጋትን መተካት ይችላል፡፡ አየሩን መበከል፣ ምግብና መጠጥ ምንጮችን መበከል ካሁኑ የተራቀቀ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላል፡፡ ሪፖርቱ ይቀጥልና የሆነ ሁኖ የአካባቢ መበከል ታማኝ የስጋት ምንጭ ለመሆን ከአንድ እስከ አንድ ከግማሽ ትውልድ በኋላ እንጂ አሁን የማይታሰብ ነው ይላል፡፡ በሌላ አባባል የኒኩሌር ያህልን ሰው ማጥፋት የሚችል የአካባቢ ብክለት እስኪደርስ የተጠቀሰውን ትውልድ ያህል ዘመን ይፈጃል ብለው ይገምታሉ፡፡ ይህን እየሰሩበትም ይገኛል፡፡
ቀጥለው የህዝብ ብዛቱ በምርጫ ማለትም የሚፈለገው አይነት ሰው እንዲጨምር ማድረግም ይቻላል፡፡ እንዲያውም ጦርነት ጠንካራ/ወጣት የማህበረሰብ ክፍል ነው የሚፈጀው (የአሜሪካና የአውሮፓ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮንስ) ከኮምፒውተር ላቦራቶሪ ሁነው በሚያንቀሳቅሷቸው ቴክኒሻኖች በተደጋጋሚ ሲቪሎችን ማጥቃታቸው ስህተት ይመስለን ይሆን?)
በመጨረሻም ሪፖርቱ ወደ ሰላም የሚደረግ ሽግግር ያለ ማህበረሰባዊ ቀውስ እንዲመጣ ከተፈለገ እንደ ጦርነት ታማኝነት ያለው የስጋት ምንጭ ሊገኝ ይገባዋል ይላል፡፡ በሌላ አነጋገር ሃገሮች በጠቅላላ ሳያንገራግሩ በአንድ ጥላ ስር እንዲሰባሰቡ የሆነ አይነት የአደጋ ክስተት መገኘት አለበት፡፡
ስነ-ማሕበረሰባዊ (sociological)
በሪፖርቱ መሰረት ጦርነት ለዚህ ዘርፍ ያደርገዋል የሚሉት አስተዋፅኦ በሰው ልጅ ንቃተ ህሊና ላይ የመቀለድ ያህል ነው፡፡ በማህበረሰቡ ላይ የአርበኝነትን ስሜት ይቀሰቅሳል፡፡ ይህ የሚጠቅመው በማህበረሰቡ ውስጥ የአጥፊነትና የጠላትነት ባህርያት ያላቸውን ሰዎች ከውስጡ በማቀፍ ለመቆጣጠር ስለሚያመች ነው፡፡ ሰራዊት ሁልግዜም ቢሆን በማህበረሰቡ ውስጥ ስራ ሊያገኙ የማይችሉ ክፍሎችን በመቅጠር አመቺ የማህበራዊ ድጋፍ ማግኛ ሁኖ ኖሯል፡፡ ቀጥለውም ይህን ሚና የሚተካው ታማኝ የግል-ሂወት የማጣት ስጋትን አብሮ የያዘ ስራ መሆን ይኖርበታል ይላሉ፡፡ በዚህ መስክ እንደ መተኪያ የሚመረጠው የሞትና ሂወት ጥያቄን የማያካትት መስክ ከሆነ ጦርነት በዚህ መስክ ለማህበረሰባዊው አደረጃጀት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ሊተካ አይችልም፡፡
ስለዚህ ሰላም በሰፈነባት ዓለም ማህበረሰቡ የተረጋጋ እንዲሆን ይህን ሚና መተክያ የሚሉትን ሲጠቁሙ ሁለት መመዘኛዎችን ቀድመው ያስቀምጣሉ፡-
(1)     ፀረ-ማህበረሰባዊ ባህርያት ያላቸውን ሰዎች ማምከን መቻል አለበት ይህ ለማህበራዊ ቁጥጥር ወሳኝ ነው፤
(2)     ማህበራዊ መሰባጠርን የሚፈጥር ታማኝ ስሜት ማነቃቅያ፣ ይህ የሰው ልጅን ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ከማህበረሰቡ ፍላጎት ጋር ማጣጣም ማለት ነው፡፡
በዚህም መሰረት በዘመናዊ መልኩ ባርነትን እንደገና ማስጀመር ጥሩ አማራጭ ነው ይላሉ፡፡ ቀድሞ የነበረው ባህላዊ የባርነት ስርአት አሁን ባለው ማህበረሰብ ለመተግበር የማይቻል ሊመስለን አይገባም ይላል ሪፖርቱ፡፡ የምእራቡ የሞራልና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ከባርነት ጋር ላይስማሙ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ሰላም በሰፈነበት አለም የተራቀቀ /ዘመናዊ የባርነት ስርአት ማዳበር ለማህበራዊ ቁጥጥር አስፈላጊው ግዴታ ነው፡፡ ይህ አስገዳጅ ወታደራዊ (ሰላም አስከባሪ) አገልግሎት ማስገባት የመጀመርያው እርምጃ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡
እዚህ ተለዋጭ ባላንጣው የእውነት የደም ዋጋ የሚያስከፍል መሆን ይኖርበታል፡፡ ቀጥለውም እውነተኛ የሂወት መስዋእትነት፣ ከግዜው ጋር የሚሄድ አፈ-ታሪካዊ (Mythology) ወይም ሃይማኖታዊ ስርአት መገንባት ያስፈልጋል፣ ይህ በኛ ዘመን አዳጋች መሆኑን ሪፖርቱ ይቀበላል፡፡ የግለሰባዊ የአመፂነት ባህርያትን ለመቆጣጠር/ለማብረድ “የደም ጨዋታዎች/ፉክክሮች”–“blood games”– ይህ ልክ እንደ ስፔኑ ምርመራ(Spanish Inquisition)ወይም የሌላ ዘመናት የመተተኞቹ ፍርድ (“witch trials”)ይካሄድ እንደነበረው ቅርፅ የያዘ አድርጎ ማስጀመር ይቻላል፡፡ አላማው “ማሕበረሰባዊ ንፅህናን” እና “መንግስታዊ ደህንነትን” ለማስጠበቅ ነው፡፡ በሪፖርቱ መሰረት እንዲህ አይነቱ ነገር የማይሆን ቢሆን እንኳ ከብዙ የሰላም እቅድ አውጪዎች በላይ ሁሉንም አማራጮች መዳሰስ ዘላቂነት ላለው ሰላም ወሳኝ ነው ይላሉ፡፡ ይህ የነሱ የጦርነት ሞራላዊ አቻውን የሚያፈላልጉበት ማለታቸው ነው፡፡
ስነ-ምህዳራዊ(Ecological)
ይህ የሰው ልጅን “ሰው ልክ እንደ ሌለቹም እንስሳት” በማለት በሚያንቋሽሽ መልኩ የሚጀምር ክፍል ነው፡፡ ሰው ከአራዊት እኩል የሚቆጠርበት ነው፡፡ የማይቀረውን የምግብ እጥረት ኡደት ለማምለጥ ከኒዮሊቲክ ዝርያ በኋላ የመጣው የሰው ዘር ጦርነት አደራጅቶ በመግጠም የዝርያውን አባሎች ትርፍ ቁጥርን ይቀንስ ነበር ይላል ሪፖርቱ፡፡ (ይህ ልበወለድ ነው፣ ሳይንሳዊ ማስረጃ አይደለም፡፡) ቀጥለው ሰውን ከአይጦች ጋር ያነፃፅሩታል፡፡ ይህን ያረጉበት ምክንያት አይጦች የራሳቸውን ዝርያ ስለሚገድሉ ነው፡፡ አንዱ የጦርነት ተግባር ይላል ሪፖርቱ የሰው ዘር መኖርን (survival) ማረጋገጥ መቻሉ ነው፡፡ በተፈጥሮ ውስጥ የጠንካራው መኖር(survival of the fittest) ነው የሚሰራው፣ ደካማው ይጠፋል፡፡ በጦርነት ግዜ ይህ የተገላቢጦሽ ነው፣ ምክንያቱም በጦርነት ግዜ የሚዋጉትና የሚሞቱት ጠንካራዎቹ አባሎች ናቸው፡፡ በዚህ መስክ (በስነ-ምህዳሩ) ተቀላቢውን የህብረተሰብ ቁጥር በመቀነስ የተዋጣለት አይደለምና የተለመደው የጦርነት ስልት የሰው ዘርን የሚያጠፋ ነው፡፡ ስለዚህ የተለመደው ጦርነት በቂ ሰዎችን አይገድልም፡፡ ቀጥለው የተለመደው ጦርነት ዘመናዊዎቹ አውዳሚ የጦር መሳርያዎች ብቃትን ያደንቃሉ፡ የጦርነትን የተሳሳተ ተፈጥሯዊ የመምረጫ መሳርያነቱን (natural selection)ያስተካክሉለታል — ብዙ ሲቪሎችን በመጨረስ ማለት ነው፡፡ እንደገና የሰው አልባ አየሮች ሲቪል መጨፍጨፋቸውን ልብ እንበል፡፡
እሚገርሙ ተለዋጭ አማራጮች አሏቸው፡፡ ጦርነት የሕዝብ ቁጥርን ለመቆጣጠር ግልፅ የተደረገው ደካማ ጎን ስላለው ለዚህ የሚሆን አማራጭ ማግኘቱ ከሌሎቹ አንፃር ቀላል ነው፡፡ አስገዳጅ የሆነ ሰው ሰራሽ የዘር ፍሬ ማዳቀል (artificial insemination) የህዝብ ቁጥርን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር በቂ አማራጭ ነው፡፡ እንዲህ አይነት በላብራቶሪ የሚደረግ የማራባት ስራ ለቀጥተኛ ኢዩጀኒክ (eugenic) አስተዳደር አመቺ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሪፖርት በሚፃፍበት ወቅት የእርግዝና/ፅንስን የተለያዩ የትም በሚገኙ ክኒኖች መቆጣጠር መቻሉ፣ በመጠጥ ውሃ አቅርቦቱ ወይም በዋና የምግብ ፍጆታዎች ላይና የእነዚህን ተፅእኖ ደሞ መልሶ የሚያረክስ–‘antidote’ ማዳበር ተችሏል ይላል ሪፖርቱ፡፡ ይህ መፍትሔ ጦርነት እያለ እንደ አማራጭነት ጥቅም ላይ መዋል እንደማይችል ተመራማሪዎቹ መገንዘባቸውን ያስረዳሉ፡፡ ምክንያቱ?  ትርፍ የህዝብ መጠን የጦርነት ግብአት ነውና መወገድ የለበትም፡፡ ሌላው ቀርቶ በሩቁም ቢሆን የጦርነት የመኖር እድሉ ካለ ኢኮኖሚውን ቢጎዳውም ትርፍ የህዝብ መጠን መያዝ ግዴታ ነው ይላሉ፡፡
ባሕላዊና ሳይንሳዊ
በአርት (በስነ-ጥበብ) ዘርፉ የጦርነት ሚና ብዙም ልዩነት የሚያመጣ ጫና የለውም፡፡ ሙያተኞቹ ጦርነት የባህላዊ እሴቶችን በመወሰን ቁልፍ ሚና እንዳለው ያምናሉ፡፡ አሁን አርት ድፍረትን በውጊያ ለመሞት ፈቃደኝነትን ያሳያል፡፡ ለሳይንስ ግን ሰፊ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ የሳይንስን እድገት ያበረታታልና፡፡ ጦርነት ባይኖር አርት ይቀየራል ወይም መነቃቃቱን ከሌላ ነገር ያገኛል ስለዚህ ለአርት ተለዋጭ ማፈላለግ አያስፈልግም፡፡ ሰላም ነክ በሆኑ ነገሮች ላይ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለማስዋቢያ፣ ለመዝናኛ ወዘተ… ፡፡ አርት ጦርነት መሰረት ያደረገ ሕብረተሰብ ከሚጠብቀው ማህበራዊ-እሴቶች ይላቀቃል፡፡
በሳይንስ ግን ምትክ ለማግኘት ወደ ግዙፍ የጠፈር ምርምር መስክ መሄድ ይቻላል፡፡ እንደደረሱበት ከሆነ ሁሉም የጦርነት ስጋቶች ቢወገዱ የሳይንሳዊ እውቀት ፍለጋው ሳይቀዘቅዝ ቢበዛ ለሁለት አስርት አመታት ነው የሚጓዘው፡፡ ብዙ ያልተፈቱ ማህበራዊ ጥያቄዎች አሉ ምርምር ሊደረግባቸውና ምላሽ ሊገኝላቸው የሚችሉ ከዛ በኋላ ግን ሳይንስ የሚያነቃቃው ይጠፋል፡፡
ሌሎች
ከላይ የሪፖርቱን ክፍል አምስትና ክፍል ስድስት ቀላቅለን የጦርነት ሚናና ባይኖር ሚናዎቹን ሊተኩ የሚችሉት ብለው ያቀረቡትን ተመልክተናል፡፡ ክፍል አምስት በተጨማሪ አስተያየቶች ነበር የደመደሙት፣ አሁን ከስር እንመለከተዋለን፡፡ ጦርነትን የሚያዩት እንደ አጠቃላይ ማሕበራዊ ውጥረት መላቀቅያ አድርገው ነው፡፡ የታመቀ ውጥረትን በመልቀቅና በማሰራጨት እንደ ህክምና (ቴራፒ) ያገለግላል፡፡ እየደከመ የሚሄደው የሚያረጀው ክፍል ወጣቱን ለመቆጣጠርና ካስፈለገው ለማጥፋት የሚጠቅም “የትውልድ ማቀዝቀዣ” —  “generational stabilizer” ነው፡፡ ርእዮተ ዓለምን (አይዶሎጂ) ያጠራል፡፡ ለዓለም አቀፍ ግንኙነት መሰረት ነው፡፡
ክለሳና ማጠቃለያ
ጦርነት የፖለቲካዊ ጥያቄ ሳይሆን የመቆጣጠርያ መሳርያ እንደመሆኑ፣ የሰላም ዘመን ቢመጣ መጠነ ሰፊ ለውጦች መከተላቸው የግድ ነው፡፡ በመጨረሻ በክፍል ሰባት ላይ ባጭሩ ሃሳባቸውን ያሳውቁናል፡፡ ጦርነት ኢኮኖሚን ለመጠበቅ አስተማማኝ ዋስትና ሁኗል፡፡ ጦርነት የኢኮኖሚ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ያለውን አስተዋፅኦ የሚተካውም አማራጭ ይህን ማድረግ መቻል አለበት፡፡ ጦርነት ከገበያው የአቅርቦትና ፍላጎት መስመር ውጪ ሁኖ ኢኮኖሚው በትርፍ ምርት እንዳይጨናነቅ የብክነት መስክ በመሆን የሚጫወተውን ሚና መተካት ያስፈላጋል፡፡ ለነፃ የፖለቲካዊ ቁጥጥር ስር (ልክ እንደ ወታደራዊ ተቋም) መሆን ይኖርበታል፡፡ በፖለቲካዊው መስክ ጦርነት የተረጋጋ መንግስት መሰረት ሁኖ ያገለግላል፡፡
ፖለቲካዊ ስልጣን ተቀባይ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ አስፈላጊ/ወሳኝ የሆነ የመደብ ልዩነት እንዲኖር አስችሏል፡፡ የዜጎች ለመንግስት ያላቸውን ተገዢነትም ያረጋግጣል፣ በብሄራዊነት ጥላ ስር፡፡ የዚህ ሚናው ተቀያሪው የውጭ ጠላት ሁኖ የሚታይና በዚህም ሳብያ ፖለቲካዊ ስልጣን ተቀባይ እንዲኖረው የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡
የስነ-ማህበረሰባዊው ሚና ፀረ-ማህበረሰብ ባህርያት ያላቸው አመፀኛ ሰዎችን መሰብሰብና ማምከን ነው፡፡ የሰው ልጆችን የማህበራዊ ህብረት እንዲፈጥሩም ያበረታታቸቸዋል/ይስባቸዋል፡፡ ይህን ሚና ለመተካት የግል ሂወትን የሚያሰጋ ዘርፍ መፈጠር አለበት፡፡ ይህ የፍርሃት ምንጭ ታላቅ መሆን ይኖርበታል እናም የግለሰቡን የግል ሂወት ዋጋውን ለብዙሃኑ ሲል የሚያሳጣ መሆን አለበት፡፡
ስነ-ምህዳራዊ ሚናው በሰው ልጆች ቁጥር ብዛት እና ለሂወት አስፈላጊ በሆኑ አቅርቦቶች መሃከል ያለውን ሚዛን እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ በዚህ መስክ የሚተካው የሰው ዘር ህልውናን የሚያረጋግጥ መሆን አለበት፡፡
የጦርነት ሚና ምትኮች፡ ማሳያዎች (ሞዴሎች)
የቡድኑ ሙያተኞች አማራጭ መተኪያዎች ብለው ያስቀመጧቸው ከዚህ ቀጥሎ እናያለን፡፡ ኢኮኖሚያዊው ሚና ስፋት ባለው የማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራም ሊተካ ይችላል፡፡ ወይም መድረሻ/ መጨረሻ በሌለው የጠፈር ምርምር ፕሮግራም፡፡ ትጥቅ የማስፈታት ስርአት ከተለያዩ ተመሳሳይ ፕሮግራሞች፡፡
ፖለቲካዊ ሚናው ሁሉም ቦታ በሚገኝ–omnipresent (ልክ እንደ ሁሉን አዋቂ –omnipotent)የሆነ ዓለም አቀፍ የፖሊስ ሃይልሊተካው ይችላል፡፡ ከጠፈር (ከምድር ውጪ) የመጡ ፍጡራን ስጋት በታማኝ መልኩ መስፈን አለበት፡፡ ሰፊ ሉላዊ የአየር ንብረት መበከልን ለስጋት ምንጭነትም ይመክራሉ፡፡ የፈጠራ የሆኑ የተለያዩ ጠላቶችንም መፍጠር አስተያየት ይሰጣሉ፡፡
ስነ-ማሕበራዊው (sociological)ሚና (ይህን የቁጥጥር ሚና ነው የሚሉት) በተለያዩ ፕሮግራሞች ለምሳሌ “የሰላም ጓዶች” (Peace Corps–በኬነዲ አስተዳደር ጀምሮ አሜሪካውያንን በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለበጎ አድራጎት አገልግሎቶች የሚላክበት ፕሮግራም) እንደ ሞዴል ይወስዳል፡፡ ሌላው ባርነትን በዘመናዊና በተራቀቀ መልኩ ዳግም የመተግበርንም አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ በአካባቢ ንብረት ብክለት እንዲከፋ በማድረግ ለድጋፍ የማነቃቃት ስሜትን መፍጠርም ይቻላል፡፡ በተጨማሪም አዲስ ሃይማኖትና አፈ-ታሪክ(mythologies) በመፍጠርም ምትክ ማነቃቅያ ይገኛል፡፡ ማህበራዊ መነሾ ያላቸው የደም ጨዋታዎች/ፉክክሮች(blood games) ሌላኛው አማራጭ ነው፡፡
ጦርነት ማን መሞት እንዳለበት ስለማይመርጥ የስነ-ምህዳራዊ(ecological) ሚናው ሁሉን አቀፍ የዘር እርባታ ሳይንስ –ኢዩጀኒክስeugenics–በመተግበር መተካት ይቻላል፡፡ (ባጭር ቋንቋ የበላይ/ምርጥ ዝርያዎችን ማራባት፣ እንደ ቤት እንስሳት ማለት ነው፡፡)
አስተያየቶቹ እየተተገበሩ ነው?
ሙያተኞቹ ማወቅ ከሚገባቸው ውጪ ማንም እንዳያውቅ የመሸኛ ደብዳቤአቸው ላይ ገልፀው ነበር፡፡ ከሙያተኞቹ መሃከል አንድ ሰው ሁሉም የማወቅ መብት አለው በማለት ለህዝብ ይፋ አደረገው፡፡ ከሪፖርቱ መጠናቀቅ (ከ1966) በኋላ ምን እንደተደረገ እንመልከት፡፡
መንጋው
የሪፖርቱ ፀሃፊ ሙያተኞች ሁሉንም የሞራል እሴቶች ከግምት ከማስገባት መቆጠባቸው የሚገርም ነው፡፡ ይህ ፕሮታጎራስ (Protagoras 490 ዓ.ዓ – 420 ዓ.ዓ) የተባለው ግሪክ ፈላስፋ “የሁሉም ነገር መለክያ የሰው ልጅ ነው” በሚለው ፍልስፍናው የከፈተው በር መሰረተ እውነታው (ሎጂካል) መደምደምያው ነው፡፡ ሰው ከእንስሳት ደረጃ ነው የወረደው ልክ ለከብት መንጋ ለአጠቃላይ ደህንነታቸው የሚወስኑበት አካሄድ፡፡ ማን መታረድ አለበት ወይም ማን ነው የመንጋውን ቁጥር ለመጨመር የሚያገለግለው? የመንጋው ትርፍ ቁጥርን ለመቆጣጠር ማን ይወገድ? የመንጋው ባለቤቶች እንደሚፈልጉት የማይሄዱ የአመፀኝነት (ወንጀለኛነት) ባህርይ ያላቸው ከብቶች የትኞቹ ናቸው? ይህ ሪፖርት ሰዎችን ጥቂት ቁንጮዎችን (ልሂቃኑን) ለማገልገል የተፈጠረ ነው የሚያደርገው፡፡ እነዚህ መገልገያዎችን እንደገና አይምሯቸውን በአዲስ አመለካከት ለመቅረፅ ጥንቃቄ የተሞላበት ምርምር ነው ያደረጉት፡፡ እየተደረጉ ያሉትን አብዛኞቹን ተመልክተናቸዋል ላለመደጋገም ባጭሩ እናስታውሳቸዋለን፡፡
የሕዝብ ቁጥጥር
የሕዝብ ቁጥጥር ብዙ ገፅታ ያለው ሳይንስ ነው፡- የሕዝብ ቁጥርን መቀነስ፣ ኢዩጀኒክስ(eugenics)፣ የንቃተ ህሊና ደረጃን መቀነስ፣ የአይምሮ ቁጥጥር፣ ድህነትን መጨመር፣ የመድሃኒት ድርጅቶችን የፋይናንስ ጥገኛ በማድረግ እና በሌሎችም መንገዶች የተለያዩ የሕዝብ ቁጥጥር ገፅታዎችን መተግበር ይቻላል፡፡ እነዚህ ሰዎች በሰው ሂወት ዙርያ የተቀደሰ ነገር አለ ብለው አያምኑም “ምድሪቱን ለመታደግ” እና ለሰው ዘር መኖር (survival of the spicies) ለሚሉት (የሪፖርታቸው መአዝን) ሲሉ ብዙ ሰዎች መግደል እንዳለባቸው ነው የሚያውቁት፡፡ በስፋት የሕዝብ ቁጥጥር የሚለውን ምእራፍ መመልከት ይቻላል፡፡
ሉላዊ ሰላም አስከባሪዎች
የተባበሩት መንግስታት በአለም ዙርያ በሰላም አስከባሪነት የሚንቀሳቀሱ ወታደሮች አሉት፡፡ እኚህ ወታደሮች ከሁሉም ሃገሮች የሚመጡ ናቸው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ሳይቀር ይንቀሳቀሳሉ፡፡ አሜሪካ አሁን ትጥቅ እየፈታች ነው፡፡ ከአለም ዙርያ የሚመለመሉት ተቀጣሪ ወታደሮችንም አንዘነጋም፣ በተለይ ወፋፍራም ኮንትራት የሚሰጣቸውና እንደ ብላክ ዋተር ያሉ የግል የደህንነት ድርጅቶች የሚያዘምቷቸው፡፡ በአለም ዙርያ ፅንፈኝነትና ዘረኝነት እንዲስፋፋ የየሃገሮች አክራሪዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው፡፡ ቀውስ ቢነሳ ተ.መ.ድ በተጠንቀቅ እየጠበቀ ነው፡፡
አዳዲስ ሐይማኖቶች? የደም መስዋእት?

ፈጠራው ሲጀመርና አሁን ያለው የሌላ አለም ፍጡራን (ኤልያን) ምስል ያለው ለውጥ ቀድሞ እና የአሁኑ ለንፅፅር ከላይና ከታች ሲታይ፡፡

የአዲስ ዘመን እንቅስቃሴ ሃይማኖት ለአዲስ የአለም ስርአት የተፈቀደው ብቸኛው ሃይማኖት ይሆናል፡፡ ይህ አንድና የግል አምላክ አንፃር የሆነው ወይም ፓንተይዝም እምነት በተለያየ ቅርስ በሰዉ ሂወት ውስጥ እየገባ ያለ ነው፡፡ ሴጣን አምላኪዎች እና ባእድ (Occult)ሃይማኖት ሰው መስዋእት የሚያደርጉበት በአሎች እንደሚያከናውኑ ያደባባይ ሚስጥር ነው፡፡
ከምድር ውጪ የመጡEXTRATERRESTRIAL —ጠላቶች?
በስልሳዎቹ ሪፖርቱን በሚፅፉበት ወቅት ይህ ሰዎችን ለማሳመን የሚከብድ ነው ያሉት ነበር፡፡ የዛኔ እንዲታዩ ተተውነው ከነበሩት የፍጡራኑ መከሰት(UFO sightings)እያለ ማለት ነው፡፡ ሪፖርቱ ከተፃፈ በኋላ ምን ተከሰተ? ከሌላአለምየመጡትፍጡራንጠለፋ–“alien abductions”–ላይተሰማርተውነበር፡፡ብዛትያላቸውቦታዎችላይምተከስተውታይተዋል፡፡
በተጨማሪምኤልያን (የጠፈርፍጡራን) ያዩወይምተጠልፈውየነበሩሰዎችየመሰረቷቸውናየኤልያንጉዳይየሚከታተሉየዩፎክለቦች–UFO clubs–ተመስርተዋል፡፡ በተጨማሪምየህዝቡንቀልብየገዛአንድየዓለምመንግስትእንዲመጣያደረገበሌላአለምፍጡራንያተኮረስታርትሬክ–Star Trek–የተሰኘፊልምአለ፡፡የአዲስዘመንፍልስፍናይሰብካል፡፡ሌላኛውስታርዋርስ–Star Wars–የተባለፊልምእንደዚሁሰዎችንእጅግእሩቅባለጋላክሲ–“galaxy far far away”–እንዲያምኑአድርጓል፡፡ሌሎችምብዙፊልሞችኤልያኖችምድርንሲወሩየሚያሳዩተሰርተዋል፡፡በፊልምምዓለምመዋሃድአለባትየሚለውስብከት የሁሉምነው፡፡
የኤልያን ፈጠራ — ፈጠራ መሆኑ በብዛት ተጋልጧል፡፡ ኤም.ጄ.—12 (MJ-12) የተባለ ዶክመት በ80ዎቹ ብቅ ብሎ ነበር፡፡ ይህ ለኤልያን ተከታታዮች እጅግ ያስደሰተ ሰነድ ነበር፡፡ ሰነዱ በ1952 ለፕሬዚደንት አይዘንሀወር ስለ ኤልያን ጉዳይ የተደረገውን መግለጫ የሚያሳይ ነበር፡፡ ሰነዱ የሐሰት ለመሆኑ ተደርሶበታል፡፡ እለቱ የተፃፈበት በወታደራዊ እና ሲቪል ፎርማት ነው “18, November, 1952″ይላል፣ ትክክለኛው መሆን የነበረበት ወታደራዊ ፎርማት “18 November, 1952” ነበር፡፡ ከቁጥሩ በኋላ ኮማ አይኖረውም፡፡ ነጠላ ቁጥሮች ከፊታቸው ዜሮ ይጨመርባቸዋል በዚህም ሰነድ ላይ ተጨምሮባቸዋል ችግሩ እንዲህ አፃፃፍ የተጀመረው በ70ዎቹ ሲሆን ሰነዱ በተፃፈበት በ1952 እንደዛ መሆን አልነበረበትም፡፡ በተጨማሪም ሰነዱን ለመፃፍ ጥቅም ላይ የዋለው መፃፍያ መኪና (ታይፕ ራይተር) ከ1963 በፊት ያልነበረ ነው፡፡
ሌላው ውዝግብ ሰነዱ ሮዝዌል የተከሰከሰውን “የኤልያን በራሪ ሳህን” ለአይዘንሀወር ምንም እንደማያውቁ አድርጎ ነው የሚነግራቸው፡፡ “በአደጋው” ወቅት አይዘንሀወር የወታደራዊ ዋና አዛዥ የነበረ እንደመሆኑ ስለ ክስተቱ ቅድመ-እውቀት ይኖረው ነበር፣ እንደማያውቅ ሊዘገብለት አይገባም ነበር፡፡ ዋናው ችግሩ ግን በ80ዎቹ ሰነዱ “ይፋ ሆነ” በሚባልበት ግዜ ይወሩ የነበሩትን የኤልያን ታሪኮች ነው የሚደግመው እንጂ አዲስ ነገር አያስደምጥም፡፡ (Jim Keith, Saucers of the Illuminati ይህ መፅሃፍ የኤልያን ቅሌትን አሳጥሮ ያቀርባል፣ የበለጠ ለማወቅ እንድታነቡት ይመከራል፡፡)
 
ከላይ፡ ከናዚ ፋይሎች የተወሰደ የ1944 Haunebu II የተሰኘው በራሪ ሳህን በበረራ ላይ ያለ ምስል ሲሆን፣ ከስሩ የተጠመደውን አፈ-ሙዝ ተመልከቱ (The Dark Side of the Moon byBrad Harris (1996, Pandora Books, Germany)
ከታች፡ የHaunebu III በራሪ ሳህን ንድፍ፣ ከናዚ ፋይሎች (The Dark Side of the Moon byBrad Harris (1996, Pandora Books, Germany)
አካባቢ ንብረት
የአካባቢ ንብርት መዛባትን በተመለከተ ያለው ሳይንሳዊ ማብራርያ ውዝግብ ላይ ነው፡፡ ልክ እንደ ፒልትዳውን ማን (የእንግሊዙ የአዝጋሚ የለውጥ ሂደት ደጋፊ “ከትላልቅ” ሳይንቲስቶች ጋር በመመሳጠር በሰውና በጦጣ መሃል የሚያገናኝ ቁልፍ አገኘሁ ብሎ የሰውና የጦጣ አፅም ቅሪት ቀላቅሎ ለ40 አመታት እንዳጭበረበረው) ሳይንቲስቶች በአካባቢ ንብረት ዙርያ መረጃዎችን ሲያጭበረብሩ ተይዘዋል፡፡ በቅርቡ ከኮፐንሃገኑ የአካባቢ ንበረት ታላቅ ስብሰባ ቀደም ብሎ ሚስጥር ያወጣው የሳይንቲስቶቹን የኢመይልና ኮምፒውተር ኮድ ጠልፎ ያጋለጠው ምሳሌ ነው፡፡ (Climategate Scandal) የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት የሚሉት ለፖለቲካዊ አጀንዳ እያዋሉት እንዳ ማስረጃ ነው፡፡
ተጨማሪ የፈጠራ ጠላቶች
በመንግስቶች ድጋፍ ሚድያው በየግዜው አዳዲስ አስጊ ጠላቶችን እየፈጠረ ነው፡፡ ክርስትያኖች፣ ሚሊሻዎች፣ የቶክ ሾው አዘጋጆች፣ ቀኝ ዘመም አክራሪዎች (ብሄራውያን)፣ ወግ አጥባቂዎች ወዘተ… በአሸባሪነት እየተፈረጁ ነው፡፡ አይምሮ ቁጥጥር ላይ እንደተመለከትነውም ግለሰቡን ብዙሃን እንዲፈጅ በማድረግ ከአንዱ ፅንፈኛ በመመደብ የዛን ፅንፈኛ ቡድን ፍርሃት ማስፋፋትም ይቻላል፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታ የፖሊስ አገዛዝ ማሳወጅ የቀለለ ይሆናል፣ በዚህም ከነሱ ጋር የማይስማማውን በስፋት በተገነቡት ማጎርያዎች መጨመር ይቻላል፡፡
ባርያ ጉልበት
በአሜሪካ በማህበራዊ ዋስትና ፕሮግራም ውስጥ ያሉ ሰዎች ለሚያገኟቸው ጥቅሞች ስራ መስራት እንደሚገባ ሕግ ለመደንገግ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ከፀደቀ እነዚህ ጥቅሞች በገንዘብ ወይም “በምግብ ካርድ” መልክ አይመጡም፡፡ ዴቢት ካርድ ይጀመራል፣ ይህ አጭበርባሪዎችን ይገታል የሚል ሰበብ ይካተትበትና መንግስት የማህበራዊ ዋስትና ባሮቹን ይበልጥ እንዲቆጣጠር ያስችለዋል፡፡ በምእራብያውያኑ ወታደራዊ ወይም ሌላ የምርምር አካባቢ እየተባሉ የተከለሉ ሰፋፊ ቦታዎች አሉ እነዚህ እንደ ስታሊን አይነት የህዝብ ማጎርያ ካምፖች መሆናቸውን የሚያስረዱ አሉ፡፡
የዘረ-መል ሙከራዎች
ይህ አዲስ ጭብጥ አይደለም፡፡ ፕላቶ ሪፐብሊክ በሚለው መፅሃፉ የሚከተለው ምክር ለተዋጣለት አገዛዝ ይለግሳል፡-
“ከቤታሁ አዳኝ ውሾች ንፁህ ዶሮ ዝርየዎች… አሏችሁ አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የተሻሉ አይደሉምን? እናም ስታረቧቸው ሳትመርጡ ከሁሉም ነው፣ ወይስ ተጠንቅቃችሁ ከምርጦቹ ብቻ? ደሞም ከወጣቶቹ ነው ወይስ ካረጁት የምታረቡት ወይስ ከደረሱት? እንዲህ አድርጋችሁ ካላራባችሁ ዶሮዎቻችሁ፣ አዳኝ ውሾቻችሁ ይወርዱብናል ብላችሁ አትጠብቁም? ፈረሶቹና ሌሎቹ እንስሳትስ? ለነዚህስ ሌላ ደንብ ነው ያለው? እኚህ መርሆች ለሰው ልጆችም የሚሰሩ ከሆነ ታድያ መሪዎቻችን የላቀ ችሎታ ያላቸው ይሆኑ ዘንዳ ማሰብ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? …እስከተቻለው ከፍተኛ መጠን ድረስ ምርጦቹ ወንዶች ከምርጦቹ ሴቶች ጋር መሆን አለባቸው፣ መጥፎዎቹ ደሞ ከመጥፎዎቹ ጋር የሚገናኙበት እስከተቻለው ዝቅተኛ መጠን መውረድ አለበት፡፡ መንጋው የተቻለውን ያህል ፍፁም ማድረግ ከተፈለገ የመጀመርያዎቹ ልጆች ማደግ አለባቸው የሁለተኞቹ ደሞ ማደግ የለባቸውም፡፡ በተጨማሪም የጠባቂ (ወታደሮቹ) መንጋ ከመከፋፈል የፀዳ እዲሆን ከተፈለገ ደግሞ ይህ ርቢ የሚደረግበት መንገድ ከመሪዎቹ በቀር ማንም ማወቅ የለበትም፡፡ እናም የሆነ ብልህ ስልት መፈጠር ይኖርበታል ዝቅተኛው ሰው መሪዎቹን ሳይሆን እድልን የሚያወግዝበት ሁኔታ እንዲፈጠር፡፡ በጦርነት የበላይ ለሚሆኑት ወጣቶች ደሞ ክብርና ሽልማቶች ማግኘት አለባቸው፣ በተለይም ደሞ ይበልጥ ከሴቶች ጋር የሚገናኙበት መንገድ ሊመቻችላቸው ይገባል፣ ይህ የተቻለውን ያህል ልጆች እንዲያስገኙ ያደርጋል፡፡ የሚወለዱት ልጆች መንግስት በመደባቸው ወንዶች ወይም ሴቶች ወይም ሁለቱም የመንግስት ስራ ለሁለቱም እኩል ይገባልና ሰራተኞች ይወሰዳሉ፡፡”
ዛሬ ይህ በሳይንሳዊ መንገድ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ ህዝብ ቁጥጥር የሚለውን ምእራፍ የጀመርንበት የ20ኛውክ/ዘመን ሳይንቲስት በርትራንድ ራስል ጥቅስ እናስታውሶ፡- “ቀስ በቀስ፣ በተመረጠ የርቢ ስራ አማካኝነት በገዢዎች እና ተገዢዎች መሃከል ያለው ልዩነት የተለያዩ ዝርያ እስኪመስሉ ድረስ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ከዚህ በውኋላ የተራው ዜጋ ለአመፅ መነሳሳት በጎች የበግ ስጋ መብላት ልምድን ለመቃወም የመደራጀትን ያህል የማይመስል ይሆናል፡፡” ዝርዝሩን የህዝብ ቁጥጥር የአለም ቁጥጥር በሚለው ምእራፍ ይመልከቱ፡፡
መደምደምያ
የአይረን ተራራ ሪፖርት የሚደንቅ ነው፡፡ ይህ አንድ ነፃ ሃገርን እንዴት ወደ ፋሽታዊ ስርአት መቀየር እንደሚቻል ያሳያል፡፡ ብዙ የሪፖርቱ ጥቆማዎችም ተግባር ላይ ውለዋል፣ እየተተገበሩም ነው፡፡ ሰነዱ ማሕበረሰቡን ለመቆጣጠርና ለማረጋጋት ብዙ ዘዴዎችን ነው የዳሰሰው፡፡ ማረጋጋት ማለት አሁን ያለውን የሃይል ሚዛን፣ የመደብ ልዩነት፣ የቁንጮ የኢሉሚናቲዎች የበላይነት ባለበት እንዲቀጥል ማድረግ ማለት ነው፡፡ በሪፖርቱ መጨረሻ ላይ ጦርነትን ተክቶ ዜጎች የመንግስትን ሸክም እንዲሸከሙ ሊያደርግ የሚችል እንደሌለ ደምድሟል፡፡
እንዲህ አይነት እውነታን ያጠማዘዘ ሰላም በነገሰበት አለም ወታደሮቹ ሰላም አስከባሪዎች እና የፈለገውን ያህል ንብረት ቢወድም የፈለገውን ደም ቢፈስ ጥይቶቹ ሰላማዊ ጥይቶች ቦምቦቹ ካስፈለገ አቶሚክ ቦምብ ቢሆንም ሰላማዊ ቦምብ ይባላሉ ይላል የግሪፊን መፅሐፍ፡፡(G.E. Griffin, The Creature from Jekyll Island) ግሪፍን ቀጥሎም የፈለገው ቢሆን ምንጩ ሁሉም አንድ በአንድ እየተተገበረ ነው ይህን ለማወቅ ማድረግ ያለብን ሪፖርቱን በአንድ እጃችን እለታዊ ጋዜጣ በሌላ እጃችን ይዘን ማስተያየት ነው ይለናል፡፡ የአሜሪካ ከውስጥ መዳከሟ፣ የመሳርያ ቁጥጥሩ፣ ባካኝ የሆነ የውጭ እርዳታ፣ የተ.መ.ድ ሰራዊቶች፣ የዓለም ባንክ፣ የዓለም ገንዘብ፣ ሃገራዊ ሉአላዊነቶችን የሚጥሱ ስምምነቶች፣ የአካባቢያዊ ቀውስ ጫጫታው ወዘተ. ይህን ይጠቁማል፡፡ በመላው ዓለም ጦርነት የሚያውጁት ሃያላን (ሃያላን ስንል እንደምናስበው ሐገራትንና ህዝቦችን ሳይሆን መንግስትን የተቆጣጠሩ የሚስጥር ማህበራቱ ተላላኪዎች ማለታችን ነው፡፡) ለኢኮኖሚያዊ ደህንነት ብለው ሳይሆን ለዓለማቀፍ ህልማቸው የዓለም መንግስት (ኢምፓየር) በቁጥጥራቸው ለማድረግ ብለው ነው፡፡ አሁን በአሸባሪዎች ፔንታጎን (የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር)፣ እና የዓለም ንግድ ማእከል ማማዎች ላይ የደረሰው ጥቃት፣ በአፍጋኒስታንና ኢራቅ ላይ የተገባው ጦርነት ለምን እንደሆነ ግልፅ የሆነልን ይመስለናል፡፡ ጦርነቶች የሚፈጠሩት ማህበረሰቡን ለመቀየር ነው፡፡ በምእራብያውያኑ ሙሉ በሙሉ የሚስጥር ማህበር አባል የሆኑ ብቻ የሚገቡበትና የሚስጥር ማህበራቱ መፈንጫ በሆኑት የስለላ ተቋማት አሸባሪዎች እሚሰለጥኑት፣ እሚደጎሙትና ማቆም ሲቻል የሚለቀቁት ለዚሁ ነው፡፡ ለዚህ ነው ንፁሃን ጓንታናሞ ሲወርዱ አሸባሪዎች በየበረሃው የሚፈነጩት፡፡ ይህ ነው የሚጋጭ የሚመስለው እንቆቅልሽ ሲፈታ፡፡
Advertisements
Comments
  1. Anonymous says:

    this is just amazing and dangerous. i had no idea abt those movements. thank you so much for ur share. it's the brave of u. LET GOD WILL PROTECT US !!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s