ሰብአውያን እና የሚስጥር ማሕበራት (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

Posted: March 9, 2012 in ሳይንሳዊ አምባገነንነትና ፍልስፍና
22
ሰብአውያንእናየሚስጥርማሕበራት
ሕብረተሰብን እንደፈለጉ ለማሾርና ለመቆጣጠር ስኬታማው ዘዴ የሄግሊያዊ ዲያለክቲክን መጠቀም ነው፡፡ ዲያለክቲኩ እንደተመለከትነው ማርክስና ኢንግልስ የጋዮሻዊ ንድፈ ሃሳባቸውን ለመደገፍ ተጠቅመውበታል፡፡ እንደተመለከትነው የዲያለክቲኩ “ዚግ ዛግ” የሚያበቃው ህብረተሰቡ ፍፁማዊው ሃሳብ(Absolute Idea)ላይ ሲደርስ ነው፡- ይህም በእነሱ አመለካከት ብሱለ ሙያ (ኤክስፐርቶች)፣ ፈላስፎች ወይም ሳይንቲስቶች የሚመሩት ጋርዮሻዊ የዓለም መንግስት አገዛዝ ሲሰፍን ነው፡፡ በዚህም መሰረት በዚህ ፍልስፍና እንቅስቃሴ ውስጥ የሚስጥር ማህበራቱን እጅ እንፈትሻለን፡፡ 
በሁለት ተቃራኒዎች መካከል ያለውን መስተጋብር መቆጣጠር የልእለ ሃያልነት (Hegemony)ቦታ ያሰጣል፡፡ ሰዎች ለዚህ ሃይል እሚገዙት በጉልበት ሳይሆን እያረጉ ያሉትን ሳያውቁ በፈቃዳቸው ነው፡፡ እንዲህ አይነት ስልት ስኬታማ፣ ዘላቂና በትእግስት የሚካሄድ ነው፡፡ አሁን ያሉት የአለም ሃያላንና ርእዮተ አለማትን እንደ ክትባት የሚሰጡት የሚስጥር ማህበራት እንደሚታወቀው ግባቸው እንዲህ ያለ ልእለ ሃያልነትን ነው፡፡ ሰብአዊነትም የዚህ ልእለ ሃያልነት አንዱ መሳርያ ነው፡፡ በ1776 አዳም ዉሻፕት የኢሉሚናቲ መስራች እንደሚለውም፡- “የማሕበራችን ታላቁ ጥንካሬ የሚገኘው መደበቅ መቻሉ ላይ ነው፤ በየትም ቦታ ቢሆን በስሙ እንዲጠራ አታድርጉ፣ ሁሌም ቢሆንበሌላስም፣በሌላስራመስክተሸፍኖካልሆነበስተቀር፡፡ሰብአዊነትሰውለራሱያለውንግምት (ራስወዳድነቱንego)የሚያሻሽወይምየማይጎዳእንደመሆኑዛሬከሚታየው ግልፅሴራ–“open conspiracy”በስተጀርባመዋናነት ተሰልፎ ይገኛል፡፡ አዳም ዉሻፕት እራሱ ሃይማኖቶችንና ሃገሮችን በጠቅላላ ለየት ያለ ለሰው በሚስማማ ስነ ምግባር (ሞራሊቲ) እና ሃይማኖት መተካት አለባቸው በማለት ሰብአዊነትን ይሰብካል፡፡ ጋርዮሻዊነትና ማሕበረሰባዊነት ከዚህ ፍልስፍና እንደፈለቁ አይተናል፡፡
ሰብአዊነት በሁሉም መገለጫዎቹ፡- ስጋዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ስነ-ምግባራዊ፣ ባሕላዊ፣ ፍልፍናዊ ወዘተ… ለማድረግ የሚጥረው ሰውንና ተፈጥሮአዊውን ዓለም በእግዚአብሔር ምትክ ከማምለክ ክብር ማድረስ ነው፡፡ የአሁኑ ዘመናዊ መገለጫው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስከ ሴጣን አምላኪነት ይደርሳል፡፡ የአዲስ ዘመን እንቅስቃሴ እና የፍሪሜሶን የኢሉሚናቲን ጨምሮ የጀርባ አጥንት ነው፡፡ ሰብአውያን ምንም አይነት የሞራል ፍፁማውያን (moral absolutes) የሏቸውም የራሳቸው የሆነው የሰብአውያን መግለጫ II እንደሚለው ከሆነ “የግብረገብ (የሞራል) እሴቶች የሚገኙት ከሰው ልጅ ልምድ ነው፡፡ ስነ ምግባር (ኤቲክስ) ራሱን የቻለና ከሁኔታዎች ጋር የሚሄድ ነው፣ ምንም ዓይነት ስነ መለኮታዊ ወይም ፅንሰ ሃሳባዊ (አይዶሎጂካል) ማእቀፍ ሳያስፈልገው፡፡” ሰብአዊነት ሌላኛው የሄግሊያዊ ሂደት መሳርያ ነው፡፡ በአሁኑ ግዜ እራሳቸውን አብዮታዊም አሉ ሊበራሎች ለተከታዮቻቸው የሚያስጨብጡት ግልፅ መርህ እና እሴት የሌለ ሲሆን ይህም አደገኛ የሞራል አልባ ሕብረተሰብ መሰረት ነው፡፡ ከእንዲህ ከሁኔታዎች ጋር መሄድ የሚል መርህ አልባ መስመር መሰረቱ እዚህ ነው ያለው፡፡ የሄግሊያዊ ዲያለክቲክ ጥቂቶቹ ቁንጮዎች ወደ አዲስ የአለም ስርአት ለሚያደርጉት ጉዞ እና ቁጥጥር ሁነኛው መሳርያ — modus operandiከሆነ ሰብአዊነት ለዚህ የሚሆነው የተዋጣለት ምርጥ ስራቸው — magnum opusይሆናል፡፡ የአሁኑ የአለማችን ትውልድ ሞራል እንዲህ መውረድ የተጠናበት ሴራ ሰለባ መሆኑ  እንጂ የአጋጣሚ አይደለም፡፡ የብሪታንያ ዘመናዊ ሰብአዊነት አባት የሚባለው ብላክሃም(H. J. Blackham)ስለ ሰብአውያን እንደሚለው “መንግስን ለመገልበጥ ከሚያሴሩት በላይ አብዮተኞች ናቸው፡፡” ይላል(September – October 1981 issue of The Humanist)
 “እንደማምነው የሰው ልጅን መፃኢ ለመቆጣጠር ውግያው መሆን ያለበት ከህዝብ ትምህርት ቤቶች ነው፣ የስራ ድርሻቸውን ወደ አዲስ እምነት ቀያሪ መሆኑን በትክክል በሚገነዘቡ መምህራን፡፡… መማርያ ክፍል መሆን ያለበት እንደሚሆነውም የድሮውና የአዲሱ መጋጫ መድረክ ነው፤ እየበሰበሰ ያለው የክርስትና ሬሳ ከነክፋቶቹና መከራዎቹ እና የሰብአዊነት አዲሱ እምነት…፡፡John J. Dunphy, A New Religion For A New Age, in The Humanist, January/February 1983 edition
“የዓለም መንግስትን እውን ለማድረግ ከሰዎች ጭንቅላት ግለሰባዊነታቸውን፣ ለቤተሰባዊ ባህል ያላቸውን ታማኝነት፣ ብሔራዊ አርበኝነት፣ ሃይማኖታዊ ዶግማ መወገድ አለባቸው…፡፡ ሁሉንም ዓይነት መርዛማ እርግጠኝነትን ከወላጆቻችን፣ ከእሁድና ተራው ትምህርት ቤት፣ ከፖለቲከኞቻችን፣ ከቄሶቻችን…. ስንቀለብ ኑረናል፡፡ የሕፃናት ትምህርት መሰረት የሆነውን የልክ እና የስህተት ጭብጥ እንደገና የመተርጎምና ቀስ በቀስ የማስወገድ፣ በሽማግሌ ሰዎች እርግጠኝነት ያለውን እምነት በብልህና ምክንያታዊ (ራሽናል) አስተሳሰብ መቀየር፣ እኚህ የሰውን ባህርያት አቅጣጫ ለማስያዝ ዘግይተው የደረሱት ዓላማዎች ናቸው፡፡” Brock Chisholm, የ1959 የአመቱ ሰብአዊና የቀድሞ የአለም ጤና ድርጅት መሪ (Feb. 1946 Psychiatry)
የላይኛዎቹን ጥቅሶች ካነበብን በኋላ በትውልዱ ላይ የታወጀውን ጦርነት መረዳት አይከብደንም፡፡ የአዲሱ እምነት ስብከት አንደኛ ክፍል ሲገባ ይጀምራል፡፡ የቡድን አስተሳሰብ የሚያሰርፁ ትምርት ፖሊሲዎች በምእራቡ አለም በሳይንስ ስም ገብተዋል ህፃኑን ማእከል ያደረገ ትምህርት እየተባሉ፡፡ በምእራቡ አለም በትምህርት ቤት ውስጥ ከፈጣሪ ጋር የሚያገናኙ መስመሮች እንዲበጠሱ ከተደረገ በኋላ ለተፈጠረው ክፍተት በዮጋ  (yoga – በህንድ አምልኮ ከአምላክ ጋር ለመገናኘት ሚያደርጉት የተመስጦ ማሰብ)፣ በራስ-ማነሁለል(self-hypnosis)፣ በተመስጦ፣ እና ትንፋሽን በመቆጣጠር ከሌላ እውነታ ለመድረስ በሚደግ የመፍታታት ስራ እየተተካ ነው፡፡ ይህ ሁሉ የአዲስ ዘመን እንቅስቃሴ/ የሰብአዊነት ሴራ ውጤት ነው፡፡ እንዲህ በየቦታው እየተለመዱ የመጡት የህፃናትን አይምሮ ለመስለብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከወላጆች ተቃውሞን ሲያስከትል ይዘገባል (The New York Times Magazine May 1st 1988)
አሁን ይፋ ባልወጣ (ኦፊሻል ባልሆነ) የአለም መንግስት ስር እየኖርን እንገኛለን፡፡ ይፋ እንዲወጣና ሁሉም እንዲቀበለው ከመስከረም 11 ጥቃት የበለጠ አስከፊ አደጋ መቅድም የግድ ሊለው ይችል ይሆናል፡፡ አፍሪካውያን ድሮም በቁጥጥር ስር ናቸው፣ ጥሩ ፕሮፖጋንዳ ይበቃቸዋል፣ እንደ ቻይና አይነቱ በጋርዮሻዊ ፖለቲካ ፓርቲ ስር እየተገዛ ያለ ህዝብ ፓርቲው የወሰነውን መደገፍ ብቻ ይጠበቅበታል፣ አደገኛ ቀውስ ነፃነታቸውን እንዲሰጡ የሚያንሸራትታቸው በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውሶች (የሚስጥር ማህበራቱ በጠነሰሷችው) ወደ ስርአት አልበኝነት እየወረዱ ያሉ የምእራቡ ዓለም ሰዎችን ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ሉላዊነት ላይ ሊደረስ የቻለው የሚሥጥር ማህበራቱ ያቀቋማቸው ተቋማት ተመድን ጨምሮ ያለማቋረጥ በአለም ህዝቦች ላይ በሚፈጥሩት ጫና ነው፡፡ ከስር ለዚህ አላማ እየሰሩ ያሉ ድርጅቶች ዝርዝር ይገኛል፡፡
·     Carter Center
·     Club Of Madrid(NGO)
·     Club Of Rome(NGO)
·     Earth Council(NGO)
·     Esalen Institute
·     Federal Reserve
·     Findhorn Foundation(NGO)
·     Ford Foundation
·     Green Cross International(NGO)
·     Group-77
·     Group of 30 (NGO)
·     Hudson Institute
·     LEAD International(NGO)
·     Lucis Trust(NGO)
·     Manitou Foundation(NGO)
·     Population Council(NGO)
·     Population Institute (NGO)
·     Rand Corp.
·     Rockefeller Foundation (NGO)
·     Share International(NGO)
·     Sierra Club(NGO)
·     Temple of Understanding (NGO)
·     Trilateral Commission (NGO)
·     United Nations
·     UNDP
·     UNESCO
·     World Bank Group
·     World Conservation Union(NGO)
·     World Goodwill (NGO)
·     World Federalist Movement(NGO)
·     World Wildlife Fund(NGO)
የባሃኢዓለምአቀፍማህበረሰብ
ከመቀጠላችን በፊት ይህ ፅሁፍ እውነትን መጠምዘዝ የሚያውቅበት የክፋት ሰው ሊናገር እንደሚችለው ከክፋት ተነስቶ የትኛውንም አካል ለማስጠላት የተፃፈ እንዳልሆነና በተግባር እውነትን ፍለጋ የታከሩ ሰዎች ድብቅ አጀንዳዎችን ለማጋለጥ ያደረጉት ጥረት መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ከላይ ካለው ዝርዝር ሶስተኛው ላይ የባሃኢ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ (Bahá’í International Community (NGO)) የሚል ይገኝበታል በሃገራችንም ከአፄ ሃይለስላሴ ዘመን ጀምሮ ይንቀሳቀስ ነበር፣ ስለሆነም ስለዚህ እምነት ታሪክና ከሚስጥር ማህበራቱ ያለውን ትስስር መዳሰስ እንሻለን፡፡ እንደ ማሳሰቢያ ወይም ልናስተውለው የሚገባ ነገር ተራው የባሃኢ ተከታይ ስለ ሃይማኖቱ የሚያወቀው ነገር ቢኖር ሌላ ሰላማዊ የፈጣሪ መልእክት መሆኑን ነው እንጂ ስለ ሚስጥር ማህበራቱ አድማ የሚያውቀው ነገር አይኖረውም፡፡ እንዲያውም ልክ እንደርሶ የሃገራችን የባሃኢ እምነት ተከታዮችም ፍሪሜሶን ወይም ኢሉሚናቲ የሚለውን ቃል ይሄኔ ሰምተውትም አያውቁ ይሆናል፡፡
ሚስጥር ማህበራቱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት ከፈለጉ ሊቃውንቶቿ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁና የክህደት ትምህርት አራምደው የማያውቁ ሃገር እንደመሆኗ ከሌላ ሃገራት የላቀ ፈተና ይገጥማቸዋል፡፡ ለዚህም ነው በመላው አፍሪካ ቅኝ ሳይገዟቸው ቀድመው የፍሪሜሶን ሎጅ (ማምለክያ፣ መስለብያ፣ መሰባሰብያ ቤታቸው ስም ሎጅ ነው) እሚከፍቱት በኢትዮጵያ እንኳን የፍሪሜሶን ሎጅ ሊከፍቱ ቀርቶ ፅሁፎቻቸውን እንኳ በቋንቋችን አሳትመው አያውቁም፡፡ ስለዚህም ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡባቸው የሚችሉት መንገዶች ቀጥተኛ ያልሆኑ እና በስውር በሌላ ስም ተሸፋፍኖ ብቻ ነው፡-
አንድ፡ የረዥም ግዜ ልምዳቸውን በመጠቀም የሃይማኖት ቀኖና አለመግባባት በመፍጠር ቤተክርስቲያን በማዳከም (ለምሳሌ በቅርቡ የተሃድሶዎች እንቅስቃሴ–በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የማኅበረ ቅዱሳን ዶክመንቴሽን ክፍል በ2003ዓ.ም ያሳተመውን “የተሐድሶ መናፍቃን ዘመቻ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ” የተሰኘውን መፅሀፍ ማንበብ ይቻላል፡፡ በመፅሃፉ ገፅ 28-29 ላይ ዊልያም ብላክ የተባለ አማሪካዊ ፕሮቴስታንት በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት እንደሆነባቸው ምስክርነቱን –“ተቃውሞውን” ቢባል ይሻላል– የሠፈረበትን ፅሁፍ ድረ ገፁን አጣቅሰው አቅርበዋል፡-
“በሃገሪቱ ውስጥ እየተንሰራፋና ስር እየሰደደ ያለውን ምእራባዊ ባህል እና በተሀድሶ አራማጆች ቤተ ክርስቲያኒቷን ለማደስ የሚደረገውን ጥረት ሁለቱንም የሚቃወምና ለዚህም እየሰራ ያለ አድሃሪ የሆነ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል እንቅስቀሴ አለ፡፡ ይህ ማኅበርም ቤተ ክርስቲያንን ለመለወጥ የሚደረገውን ማንኛውንም ነገር ለመከላከልና ለራሳቸው ማንነትና ኢትዮጵያ በዓለም ስላላት ቦታ አስፈላጊ ነው የሚሉትን የቤተ ክርስቲያኒቷን ገጽታ ለመጠበቅ ይፈልጋሉ፡፡”
መፅሃፉ በጥንቃቄ የተፃፈ እንደመሆኑ ሙሉ ታሪኩን ከመፀሃፏ ማንበብ ይቻላል፡፡)፤
ሁለት፡ ፖለቲካዊ ርእዮተ አለሞችን በመከተብ ሕዝቡን መከፋፈል (ምሳሌ አያስፈልገውም)፤
ሶስት፡ እንደ ሰብአዊነት ያሉ ፍልስፍናዎችንና እንደ ባሃኢ ያሉ እምነቶች ተከታዮችን ማብዛት ብቸኛ አማራጫቸው ነው፡፡ (ሰብአዊነትን በቀጥታ ወይም ደግሞ በስፋት እንደምንመለከተው እራስን ስለማሳደግና ስለ ጥሩ ሂወት የሚሰብኩ “self-help” እና “how-to” የስነ-ልቦና መፃህፍትን ተጠቅሞ ልቦናን በመስረቅ ወይም ስለ ተመስጦና ጠፈር (ዩኒቨርስ) እና ሁሉም ነገር ውስጥ እግዚአብሔር እንዳለ (ፓንተይዝም) የሚሰብኩ የምስራቁ እምነት ነክ መፃህፍቶች በማባዛት ማስፋፋት ይቻላል፡፡) እነዚህ ሁሉ ጨምሮ የታወቁ የአዲስ ዘመን እምነት አራማጆች የፃፏቸው ስራዎች በስፋት ተሰራጭተዋል፡፡
ወደ ባሃኢ ስንመለስ አንድ ወጣት ኢራናዊ ነጋዴ ነበር በ1844 አዲሱን ሃይማኖት የመሰረተው፡፡ አላማውም እንዳሳወቀው ለአዲሱ የእግዚአብሔር መልእክተኛ መንገድን ማመቻቸት ነበር፣ በዚህም በአረቢኛ “መግቢያ” — “ባብ” ተባለ፡፡ ወዲያውም “ባቢስ” እየተባሉ የሚጠሩት ተከታዮቹን ማፍራት ቻለ፡፡ በ1850 ባብ ታስሮ በሞት ተቀጣ፡፡ እንደሚሉት ከሆነ አንመለስም ያሉ 20,000 ባቢስ ተገድለዋል፡፡
ባለዘጠኝ ጫፍ ኮከብ የባሃኢ እምነት ምልክት
ግድያውን ካመለጡ የባብ ተከታዮች አንድ ሚርዛ ሁሴን ዓሊ የተባለ ነበር፣ በኋላ ባሃኡላ የተባለው፡፡ በ1863 ባሃኡላ ባብ የተነበየለት መልእክተኛ እኔ ነኝ ብሎ አሳወጀ፡፡ የባሃኡላ ተከታዮች ባሃኢስ ተባሉ፡፡ ባሃኡላ ያለፉት የፈጣሪ መልእክተኞች፡- እንደ አብርሃም፣ ክሪሽና፣ ሙሴ፣ ዞሮአስተር፣ ቡድሃ፣ ክርስቶስ፣ መሃመድ፣ እና ባብ ሁሉም የሰላም እና የፍትህ ቀናት በዓለም ዙርያ ይመጣል ብለው እንደተነበዩ ያስረዳል፡፡ ባሃይስ የባሃኡላ መገኘት የዓለማቱን “ቅዱሳን” ፅሁፎች እውን ያረገ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በ1867 ባሃኡላ ለነገስታት፣ ለገዢዎች እና የሃይማኖት መሪዎች ተልእኮውን በተመለከተ ተከታታይ ደብዳቤ ይፅፍላቸው ጀመር፡፡ የአዲስ ዘመን መምጣትንና እየመጡ ስላሉት አብዮቶች እና የዓለም ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስርአት መቀየር ያስጠነቅቅ ነበር፡፡ በ1868 ወደ ኣካ የግዞት ከተማ እንዲሄድ ተደረገ እዚህም ከመቶ በላይ የሚሆኑ የባሃኢ እምነትን አጠቃለው የሚይዙ ፅሁፎችን ፃፈ፡፡ የመጨረሻ ኑዛዜው የመጀመርያ ልጁ አብዱል ባሃ የባሃኢ እምነት መሪ አድርጎ መምረጥ ነበር፡፡ የአብዱል ባሃ ፅሁፎችም እንደ ቅዱስ ነው የሚቆጠሩት፡፡
ባሃኡላ ትክክለኛውን አዲስ የአለም ስርአት ይሰብክ ነበር፡፡ አዲስ የአለም ስርአት የሚለው ቃልም የራሱ ነው፡፡ እንደሚያዘው ከሆነ፡- የዓለም መንግስት፣ የዓለም ምክርቤት (ፓርላማ)፣ የዓለም ሕግ፣ የዓለም ፍርድቤት፣ የዓለም ፖሊስ ሃይል፣ የዓለም ቋንቋ፣ አንድ ቋሚ የዓለም መገበያያ ገንዘብ፣ ዓለም ዓቀፋዊ እኩል የቀረጥ ስርአት፣ እና በባሃይ እምነት ጥላ ስር የዓለም ሃይማኖቶች ጠቅላላ መዋሃድ (ሕብረት) ይሰብክ ነበር፡፡ በተ.መ.ድ. ህንፃ ውስጥ ከሚገኘው ቢሯቸው ሁነው ብዙ ፖለቲከኞችን የባሃኡላ ትምህርትን እንዲቀበሉ ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ አዲስ የአለም ስርአት የሚያቀላጥፉ ፕሮጀክቶች ላይ በዋናነት ይሳተፋሉ ለምሳሌ ባካባቢ ንብረት ዙርያ በሚሰሩት፡፡ እምነቱ መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ሃይልም ነው፡፡ ይህ ድርጅት ከፍተኛ ተፅእኖ ያለው ሲሆን ባሃኢስ በኢትዮጵያ እድሜያቸውን የሚቆጥሩት ሳብሪ ኤልያስ የተሰኘ ግለሰብ (ኢትዮጵያዊ አይደለም) ከግብፅ አዲስ አበባ ከገባበት ግዜ ከ1934 ጀምሮ ነው፡፡ ወዲያውም መፃህፍት በአማርኛ ተርጉሞ አሳትሟል፡፡ በቅርቡ ደግሞ በ2009 75 ዓመታቸውን አክብረዋል፡፡ ባሁኑ ወቅት ህፃናት ትምህርት ላይ በስፋት የሚሰሩ ሲሆን ከህፃናት ትምህርት እስከ ሁለተኛ ደረጃና መሰናድኦ እና ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ድረስ በባሃይ መርህ የተመሰረቱና የሚንቀሳቀሱ ተቋማትን እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ በዓለም አቀፍ መድረክም “ሽልማቶች” እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
በአፄ ኃይለስላሴ ግዜ የባሃኢስ መሪ መጥታ ጉብኝት በምታደርግበት ወቅት ንጉሱ፣ ሚስታቸውና፣ ልጆቻቸው በተለያየ ፕሮግራም እያገኙ ሰፊ መስተንግዶ አርገውላት ነበር፡፡ በ2009 75 ዓመታቸውን በሚያከብሩበት ወቅት ከአሜሪካ የመጡ የባሃኢ “መዘምራን” በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ዝግጅታቸውን አቅርበው ነበር፡፡ http://en.wikipedia.org/wiki/Bah%C3%A1’%C3%AD_Faith_in_Ethiopia(በምን ስሌት እንደተፈቀደላቸው ፀሃፊዎቹ የሚያውቁት ነገር የለም፣ ምናልባት የፈቀዱላቸው አባቶች ምክንያት ይኖራቸው ይሆናል፡፡)
የኢሉሚናቲ ትስስር
የመጀመርያ ክፍል ላይ እንዳየነው ይህቺ መካከለኛው ምስራቅ የብዙ እምነቶችና ሚስጥራት መፍለቂያ ነች፡፡ ከራሳቸው ከባሃኢ ፅሁፎች የተወሰዱ ጥቅሶችን በማቅረብ ከኢሉሚናቲ ጋር ያላቸውን ትስስር ባጭሩ እንመለከተዋለን፡፡
“በስነመለኮት ብቻ ሳይሆን በሌሎች የእውቀት ቅርጫፎችም የላቀ ነበር፣ እንደ ሰብአውያን [ጥናት](humanities)እንደ ኢሉሚናቲ ፍልስፍና፣ እንደ ጥንታውያን (mystics)አስተምህሮዎች….፡፡” Memorials of the Faithful: Nabíl-i-Akbar
“ከአንድ ሺህ አመታት በፊት ከሃያሉ ጋር በፀጥታ ለመገናኘት በአንድ የሚሰበሰቡ በፐርሺያ የጓደኞች ማህበር የተባለ ማህበር ተመስርቶ ነበር፡፡ …የተቀደሰ ፍልስፍናን ለሁለት ይከፍሉት ነበር፡ አንደኛው በትምህርት ቤት በሚሰጥ ትምህርት እና ጥናት የሚደረስበት፤ ሁለተኛው ደግሞ ኢሉሚናቲዎች ወይም የውስጠኛውን ብርሃን ፈላጊዎች (ተከታዮች) ነው፡፡ የዚህ ፍልስፍና ትምርት ግዜዎች በፀጥታ የሚከወኑ ነበሩ፡፡ … ሁሉም ቅዱሳዊ ችግሮች (ጥያቄዎች) ይህ ብርሃን በሚሰጠው የብርሃት ሃይል(illumination)ይፈቱ ነበር፡፡ …እኚህ ሰዎች፣ “የውስጥ ብርሃን ተከታዮች” የመጨረሻው የሃይል መአርግ ላይ ይደርሳሉ፣ ሙሉ ለሙሉም ከጭፍን ዶግማዎችና ሌሎችን ከማስመሰል ነፃ ይወጣሉ፡፡ ሰዎች የእኚህን ሰዎች ንግግሮች ይከተላሉ፤ በራሳቸው፣ ከራሳቸው ውስጥ፣ ሁሉም ሚስጥራት ይፈታሉ፡፡”
BAHÁ’Í SCRIPTURESWords of Bahá’u’lláh, THE ILLUMINATI p.322
“ቀጥሎም ካህሊል “ሊቁ” (“ማስተር”) ተከታዮች አፈራ፡፡ በፐርሺያ ካሉት ኢሉሚናቲዎችም ጎራ እንደሆነ ነገረኝ፡፡ ብድግ ብሎ እንዲህ ይላል፣ የእግዚአብሔር መገለጫዎች ለምን እንፈልጋለን? እያንዳንዳችን ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት እንችላለን፡፡ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር በቀጥታ እገናኛለው፡፡”
Juliet Remembers Gibran AS TOLD TO MARZIEH GAIL, WORLD ORDER A Baha’i Magazine, Vol. 12, Number 4, Summer, © 1978. Pages 29-31
“የዓለም ፈላስፎች በሁለት ክፍል ይከፈላሉ፡ ቁሳውያን ነፍስንና ዘላለማዊነቱን የሚክዱ፤ እና ቅዱሳን ፈላስፎች፣ የእግዚአብሔር ጥበበኞች፣ በነፍስ እና ከዚህ በኋላም በቀጣይነቱ የሚያምኑት ትክክኛ ኢሉሚናቲዎች፡፡”
The Promulgation of Universal Peace, ለቲኦዞፊ ማህበር የተደረገ ንግግር 24 July 1912
“የባሃይ አስተዳደራዊ መዋቅር ካሁኑ በቀጠና፣ በሃገር፣ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተዘርግቷል ለወደፊት ለሚመጣው ማህበረሰብም እንደ አርአያ (ሞዴል) ሊሆን ይችላል፡፡ ለባሃይ መዋቅሮች ሰዎች የሚመረጡት በስራቸው (በችሎታቸው) ብቻ ነው፣ ያለምንም ምልመላና የምረጡኝ ዘመቻnominations or canvassing፡፡ በባሃይ ስርአት ስልጣን ወደ ዝቅተኛው ደረጃ የወረደ ነው፣ በተጨማሪም ለግለሰቦች ሳይሆን ለቡድኖች ነው የሚሰጠው፡፡
“በሁሉም ደረጃ መወያየት የባሃይ አስተዳደር ቁልፍ ክፍል ነው፡፡ የቀጠና ማህበረሰብ ስብሰባ የሚያካትተው ፀሎት፣ ውይይት፣ እና ማህበራዊ መስተጋብር ናቸው ይህ የሕብረትና መተጋገዝ መንፈስ ለማዳበር የተቀረፀ ነው፡፡ ባሃኡላ ከ100 ዓመት በፊት ያሰማው ጥሪ እስከአሁን ዓለም ምላሹን እንዲሰጥ እየጠበቀ ነው፡፡ የአዲስ የአለም ስርአት መጀመርያው ከጉያችን ስር ነው፡፡”
THE NEW WORLD ORDER – Published by the Spiritual Assembly of the Bahá’ís of Warwick
ይኚህ ከላይ ያነበብናቸው ጥቅሶች ስለዓለም መንግስት የሚያሰስተምሩት ከሚስጥር ማህበራቱና ከኢሉሚናቲጋ ያላቸውን ቅርርብ በሚገባ እንደሚያሳዩ ግልፅ ነው፡፡ ከስር ወደ ሰብአዊነት ሃይማኖት ተመልሰን መጀመርያ ካነሳናቸው ባእድ አምልኮዎች ያለውን ዝምድና እናያለን፡፡
ሰይጣን አምልኮ እና የሰብአዊነት ሃይማኖት
ሰይጣን አምላኪነት የመሪዎች  ዋናው እምነት ነው፡፡ መሪዎች ለሚያደርሱት ጥፋት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ቢኖሩም ለጥቂቶቹ ቁንጮዎች የበላይነት እቅድ ዋናው መንስኤ ግን ይህ አምልኮ ነው፡፡ ለዘመናት የፍሪሜሶን አካል የነበረ ነው፡፡ የጥንት ባእድ አምልኮ ሚስጥራትም ይኸው ነው፡፡ ከክርስትናና ከይሁዴ ያፈነገጡት የግኖስቲሳዊነት እና ካባላ የክህደት ትምህርቶች ይህንኑ ከባቢሎን የሚስጥር ማህበራት የተዋሱት አምልኮ ነው፡፡ የዳርዊን አዝጋሚ የለውጥ ሂደት ንድፈ ሃሳብ (ኢቮሉሽን ቲኦሪ) ለዚህ አምልኮ ሳይንሳዊ መጠግያ የሰጠው ነው፡፡ ስጋዊ ሰብአዊነትም ይህን የዳርዊን ንድፈ ሃሳብ ተጠግቶ አምልኮውን ያቀረበ ነው፡፡ ይህ አምልኮ እስከ አሁን ድረስ አቀራረቡን እየቀየረ በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡
በዘመነ አብርሆት (ኢንላይትመንት) ግዜ ሴጣን አምልኮ ስጋዊ ሰብአዊነትን ተላብሶ መምጣቱን የመርሃቸውን መግጠም በመመልከት አገናዝበናል፡፡ ይህ የሆነው ማንኛውንም መለኮታዊ የስነ ምግባር ትእዛዛት/ሕግጋትን በመሻርና የነዚህን ጥያቄዎች በተመለከተ የሰው ልጅ የመጨረሻው ብቸኛ ወሳኝ መሆኑን መግለጫ ሲፅፉ ግዜ ነው፡፡ ዋይታከር ቻምበርስ በአሜሪካ ድብቅ የጋርዮሻውያን (የኮሚኒስት) እንቅስቃሴ አባል የነበረ ባጭሩ እንደሚከተለው ይገልፀዋል፡-
“ሰብአዊነት አዲስ አይደለም፡፡ እንዲያውም የሰው ልጅ ጥንታዊው ሁለተኛው እምነት ነው፡፡ ቃል ኪዳኑ በፍጥረት የመጀመርያዎቹ ቀናት ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ስር ነበር ሹክ የተባለው፡ “እንደ [አማልክት] ትሆናላችሁ፡፡””
ሰብአዊነት-ሸገር(Transhumanism) በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተራቀቀ ጥንታዊውን አምልኮ ያቀርብልናል፡፡ ቃሉን የፈጠረው የአዝጋሚ ለውጥ ንድፈ ሃሳብ አራማጁ ጁልያን ሃክስሌ (የደራሲው አልዶክስ ሃክስሌ ወንድም) ሲሆን በ1957 “ሰው እንዳለ ሰው ሁኖ ነገር ግን የሰብአዊ ተፈጥሮ እምቅ አቅሙን በማወቅና ለሰብአዊ ተፈጥሮው የሚሆን አዲስ አቅምን በመፍጠር እራሱን ተሻግሮ [ወይም ከራሱ ተሽሎ] ሲገኝ ነው፡፡” በማለት ይተረጉመዋል፡፡ ከ1980ዎቹ ወዲህ ደሞ ትርጓሜው ከዚህም ከረር ብሏል፡፡ በ1990 በዶ/ር ማክስ ሞር እንደሚከተለው ተተርጉሟል፡-
ሰብአዊነት-ሸገር ከሰው-ያለፈ ሁኔታ ላይ እንድንደርስ የሚመራን የፍልስፍና አይነት ነው፡፡ ሰብአዊነት-ሸገር ከሰብአዊነት፣ ለአመክንዮና ሳይንስ ያለውን አክብሮት፣ ለተራማጅነት (ፕሮግረስ) ያለውን ቆራጥነት፣ እና ለሰው (ወይም ለሰው-ሸገር) ልጅ ሂወት ያለውን ዋጋ/ክብር ጨምሮ ይጋራል፡፡… ሰብአዊነት-ሸገር ከሰብአዊነት የሚለየው በተለያዩ ሳይንሶችና ቴክኖሎጂዎች ምክንያት በሂወት ተፈጥሮና አማራጭ ላይ የሚከተሉት መሰረታዊ ለውጦችን እውቅና መስጠቱና መጠበቁ ነው፡፡
ሰብአዊነት-ሸገር የናኖቴክኖሎጂ፣ ባዮቴክኖሎጂ፣ ኮግኒቲቭ ሳይንስ (አይምሮን እንደ መረጃ ማብሰልሰያ የሚያይ)፣ እና የመረጃ ቴክኖሎጂን የሰው ልጆችን ወደ “ሰውን-ያለፈ” ደረጃ እንዲደርሱ ለመግፊያ መጠቀምን ይደግፋል፡፡ እዚህ ከደረሰ ሰው – ሰው መሆኑ ያበቃለታል፡፡ ማሽን ይሆናል፣ ሞትንና ሌሎችን የሰው ደካማ ጎኖችን ያሸንፋል፡፡ የመጨረሻው ግብ እንደ አማልክት ለመሆን ነው፡፡ ሰብአውያን-ሸገሮች እንደጥንታውያን የሰይጣን አምላኪዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እግዚአብሔር እንደ ጨቋኝ ሰይጣንን እንደ ነፃ አውጪ አርገው ይወስዳሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ዶ/ር ማክስ ሞር የተሰኘው ሰብአዊ-ሸገር 33ኛ መአርግ የደረሰው አሜሪካዊው ኢሉሚናቲ አልበርት ፒኬ ስለ ሴጣን ያለውን ይደግማል፡- ሉሲፈር፣ ብርሃን [ችቦ] ያዢው! ለጭለማ መንፈስ ይህን ስም መስጠት እንግዳ ነው፡፡ ሉሲፈር፣ የንጋት ልጅ! እሱ ነው ብርሃን የሚይዘው….(Morals and Dogma, 321) በዶ/ር ማክስ ሞር ደሞ፡- ሉሲፈር የአመክንዮ፣ የወሳኝ ሃሳብ መግለጫ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር እና ሌሎች ዶግማዎች በተቃራኒው የቆመ ነው፡፡ እሱ በእውነት ፍለጋ ላይ ለአዲስ ሃሳብና አዲስ መአዝን መገኘት የቆመ ነው ይላል፡፡
እንዲያውም በአንዳንድ ሰብአውያን-ሸገሮች ሰይጣንን እንደ ታዳጊያቸው –patron saint– አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሰብአዊ-ሸገር የሉሲፈራዊነት ዋና የሆኑ ባህርያቶችን የያዘ ነው፡፡ የባሰው ደግሞ ይህ የሆኑ የተገለሉ ጥቂቶች የሚከተሉት ፍልስፍናዊ እምነት አለመሆኑ ነው፡፡ የዘረመልና ሕብረተሰብ ማእከል(Center for Genetics and Society)ዋና ዳይሬክተር የሆነው ሪቻርድ ሄይስ(Richard Hayes) እንደሚያብራራው፡-
“…በየል ዩኒቨርሲቲ የዓለም የሰብአዊ-ሸገር ማህበር የመጀመርያ ብሔራዊ ስብሰባቸውን አድርገው ነበር፡፡ ከ20 ሃገሮች በላይ ቅርንጫፍ አላቸው፣ “በዘረመላቸው የዳበሩ” “ሰው-ያለፉ” ፍጡራንን ስለማርባት ያቀነቅናሉ፡፡ ሌሎች የዚህ የአዲሱ ቴክኖ-ኢዩጀኒክስ አቀንቃኞች ለምሳሌ የፕሪንስተን ዩኒቨርስቲው ሊ ሲልቨር(Lee Silver)፣ እንደሚገምተው ከሆነ በዚህኛው ክ/ዘመን መገባደጃ ላይ “የኢኮኖሚው፣ የሚድያው፣ የመዝናኛ ኢንዱስትሪው፣ እና የእውቀት ኢንዱስትሪው ሁሉም ገፅታዎች በዘረመላቸው በበለፀጉ መደቦች–GenRich class–ቁጥጥር ስር ይገባሉ፡፡… የተፈጥሯዊው ብቻ ሁነው የሚቀሩት ደግሞ የዝቅተኛ ክፍያ የሚሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች ወይም ላብአደሮች ይሆናሉ፡፡””
እየጨመሩ ያሉት የምሁራኑና የቴክኖ-ኢዩጀኒክስ የወደፊት እይታ ተዳምሮ ሰብአዊ-ሸገር የሉሲፈራዊነትን አርማ ይዞ ወደ 21ኛው ክ/ዘመን ተሻግሯል፡፡ ሰብአዊ-ሸገሮች በዘረመል ምህንድስናና በባዮቴክኖሎጂ የሰውነት መቀያየር ስራቸው ታዳጊያቸው ሰይጣን ያደረገውን ዓላማ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡-
“ወደ ሰማይ ዐርጋለው፣ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰብያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፣ በልኡልም እመሰላለሁ…” ትንቢተ ኢሳያስ 14፣ 13-14፡፡
ይህ የጥቂቶቹ ቁንጮ መሪዎችም ህልም ነው፡፡ የሉሲፈራውያን አምልኮ የፈለገውን ቅርፅ ቢይዝ አላማው ግን አንድና የማይቀየር ነው፡ ለሰው ልጅ የማይገባውን ክብር በመስጠት ከአምላክ መቁጠር፡፡ ይህ ለርሶ ወይም ለኔ ተቆርቁረው ሳይሆን ለራሳቸው ጥማት ማርኪያ ዘዴ ፈልገው ያደረጉት ነው፡፡ በቀጣይ ምእራፍ የዚህ ጥማታቸው መገለጫ የሆነውን ሳይንሳዊ አምባገነንነት፣ የመርህ አልባው የሰብአዊነት ፍልስፋናዊ ሃይማኖት መስመር የወለደው ሳይናሳዊ አምባገነንነትን እንመለከታለን፡፡ ይህ የስራ ፈት አይምሮ ፈጠራ ሳይሆን አወዛጋቢ በሆነው የአይረን ተራራ ሪፖርት በተሰኘው ሰነድ ተሞርኩዘን የምናየው ነው፡፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s