ቅንጫቢ ፮ የቦልሸቪክ አብዮትና ደጓሚዎቹ ከበርቴዎች (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

Posted: March 7, 2012 in ሽብር

የቦልሸቪክ አብዮት
ራሽያና ነገስታቶቿ ሁሌም የኢሉሚናቲዎችን የበላይነት ህልምን እንዳከሸፉ ነው፡፡ እናም የገንዘብ ባላባቶቹ በራሽያ አብዮት እንዲነሳ ገንዘብ ከማፍሰስ ተቆጥበው አያውቁም፡፡ በአንደኛ አለም ጦርነት ተወጥራ እያለች ቦልሸቪኮችን፣እንደ አብዮተኛነት እንኳ ሰፊ ተቀባይነት ያልነበራቸውን ፅንፈኞችን-ይሄ በመጀመርያው የራሽያ “ዱማ” ምርጫ ባገኙት ድምፅ (ባላገኙት ቢባል ይሻላል) በግልፅ የታየ ነው፣ እነዚህን አናሳ ተደማጭነት የነበራቸውን ሲደጉሙ ነበር፡፡
በ1917 ተከታታይ አመፆች በውኋላ ዛር ኒኮላስ ከስልጣኑ እንዲወርድ ተደረገ፡፡ ስልጣኑንም ሊበራል ዲሞክራት የሆነው መስፍን ጆርጅ ልቮቭ ለጥቂት ግዜ ይዞ ለዲሞክራት ሶሻሊስት ለሆነው ኪረንስኪ አስረከበ፡፡ ኪረንስኪም ከጀርመን ጦርነቱን ሳያስቆም ለሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ምህረት ሰጠ፡፡
እነ ሮዝስቻይልድ ከሚልነር ጋር የራሽያን አብዮት አቀዱ፣ ከሺፍ (20 ሚሊዮን ዶላር ለቦልሸቪኮች የሰጠ) ጋር ሁነውም በገንዘብ ሲደጉሙ ነበር፡፡ ወረንበርግ ቤተሰብ (የጀርመን ማእከላዊ ባንክ ጌቶች)፣ እነ ሮክፌለር፣ እነ ሞርጋን ድጋፋቸውን ሲሰጡ ነበር፡፡
በ1814 ኢሉሚናቲዎችና እነ ሮዝስቻይልድ በቪየና ኮንግረስ ግዜ ማለትም ከናፖሊዮን ሽንፈት በውኋላ አውሮፓን በፌደሬሽን አንድ አድርጎ የመግዛት ህልማቸውን በመጀመርያ ሙከራቸው (የናፖሊዮን ጦርነት ባስከተለው ውድመት) እውን የሚያደርጉ መስሎአቸው ተደስተው ነበር፡፡ ግን የራሽያው ንጉስ በቪየና ኮንግረስ ሳይስማማ ቀርቶ ለብቻው ከፕረሽያ (ጀርመን) እና ኦስትሪያ ጋር “ሆሊ አልያንስ” በመፈረም አከሸፈባቸው፤ ኢሉሚናቲዎችም ራሽያን የሚበቀሉበትን ቀን ሲጠብቁ ነበር፡፡ 1917ትም መጣች ሁሉም ለአብዮቱ የድጋፍ እጁን ዘረጋ፡፡ ንጉሱ ከተወገደ በውኋላ ቀይ ሰራዊቶች -ቦልሸቪኮች እና ነጮቹ ራሽያን ለመቆጣጠር እየታገሉ እያለ የአሜሪካ ሰራዊት በሳይቤርያ ግዛት በመስፈር ነጮቹን ሊደግፉ እንደመጡ በማስመሰል የራሽያ ገበሬ ከቀዮቹ ጋር ተሰልፎ እንዲዘምት አደረጉ፡፡ ነጮቹ ከተደመሰሱ በውኋላ አሜሪካኖቹ በጀግና አሸኛኘት ተሰናብተው ሄዱ፡፡ እስኪ ከስር በኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የወጣውን ዜና ተመልከቱ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ዜና በስህተት እንጂ እውነት ለመናገር ተብሎ የሚወጣ አይደለም፡፡ ጥብቅ የመረጃ ቁጥጥር አለና፡፡
“ኒው ዮርክ ታይምስ New York Times (February 15, 1920 7:4)እንደዘገበው ከሆነ፡
“የጋዜጣው ዘገባ ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡- 
ቭላዲቮስኮቭ አሜሪካ-ዘመም
የአብዮታዊው ወተሃደር ግሬቭን  ከመወገን በመቆጠባቸው አመስግኗል
ቭላዲቮስኮቭ የካቲት 1 (አሶሽኤትድ ፕሬስ) – የከተማዋን ከኮልቻክ [ከነጮቹ] አገዛዝ ሙሉ ለሙሉ ነፃ መውጣት ዛሬ ሁለተኛ ቀን ክብረ በአልን ሰልፍ፣ ጎዳና ስብሰባና መድረክ ንግግር አድምቀውት ውለዋል፡፡ በሁሉም የመንግስት ህንፃ ላይ፣ ብዙ ንግድ ቤቶች እና መኖርያ ቤቶች ላይ ቀይ ባንዲራ ይውለበለባል፡፡
የጎላ አሜሪካ-ዘመም የሆነ ስሜት እንዳለ ግልፅ ነው፡፡ ከአሜሪካ ዋና መስሪያቤት ህንፃ ፊትለፊት የአብዮታዊው መሪዎች መንገዱን ተሻግሮ ካሉ ህንፃዎች ደረጃ ላይ በመውጣት፣ ንግግር አደረጉ፣ አሜሪካውያኑን እውነተኛ ጓደኞች በወሳኝ ግዜ ይሄኛውን እንቅስቃሴ ያዳኑት በማለት፡፡ ህዝቦቹም በአለምአቀፍ መድረክ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይም ከጣልቃ ገብነት የፀዳ የጓደኝነት ፖሊሲ እንዲኖር በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
አዲሱ መንግስት በኒኮላክ ጠቅላይ ሹሙም ወደ አሜሪካኑ አዛዥ (ኮማንደር) ቴሌግራም ለሜጀር ጀነራል ግሬቭስ ልኳል፣ ከተማዋ ተይዛ በነበረችበት ወቅት በነበረው ከጣልቃ-ገብነት የፀዳ የወዳጅነት ፖሊሲን ለማረጋገጥ ላሳዩት ጥረት እና በተጨማሪም ለአካባቢው ሁኔታ በሰላም ስምምነት ለመቋጨት በተለገሰው ድጋፍ ምስጋናውን ገልፅዋል፡፡
…………………………..
“በተለይም ደሞ ልብ ማለት ያለብን፡-
“. . . አሜሪካውያኑን እውነተኛ ጓደኞች በወሳኝ ግዜ ይሄኛውን እንቅስቃሴ ያዳኑት በማለት፡፡”” የአሜሪካ የሚስጥር ተቋም ከሚለው ያልታተመው መፅሃፋችን የተወሰደ፡፡
እስኪ ባጭሩ ድጋፋቸውን ወደ ኋላ መለስ ብለን እንየው፡- “ይሄ ሁሉ ሲከናወን ግን [ጦርነቱና አብዮቱ] ሌኒን እና ትሮትስኪ የት ነበሩ?” ብሎ ስለነዚህ ሁለቱ የራሽያ/ቦልሸቪክ አብዮት ጀግኖች ጠይቆ መመለስ ይጀምራል ጌሪ አለን None Dare Call it Conspiracyበተሰኘው መፅሃፉ፡፡ “ሌኒን በስዊዘርላንድ ነበር፣ ከ1905 ዓ.ም. የከሸፈው አመፅ ተከትሎ በግዞት በምእራብ አውሮፓ ነበር እሚገኘው፡፡ ትሮትስኪም በግዞት ነበር፣ በኒውዮርክ ከተማ ለሚገኝ የኮሚኒስት ጋዜጣ ሪፖርተር ነበር፡፡ ዛሩ ከስልጣን ሲለቅ ቦልሸቪኮች ብዙም እሚታይ ፖለቲካዊ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ወደ ስልጣን የመጡትም የተጨቆኑት የራሽያ መደቦች ጠርተዋቸው ሳይሆን፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ እሚገኙ እጅግ ሃያል የሆኑ ሰዎች ስለላኳቸው ነው፡፡
“ሌኒን የቀለጠ ጦርነት ቀጠና ሁኖ በነበረው የአውሮፓ ምድር በዝነኛዋ “የተሸፈነችው ባቡር” –“sealed train” ውስጥ ተደርጎ ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ዶላር በወርቅ መልክ ይዞ ተላከ፡፡ ይህ ሁሉ የተመቻቸለት በጀርመን ከፍተኛ አዛዥ እና ማክስ ዋረንበርግ በሌላ ዝነኛ የረዥም ግዜ ሶሻሊስት የነበረ አሌክሳደር ሄልፕሃንድ ቅፅል ስም “ፓርቨስ” በኩል ነበር፡፡ ትሮትስኪ ደሞ ኒውዮርክን በኤስ.ኤስ. ክሪስቲና ተሳፍሮ በመጋቢት/ማርች/ 27፣ 1917 ለቆ ሲሄድ መጀመርያ ያረፉበት ወደብ ሃሊፋክስ፣ ኖቫ ስኮሽያ ነበር፡፡ እዚያ ሲደርሱ ካናዳውያኑ ትሮትስኪንና የያዘውን ገንዘብ በህግ ቁጥጥር ስር አዋሏቸው፡፡ ይህ ለካናዳ መንግስት ማድረግም እሚገባው ነገር ነበር፣ ምክንያቱም ትሮትስኪ በተደጋጋሚ እንደተናገረው ከሆነ በራሽያ ገብቶ ስልጣን እሚይዝ ከሆነ ይህ “የኢምፐርያሊስቶች ጦርነት” እሚለውን ወዲያውኑ እንደሚያስቆመውና ከጀርመን ጋር ለብቻ ስምምነት እንደሚያካሂድ ነው፡፡ ይህ ደሞ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጀርመን ወታደሮችን ከምስራቁ ግንባር ወደ ምእራቡ ግንባር እንዲሸጋገሩ እና የካናዳን ወታደሮች እንዲገድሉ ይረዳቸዋል፡፡ ስለዚ ትሮትስኪ በካናዳ እስርቤት ለአምስት ቀናት ተረከዙን እንዲያበርድ አደረገው፡፡ ቀጥሎ ከየት መጣ ሳይባል ብሪታንያ (የወደፊት የኩን፣ ሎኢብ [በጀርመን ትልቅ የካዛሮች ባንክ] ሸሪክ ሰር ዊልያም ዋይዝማንን) ዩናይትድ ስቴትስ ደሞ (ሌላ ማንንም ሳይሆን በሁሉም ቦታ እሚከሰተው “ኮኖሬል” ሃውስን) ልከው የካናዳ መንግስት ላይ ጫና መፍጠር ጀመሩ፡፡ ምንም እንኳ ጦርነት ውስጥ ብንሆንም፣ በብዙ ቃላት ተጠቅመው  “ትሮትስኪን ልቀቁት” አሏቸው፡፡ እና በአሜሪካ ፓስፖርት፣ ትሮትስኪ ሌኒንን ሊያገኝ ሄደ፡፡”
እንግዲህ እነዚህ ዝነኞቹ የጭቁኖቹ ጠበቆች ትክክለኛ ታሪክ ሲታይ የበዝባዥ ካፒታሊቶች እሚሏቸው ወዳጆች ሁነው ይገኛሉ፡፡ ምናልባት ኔስታ ዌብስተር እንዳለችው ቴምፕላሮች እና አይሁዶች ከፀረ-ክርስትና አቋም ጋር የዓለም አቀፋዊ ፋይናንሻል ሞኖፖሊን ስለሚያራምዱ የዓለም አቀፋዊ ማህበረሰባውያን ወዳጆች እንጂ ጠላቶች ሊሆኑ ስለማይችሉ ይሆናል ወዳጅነታቸውና መረዳዳቱ ሊመሰረት የቻለው፡፡

 

ትሮትስኪንና ሌኒንን [ሂትለርንም] ፋይናንስ ያደረጓቸውን “ብርዥዋዎች” እሚያሳይ ሰንጠረዥ፡፡ (ላይ ከጠቀስነው መፅሃፍ የተወሰደ)
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s