ቅንጫቢ ፬ 9/11 (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

Posted: March 7, 2012 in ሽብር
12
9/11፡የሽብራዊ አገዛዝ ውሎ
በመስከረም 11፣ 2001 አራት አውሮፕላኖች ውስብስብ በሆነ አኳኋን በተሳፋሪዎች፣ በማንሃታን ቀጠና እንዲሁም ፔንታጎን ላይ ጥቃት ፈፀሙ፡፡ ግዜውን፣ የጥቃት አላማውን እና ግጭቱን ተከትሎ ለህንፃው ውድመት የተሰጠው ማብራሪያ ያስከተለው የኢንጂነሪግ ህጎች ጥሰት ኦፊሻላዊው መግለጫ ጥያቄ ውስጥ አስገብተውታል፡፡ በዚህ ምእራፍም ጥቃቱ ዋሻ ፅፈት ቤታቸውን ያደረጉ ፅንፈኞች ሳይሆኑ ውስጥ አዋቂዎች ያቀነባበሩት ውስብስብ ዘመቻ መሆኑን እንፈትሻለን፡፡
ጥቃቱ ከተፈፀመበት ዕለት ጀምሮ ነበር ኦፊሻላዊ የጥቃቱ መንስኤ መግለጫዎች ሲሰጡ የነበሩት፡፡ እነዚህ መግለጫዎች በዋናነት የሚያውጠነጥኑት፡- በኦሳማ ቢንላድን የሚመሩ ፅንፈኛ ሙስሊም አክራሪዎች ቀላልና ያልተወሳሰበ መሳርያ ብቻ በመታጠቅ አራት አይሮፕላን መጥለፍ እንደቻሉ፤ ጠላፊዎቹ ከጠለፏቸው አይሮፕላን ሁለቱንም ወደ መንትየ ማማዎች ለማብረር እንደቻሉ፤ ጠላፊዎቹ ሶስተኛ አይሮፕላን ይዘው ወደ ፔንታጎን በረሩ፤ ቆይቶም የህንፃው ክፍል ላይ እንዲደረመስ አደረጉ፤ ማማዎቹ ከደረሰባቸው የአይሮፕላን ግጭት በተነሳው የእሳት ቃጠሎው በመዳከማቸው ለመድርመስ ቻሉ የሚሉ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ይሁንና ከነዚህ ውስጥ አንዳቸውም መግለጫ የሚያረጋግጥልን ጠንካራ ደጋፊ ሃሳብ ያቀረበ አካል የለም፡፡ በአይሮፕላኖቹ ውስጥ ይገኙ የነበሩ ብላክ-ቦክስ የያዙት መረጃ ይፋ አልተደረጉም፡፡ ከአይሮፕላኖቹ ተደረጉ የተባሉት የስልክ ጥሪ ምንም አይነት ማስረጃ አልቀረቡም፡፡ ከአየር-ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የተደረጉ ቃለመጠየቆች በሙሉ እንዲጠፉ ተደርገዋል፡፡ መንትያ ሕንፃዎቹ ከተደረመሱ በኋላ ይገኙ የነበሩ የብረት ቅሪቶች (የወንጀሉ ማስረጃዎች) ያለምንም ምርመራ በፍጥነት እንዲወገዱ ተርገዋል፡፡ (ወደ ቻይና ተላኩ፡፡) እነዚህ ሕንፃ የተሰሩበት ንድፍ ህዝቡ እንዲያውቅ የተደረገበት አጋጣሚ የለም፡፡ ኤፍ.ቢ.አይ በራሱ ፈቃድ ያለምንም ማስረጃ ከተወነጀሉት ጠላፊዎች የተገናኘ አንድም ዘገባ ማቅረብ አለመቻሉ ከብዙዎች ጥቂቶቹ ያልተፈቱ እንቆቅልሾች ናቸው፡፡
የመስከለም 9/11 ጥቃት  አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት በዋናነት መጀምርያ በፌማ (Federal Emergency Management Agency /FEMA 2002) ከዛም በ 9/11 ኮሚሽን ( The 9/11 Commission, 2004)በመቀጠል ኒስት (National Institute of Standards and Technology/NIST,2005) በዋናነት ሪፖርት ቀርቧል (የ9/11 ኮሚሽንሪፖርት ማንም ሳይነካው የፈረሰው ስለዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ መፍረስ ያለው ነገር የለም፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ኒስት የዚህ ሕንፃ ሪፖርት በተደጋገሚ እንዲዘገይ በማድረግ በመጨረሻ በ2008 ይፋ አድርጓል፡፡) ሪፖርቱ ባጠቃላይ  የመንትዮቹ ማማዎች መውደም ዓይነተኛ ምክንያት የሚያደርጉት አውሮፕላኖቹ ከመንትዮች ማማዎች በመጋጨታቸው ምክንያት በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር መቅለጥ ነው፡፡ የሚገርም ነው ታድያ ምግብ ስናበስል ብረድስቱ የማይቀልጠው ለምንድ ነው? ሲሉ እንዲጠይቁ ያደረጋቸውም ነበሩ፡፡ በፌማ 2002 ሪፖርትላይ፡
 “The structural damage sustained by each tower from the impact, combined with the ensuing fires, resulted in the total collapse of each building.”የሚል ዓ.ነገር እናገኛለን፡፡
በቀጣዩ ክፍል የ9/11 ጥቃት በማስመልከት የቀረቡት አፊሻለዊ መግለጫዎች ከእውነት በእጀጉ የራቁ መሆናቸውን እናያለን፡፡ ከታሪኩ ስፋትና ጥልቀት አንፃር በሰፊው መዳሰስ ባንችልም የቅጥፈቱን መሰረታዊ ጭብጥ ይቀርባል፡፡ ቀጣዩ ዘገባ በተለያዩ የሂወት ዘርፎች ምርምር በማድረግ በዛ ያሉ መፅሃፍቶች የፃፈውና በተለይ 9/11በማስመልከት ጥልቅ የሆነ ጥናት ያሰፈረበትና እጅግ ታወቂ የሆኑት The New Pearl Harbor: Disturbing Questions about the Bush Administration እና 9/11 and The 9/11 Commission Report: Omissions and Distortionsበሚለው መፅሃፎቹ የሚታወቀው ዴቪድ ሬይ ግሪፈን (David Ray Griffin) እና በሌሎች ጥናቶቹ በመመስረት ይሆናል፡፡በሚቀጥለውዘገባላይ  ዴቪድሬይግሪፈን፡ The Destruction of the World Trade Center: Why the Official Account Cannot Be True(ሰፊ ጥናት)፣ Building What? How SCADs Can Be Hidden in Plain Sight: The 9/11 “Official Story” and the Collapse of WTC Building Seven (ሰፊ ጥናት)፣ ጥቃቱን በማስመልከት በሚያዝያ 18 2005University of Wisconsin at Madison ካቀረበው (ሰፊ ጥናት)፣The Mysterious Collapse of World Trade Center 7 (መፅሀፍ)፣ Significant Pattern to 9/11 Report’s Omissions & Distortions, The 9/11 Commission Report: Omissions and Distortions, “a 567-page lie”(ጥናት)ከሚሉት ሰፊ ጥናትናቶቹ ባጭሩ እንዳስሳቸዋለን፡፡
1.የመንትዮቹ ሕንፃዎች መደርመስ
ኦፊሻላዊው ታሪክ ለዚህ ሁነኛ ምክንያት አድርጎ የሚያቀርበው አውሮፕላኖቹ ከመንትዮች ማማዎች በመጋጨታቸው  ምክንያት የተነሳው የእሳት ቃጠሎ ነው የሚል ነው፡፡ኦፊሻለዊው ታሪክ በሁለት አብይ ምክንያት ተቀባይት አይኖረዉም፡- (ሀ) ከዚህ በፊት በእሳትቃጠሎ የወደመ ሕንፃ አለመኖሩ፤ (ለ) ማማዎቹ የወደሙት በማፍረሻ ዘዴ (Controlled Demolition) መሆኑን የሚያስረዱ ብዙ መረጃዎች መኖራቸው፡፡
(ሀ) ከዚህ በፊት በእሳትቃጠሎ የወደመ ሕንፃ አለመኖር
የመስከረም 11 (9/11)ኦፊሻላዊው ታሪክ ተሟጋቾች ይህንን ግልፅ የሆነ እውነታ ምናልባት ከጠቀሱት ከስንት አንዴ ነው፡፡ የ9/11 ጥቃት በተመለከተ ግልፅና ቁርጥ ውሳኔ የያዘው ሪፖርት ተብሎ የሚታሰበው በ2005 የወጣው የኒስት –National Institute for Standards and Technology (NIST)- ሪፖርት`ኳ በጠንካራ የብረት ምሶሶዎች የተገነቡት ትላልቅ ሕንፃዎች በእሳት ቃጠሎ መውደም የተለመደ ክስተት ነው ሲል ይዋሻል፡፡ የ9/11 ኦፊሻላዊ ቲዎሪ ተሟጋቾች በእርግጥ ውድመቱ  በቀላሉ በእሳት ቃጠሎ ብቻ የተፈጠረ ሳይሆን የእሳት ቃጠሎውና የአይሮፕላን ግጭቱ የፈጠሩት ጉዳት ጥምር ውጤት ነው ይላሉ፡፡ሆኖም ግን፣ማማዎቹ ሲሰሩ ቦይንግ 767 የሚያክል መጠን ያላቸው አይሮፕላን ሊያደርሱ ከሚችሉ ግጭቶች  መቋቋምእንዲችሉ ተደርገው ነበር የተሰሩት፡፡የመንትዮቹ ማማዎቹኮንስትራክሽን ማናጀር ሆኖው የሰሩት ሃይመን ብራውን “ማንኛውንም ነገር ለመቋቋም ከሚገባው በላይተነድፎ (over-designed)ነበር የተሰራውይህም አደገኛ አውሎንፋስ፣ፍንዳታዎችናአይሮፕላን ግጭት ጭምርያጠቃልላል፡፡” በማለት ይገልፃሉ፡፡ (Bollyn, 2001)በኤም.አይ.ቲ የ materials engineering ፕሮፌሰር የሆነውና የ9/11 ኦፊሻላዊ ቲዎሪ ደጋፊ የሆኑት ቶማስ ኢጋር(Thomas Eagar) እንኳ ይህን ሃሳብ ይደግፋል፡፡ ኢጋር የአይሮፕላኖቹ ተፅእኖ ይህ ነው የሚባል አይደለም ምክያቱም ይላል “በመጀመርያ ግጭት የወደሙት ቀዋሚ አምዶች/ ምሶሶዎች ብዙ ባለመሆናቸው፤ በተቀሩት አምዶች የሚፈጥሩት ጫና አሁንም አምዶቹ የነበራቸው እጅግ ጠንካራ ቅርጽ ይዞው እንዲቀጥሉ የሚያደርግ ነው፡፡” (Eagar and Musso, 2001, pp. 8-11) በተመሳሳይ ሁኔታ፣ የኒስት ሪፖርት የአይሮፕላኖቹ ግጭት ሕንፃዎቹን ለመደርመስ የነበረውን አስተዋፅኦ ሲያብራራ በቅድምያ የሚያተኩረው አይሮፕላኖቹን ብዙ “እሳትን/ሙቀትን መከላከያ” (fire-proofing) ከብረቱ አስለቅቀዋል የሚል ነው፡፡
ሰለዚህ ኦፊሻላዊ ቲዎሪ የ9/11 መንትያ ማማዎቹ ለመደርመስ ምክንያት አድርጎ በዋናነት የሚያቀርበው የእሳት ቲዎሪ ነው፤ ስለዚህ የእሳት ቃጠሎ በብረት ምሶሶዎች የጠነከሩ ሕንፃዎች ላይ ከ 9/11 በፊት ሆነ በኋላ ፣ወይም በ9/11 ለት በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ግዙፍ ሕንጻዎች መውደም መንስኤ ሁኖ አያውቅም የሚለውን እንመረምራለን፡፡  አንድ ሰው ምናልባት ለሁሉም ነገር መጀመርያ አለው በማለት በ9/11 የመንትየዎቹ ማማዎቹ ጥቃት ላይ የነበረው እሳት ከዚህ በፊት ተከስቶ የማያውቅና ለየት ያለ ስለነበረ ለማውደም በቂ ነበር ሊል ይችላል-በርግጥም ይላል፡፡ እስቲ ይህንን እሳቤ እንመርምረው፡፡ ከዚህ በፊት ተከስቶ የማያውቅና ለየት ያለ እሳት ቃጠሎ ብለን እንድናምን የሚያደርገን ምንድ ነው? ከብረት (steel) ባህርይ በመነሳት አንድ ብረት ጥንካሬ ሊያጣ የሚችለው የተከሰተው እሳት እጅግ የጋለ፣ መጠነ ሰፊ/ብዙ ቦታ የሚሸፍንና ቃጠሎው ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ይሁንና በወቅቱ በማማዎቹ ላይ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ሶስቱ ባህርያት ይቅርና አንዱም አልነበረውም፡፡
ከዚህ በመነሳት ማማዎቹ የወደሙት የብረት ዓምዶቹ ስለቀለጡ ነው የሚለው መግለጫ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ብረት 2008°F እስኪደርስ ድረስ መቅለጥ አይጀምርም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሃይድሮካርበን (የሃይድሮጅንና ካርቦን ድብልቅ) አማካኝነት በግልጽ/ክፍት ቦታ የሚነሱ የእሳት ቃጠሎዎች፣ ለምሳሌ በነጭጋዝ (kerosene) ማለትም የጄት ነዳጅ የመቃጠል ደረጃቸው እስከ 1700°F አከባቢ የሚደርስ ሲሆን፤ ይህ ማለት ብረት ከሚቀልጥበት ደረጃ1100°F ገደማ ያነሰ ነው፡፡ከዚህ በመነሳት ማማዎቹ የወደሙት የብረት ዓምዶቹ ስለቀለጡ ነው የሚለው መግለጫ ተቀባይነት የለውም፡፡ በርግጥ፣ አብዛኞቹ የኦፊሻል ቲዎሪ ደጋፊዎች ይህን ወለፈንዴ ሃሳብ ይዘው አይሟገቱም፡፡ ይህም እውነታውን በሚገባ ሳይመረምሩ እንዲሁ ዝምብለው የእሳት ቃጠሎው ብረቱ ጥንካሬውን እስከሚያጣበት ደረጃ ድረስ በመቆየቱ፣ ለመታጠፍ በቃ የሚሉ ትንሽ አይደሉም፡፡ ቶማስ ኤጋር ከነዚህ የሚመደብ ነው፡፡ ኤጋር “ብረት የሙቀት መጠን 1300°F ሲደርስ 80% ጥንካሬው ያጣል፡፡ በወቅቱ የሆነውም ይሄው ነበር” ይላል፡፡ይሁንና ይህን ንግግር ተአማኒነት እንዲኖረው ከተፈለገ እንኳን አሁንም ብረቶቹ ከዚህ በላይ በእጅጉ መጋል አለባቸው፡፡
በወቅቱ የነበረው የሙቀት መጠን ይህን ያህል የሙቀት ሐይል አልነበራቸውም፡፡ አብዛኛው አውሮፕላኑ ውስጥ የነበረው ነጭ ጋዝ (የጀት ነዳጅ) እዛው አውሮፕላኑ የተጋጨበት ቦታ በፍጥነት የተቃጠለ ሲሆን የተቀረው ደግሞ በ10 ደቂቃ ውስጥ ደብዛው ጠፍቷል፡፡ ከዚህ በኋላ የእሳቱ ነበልባልም (flames) ጠፍቷል፡፡ ማማዎቹ ከተጋጩ 15 ደቂቃበኋላ የተነሱ ምስሎች የተወሰነ የእሳት ነበልባልና እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥቁር ጭስ ያሳያሉ፤ ይህ እሳቱ (ከውስጥ አየር በማጣት) ኦክስጅን እንደተራበ ጠቋሚ ምልክት ነው፡፡ ይህን እውነታ የተገነዘበው ቶማስ ኤጋር፣ የእሳት ቃጠሎው “1200 ወይም 1300°F አከባቢ” ነበር ይላል፡፡ (Eagar, 2002)
በማማዎቹ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ኢጋር ያለውን ያህል የሙቀት መጠን እንዳልነበራቸው የሚያሳምኑ ምክንያቶች አሉ፡፡ የፎቶግራፍ ምስሎቹ እንደሚያሳዩት የእሳት ቃጠሎው መስኮቶች አልሰበረም፤ ከተከሰተበት ቦታም ተሻግሮ አልተዛመተም፡፡ (Hufschmid, 2002, p. 40) እነዚህ የፎቶግራፍ ምስሎቹ በመረጃ ተደግፈው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በኒስት –National Institute for Standards and Technology/ NIST,2005 ጥናት ተደርጎባቸዋል፡፡ አስራ ስድስት ወሰን ላይ የሚገኙ ቋሚ አምዶች ምርመራ የተካሄደባቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 3 አምዶች ላይ የሚገኙት ብረቶች ብቻ ከ250°ሴ.ግ (482°F) በላይ የሙቀት መጠን እንደነበራቸው ተረጋግጥዋል በማንኛውም የማሀል ቋሚ አምዶች (core columns) ይህን ያህል የሙቀት መጠን እንኳ መድረሳቸው ምንም መረጃ የለም (NIST ,2005, p. 88) ይላል፡፡
የኒስት ሪፖርት “በዚህ ውጤት መሰረት ድምዳሜ መድረስ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ጥናት የተካሄደባቸው አምዶች፣ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰባቸው ወለሎች ውስጥ ከሚገኙት የወሰን አምዶች(perimeter columns) 3% ሲሆኑ፤ ከማሀል ቋሚ አምዶች ደግሞ 1% ስለሚወክሉ ነው ይላል፡፡” የእሳት ቃጠሎ ከተከሰተው ወለል ከነበሩት አምዶች ውስጥ በእርግጥ ይህን ያህል ትንሸ ፐርሰንት ብቻ በጥናቱ መቅረባቸው ጥያቄ የሚያስነሳ ቢሆንም “ተገቢ” እና የሚጠበቅ ነው፡፡ ምክንቱም የመንግስት ባለስልጣኖች (የሚስጥር ማሕበራት ቁንጮዎቹ) ከጥቃቱ ባኋላ በአፋጣኝ አብዛኛውን ስብስርባሪ ብረቶች ተሽጠው በመርከብ ወደ ቻይና እንዲላኩ አድርገዋልና፡፡ የሆነ ሁኖ፣ በየትኛውም መስፈርት በትንሽ ፐርሰንት የአምዶች ግኝት የተመሰረተው የኒስት ዘገባ የሚናቅ አይደለም (የጥቃቱ መንስኤ የእሳት ቃጠሎ አለመሆኑ ይጠቁማል፡፡) ምክንያቱም ማንኛውም የማሀል ቋሚ አምዶች ከሚጠበቀው የሙቀት ደረጃ በላይ ደርስው ነበር የሚለው ግምት…በተግባር ያልተመረመረ ግምት መሆኑን ያስረዳሉና፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ፣ 78ኛውፎቅ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ተከላካዮች ቡድን አለቃ ባደረደው የሬድዮ ግንኙነት መሰረት ባካባቢው በሁለት የተለያየ ቦታ የእሳት ቃጠሎ እንዳለና መቆጣጠር እንደሚችልና አጋሮቹን ሲያሰማራ ተደምጧል፡፡ ብረት የሚያቀልጠው እሳት እንዴት አልበላውም? ሰሜናዊው ማማ የወደመው ከተገጨ 1 ሰዓት ከ42 ደቂቃ በኋላ ሲሆን፤ ደቡባዊው ማማ ደግሞ ከተገጨ 56 ደቂቃ በኋላ ነበር የወደመው፡፡ የቆየው ለአጭር ሰዓት መሆኑ ብቻ አይደለም የሚደንቀው በህንጻው ላይ የነበረው ቃጠሎ በጥቂት የሕንጻዎቹ ክፍል መሆኑ ጭምር እንጂ፡፡ አጭር ጊዜ የቆየው ቃጠሎ ማማዎቹን እንዲወድሙ መንስኤ ሆኗል የሚለው “ቅሌት የወረሰው ሰበብ” ምን ያህል አስቂኝ መሆኑን ለመረዳት በሌሎች ቦታዎች ከተከሰቱ ቃጠሎዎች በማነጻጸር እንመልከት፡፡ “በ1988 ሎስ አንጀለስ በ First Interstate Bank ሕንጻ ላይ ለ3.5 ሰዓታት የተሰራጨ የእሳት ቃጠሎ ተከስቶ ነበር፡፡ ከሕንጻው 62 ፎቆች ቃጠሎው ያጠቃቸው 5ቱ ሲሆኑ፤ በሕንጻው  መሰረታዊ ቅርፅ ላይ (ስትራክቸራል) የደረሰ ምንም ዓይንት ጉዳት አልነበረም ”ይላል፡፡ (FEMA, 1988) ሌላው፣ በ1991 ለ18 ሰዓታት ቆይታ የዘለቀው ከባድ ቃጠሎ በፊለደልፍያ በሚገኘው ባለ 38 ፎቅ One Meridian Plaza ሕንጻ ላይ ተከስቶ ነበር፡፡ የFEMA ሪፖርት ምንም እንኳን “እጅግ ዘግናኝ ለሆነ የእሳት ቃጠሎ በመጋለጣቸው…የሕንጻው አግዳሚዎች/ተሸካሚዎች (beams) እና የብረት ዘንጎቹ (girders) የረገቡና (sagged)፣ የተጣመሙ ቢሆኑም…አምዶቹ ያለምንም ጉልህ ጉዳት ጭነቱን ደግፈው ቀጥለዋል ይለናል፡፡ (FEMA, 1991) በ1994 “በካራገስ” (Caracas) 50 ፎቆች ያሉት ሕንጻ ላይ ለ 17 ሰዓታት የቆየ ቃጠሎ ተከስቶ ነበር፡፡ የሕንጻው የላይኛው 20 ፎቆች ሙሉበሙሉ በቃጠሎው የጋዩ ቢሆንም ሕንጻው ግን አልወደመም ይላል፡፡ ከዚህ ሲነፃፀር ነው ለ56 ደቂቃ ብቻ ቆይታ የነበረው ደቡባዊ ማማ ቃጠሎ እንዲወድም መንስኤ ሆኗል የሚል “ቅሌት የወረሰው አመክንዮ” እውነት ነው ብለን እንድናምን የሚፈለገው፡፡ በማማዎች (ለአጭር ግዜ) ላይ ከነበረው የእሳት ቃጠሎ በተቃራኒ፤ በሎስ አንጀለስ ፣በፍላደልፍያና “በካራገስ” የተከሰቱት የእሳት ቃጠሎ መስኮቶች ለመስበር በቂ የሆነ የሙቀት ሓይል ነበራቸው፡፡
ሌላው  ለንፅፅር  የሚቀርበው በ1990ዎቹ አጋማሽ በብሪታንያ በብረት የተገነቡ ሕንጻዎች ላይ ለብዙ ግዚያት በሚቆይና ማንኛውንም ነገር ማቃጠል በሚችል እጅግ ከፍተኛ ሙቀት ላለው እሳት ቢጋለጡ  ብረቶቹ ላይ ምን ዓይነት ጉዳት ሊደርስ ይችላል የሚለውን ለማወቅ የተደረገው ሳይንሳዊ-ፍተሻ ነው፡፡ FEMA እነዚህ ሳይንሳዊ-ፍተሻ ከዳሰሰ በኋላ “በተደረገው ፍተሻ ምንም እንኳ በሶስቱ የብረት አግዳሚዎቹ የሙቀት መጠን ከ800-900ዲ.ሴ (1500ዲ.ፋ-1700ዲ.ፋ) ቢደርስም…ጥናት በተካሄደባቸው ስድስት ውስጥ የውደመት ምልክት በአንዱም  አልነበረም” ይላል፡፡(FEMA, 1988, Appendix A)
አንዳንድ የኦፊሻላዊው ታሪክ ተሟጋቾች መንትሟቹ ባልተለመድ ሁኔታ ለየት ላለ የእሳት ቃጠሎ እንዲጋለጡ ያደረጋቸው  የሆነ ነገር ነበር የሚል ግምት ይሰጣሉ፡፡ ይሁንና እነዚህ ግምቶች በምንም ዓይነት መረጃ የተደገፉ አይደሉም፡፡ ኖርማን ግሎቨር (Norman Glover) እንዳብራራው፡- “አብዛኞቹ ትላልቅ ሕንፃዎችበአገልግሎት ዘመናቸው የአደገኛ እሳት ቃጠሎ መከሰቻ ሁነው ያውቃሉ፡፡ ማንኛውም ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በእሳት ሳቢያ ፈርሶ አያውቅም፡፡ የዓለም ንግድ ማእከልም በ1975 እንዲህ ዓይነቱን አደጋ አስተናግዶ ነበር፤ ሆኖም ህንፃው አናሳ ጉዳት ደርሶበት ተጠግኖ ወደ አገልግሎት ሊመለስ ችሏል፡፡” ብሏል፡፡
(ለ) ማማዎቹ የወደሙት በማፍረሻ ዘዴ (Controlled Demolition) መሆኑን የሚያስረዱ ብዙ መረጃዎች መኖራቸው
እውነታው ብረቶቹ በእሳት ወድመዋል ከሚለው ሪፖርት በተገላቢጦሽ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም እሳት በብረት ለተገነቡት ሕንፃዎች ለመውደም ምክንያት ሁኖ አያውቅም፡፡ ማማዎቹ በእሳት ካልወደሙ ታድያ በምን ሊወድሙ ቻሉ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ እንደሚችል የሚጠበቅ ነው፡፡ መልሱ ሰው ሰራሽ ህንፃ የማፍረሻ ዘዴ (Controlled Demolition) የሚል ይሆናል፡፡ “ኮንትሮልድ ዲሞሊሽድ” /በቁጥጥር ስር የሚከናወን ውድመት/ ማለት የብረት ዓምዶች የመቁረጥ በቂ ሐይል/ጉልበት ያላቸው የሚፈነዱ መሳርያዎች በሕንጻው ወሳኝ በሆኑ ቦታዎች በልዩ ጥንቃቄ በማጥመድ ሕንጻው ዱካው ስር እንዲወድቅ የሚደረግበት ሳይንስ ነው፡፡ ዴቪድ ዲ. ግሪፈን “ማማዎቹ ከወደሙበት ሂደት ልንረዳው የምንችልውና ተቀባይነት ያለው ግምት (natural assumption) ሊሆን የሚችለው በፈንጂዎች አማካኝነት ከላይ ወደ ታች እንዲወድቁ መደረጋቸው ነው ይለናል፡፡ ይህን ቅድምያ የሚይዘው ግምት ማማዎቹ ከወደሙበት የተለየባሕርይ በመነሳት በተግባር የተመረኮዘ ምርመራ የተደገፈ ነው፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ለሁለተኛው የኦፊሻላዊ ቲዎሪ አብይ እክል የሚሆነው፡፡ ይህም መንትያ ማማዎቹ  የወደሙበት መንገድ፣ የሚፈነዱ መሳርያዎች (explosives) ብቻ ጥቅም ላይ ከዋሉ የሚጠበቁ በትንሹ 11 ሁነኛ መለዮ ባሕርያት(features) ኣሳይተዋል፡፡ እነዚህ ባህርያት ባጭሩ እንደሚቀጥለው ለመቅረብ እንሞክራለን፡፡
1.        ድንገቴ ጅማሮ-Sudden Onset
አንድ ሕንፃ በኮንትሮል ዴሞሊሽን መደርመስ የሚጀምረው በድንገት ነው፡፡ በአንድ ወቅት የማይንቀሳቀስ የነበረው ሕንጻ፣ ቅጽበታዊ በሆነ ሂደት መውደም ይጀምራል፡፡ ብረት ቢግልም በሙቀት ሃይል በድንገት አይታጠፍም አልያም አይቆረጥም፡፡ ስለዚ በእሳት ቃጠሎ ግፊት የወደሙ…ክስተቶች የምንጠቅሳቸው ካሉ (ምንም እንኳን ባይኖርም)…መደርመስ የሚጀምሩት ድንገት ሳይሆን በዝግታ (gradual) ይሆናል፡፡ የጎን ተሸካሚዎችንና(Horizontal beams) “ማሰርያ ምሶሶዎች” (trusses) መርገብ (sag) የሚጀምሩት ቀዋሚ አምዶች ጠንካራ ለሆነ ሃይል በመጋለጥ መታጠፍ ሲጀምሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን የመንትዮች የቪዲዮ ምስል እንደሚያሳየው 16ቋሚ አምዶቹ ምንም ዓይነት የመታጠፍ እና የመርገብገብ ምልክት አያሳዩም-የአውሮፕላን ጥቃት ከደረሰባቸው ወለል በላይ ያሉት ደብሮችም ቢሆኑ፡፡ መንትዮቹ መውደም እስከጀመሩበት ቅጽበት ድረስ ፍጹም እንቅስቃሴ ያልነበራቸው (perfectly motionless) ነበሩ፡፡
2.        ቀጥ ያለ ከላይ ወደ ታች አወዳደቅ-Straight Down
ለሌሎች ሕንጻዎች ቅርብ የሆኑ ረጃጅም ሕንጻዎች ላይ ኮንትሮል ዲሞሊሽን  በሚከናወንበት ወቅት በጣም ወሳኙ ነገር የሚሆነው ከላይ በቀጥታ ወደ ዱካቸው ስር ካልሆነም  ለዱካቸው ቅርብ ወደ ሆነ ቦታ እንዲወድቁ ማድረግ ይሆናል፤ ይህ በመሆኑ ከህንጻው ጎን የሚገኙት ሌሎች ህንጻዎች እንዳይጎዱ/እንዳይወድሙ ያደርጋል፡፡ ይህንን ሂደት የControlled Demolition, Inc. ፕሬዝደንተ ማርክ ሎይዙይክስ (Mark Loizeaux) ሲያብራራ “[አንድ ሕንጻ] እነደፈለግነው አድርገን ከላይ ወደ ታች በፍጥነት በመጣል፤ ከዛ…ምንም ሌላ ስትራክቸር እንዳይጎዳ ለማድረግ ፍንዳታው የግድ “ፍጹም የታቀደ” መሆን ይርበታል፣ ይህ የሚሆነው  “ትክክለኛው የሚፈነዳ መሳርያና ለማፈንዳት ትክክለኛ ንድፍ/ቀመር” በመጠቀም ይሆናል ብሏል፡፡ (Else, 2004) ባለ 110 ፎቅ የሆኑት መንትያ ማማዎቹ ወደ ጎን ቢወድቁ ኖሮ ባካባቢው ያሉት ሌሎች ብዙ ህንጻዎች ላይ እጅግ መጠነ ሰፊ ጉዳት ያደርሱ ነበር፡፡ ይሁንና ህንጸዎቹ ከላይ ወደ ታች ነበር የወደቁት፡፡ በእሳት ተቃጥሎ እንደ ኮንትሮልድ ዲሞሊሽን ፈረሰ የሚለው የኦፊሻል ማብራሪያን ለማመን ተአምር መቀበልን ይጠይቃል፡፡
3.        ነፃ አወዳደቅ የሚያክል ፍጥነት –Almost Free-Fall Speed
በኮንተሮል ዲሞሊሽን የሚወድሙ ህንጻዎች በነጻ አወዳደቅ ሊባል በሚችል ፍጥነት ከላይ ወደ ታች በመውደቅ ነው፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የወለሎቹ ስር ደጋፊዎች እንዲወድሙ ስለሚደረጉ ነው፤ በመሆኑም ከላይ ያሉት ወለሎች ወደታች ሲወድቁ ከስር የሚታገላቸው ሐይል አያጋጥማቸውም፡ ማማዎቹ የተደረመሱበት መንገድ የኮንተሮል ዲሞሊሽን መለዮ ከሆኑት አንዱ የሆነው ነፃ አወዳደቅ ባሕርይ እንደነበራቸው  በተዘዋዋሪም ቢሆን በ9/11 ኮሚሽን ሪፖርት ተገልጸዋል፡፡ ይህም “ደቡባዊ ማማው በ10 ሰከንድ ውስጥ ተደርምሷል” በማለታቸው ነው፡፡ (Kean and Hamilton, 2004, p. 305) የዚህ ሪፖርት ጸሀፊዎች በግልጽ እንደተናገሩት የውድመቱ ፍጥነት ከኦፊሻል ቲዎሪ ማለትም “pancake” theoryተብሎ ከሚታወቀው አይጋጭም በማለት ነበር፡፡ በዚህ  ቲዎሪ መሰረት በአይሮፕላን ግጭት ምክንያት ክፉኛ በመጎዳት የመቋቋም ሃይላቸው ከተዳከመው ወለል በላይ የሚገኙት ወለሎች ከስራቸው ያለው ወለል ላይ መውደቅ በመጀመራቸው፣ ከዛም “ሰንሰለታዊ በሆነ አጸፋዊ ምላሽ ”(chain reaction) በሆነ ወለሎቹ “ከላይ ወደ ታች አንዱን ባንዱ ላይ፣ በላይ በላዩ በመውደቅ” (“pancaked”) ሕንፃዎቹ  ሊደረመሱ ችሏል ይላል፡፡ ይሁንና በወቅቱ የተከሰተው ይህ ከሆነ፣ ብዙ ብረቶች እና ኮንክሪት የነበራቸው የታችኛው ወለል (በጥቃቱ ከተጎዳው ክፍል በታች ያለው አብዛኛው የህንጻው ክፍል) በሚገባ የመቋቋም ብቃት ይኖራቸው ነበር፡፡ ከላይ የነበሩት ወለሎች (አይሮፕላኖቹ ከገጩት ቦታ በላይ)  ከስራቸው ይገኙ የነበሩት ወለሎች ላይ፤ ልክ አንድ ነገር በባዶ አየር ላይ ከላይ ወደ ታች ሊወድቅ  በሚችል ፍጥነት ሊወድቁ አይችሉም (ይህንን ድራማ በቦሊውድ አልያም በጀምሰ ቦንድ ፈልም እንኳ የማይሞከር ነው)፡፡ ማማዎቹ የወደሙበት ሂደት ቪድዮ በህንጻው ውስጣዊ ገጽታ  ይወድቁ የነበሩ ስብርባሪ (rubble) ልክ በውጪ ገጽታ በሚወድቁበት ፍጥነት እንደተደረመሱ ያሳያል፡፡ (Jones, 2006)ዴቪድ ሄለር (Dave Heller) በፊዚክስና በንድፍ-ጥበብ ድግሪ ያለው ግንበኛ ሲሆን እንዲህ በማለት ያብራራል፡-
ወለሎቹ አንዱ ባንዱ ሊደራረቡ አይችሉም፡፡ ሕንጻዎቹ በእጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ነበር የወደቁት፡፡ በዚህ ያህል አጭር ግዜ ውስጥ መሬት ላይ ለመድረስ፤ ሁሉም ወለሎች የግድ በተመሳሳይ ግዜ መውደቅ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ግን እንዴት ይሆናል? [ኮንተሮል ዲሞሊሽን ተብሎ በሚታወቀው ዘዴ]፣ እያንዳዱ የህንጻው ወለል የሚወድመው ከላይ ያለው ወለል ሊገጨው ሲል አከባቢ ባለው ቅጽበት በመሆኑ ወለሎቹ በተመሳሳይ ግዜ እና ነጸ አወዳደቅ በሚጠጋ (virtual freefall) ፍጥነት ለመውደቅ ይገደዳሉ፡፡ (Garlic and Glass6)
4.        አጠቃላይ ዉድመት – Total Collapse
ኦፊሻል ንድፈ ሃሳቡ በበለጠ ግልፅ በሆነ ሁኔታ ተቀባይት እንዳይኖረው ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ በወቅቱ ሕንፃዎቹ የተደረመሱበት መንገድ ሙሉ በሙሉመሆኑ ነወ፡፡ እነዚህ 110 ፎቆች ከጫፍ በተደረመሰ ትንሽ የሕንፃው ክፍል አማካኝነት እንዴት ወደ ስብረባሪ ክምር ሊቀየሩ ቻሉ? እያንዳንዱ ማማዎች በውስጣቸው 47 የመሃል የብረት ቋሚ አምዶች (steel box columns) ይዘዋልና፡፡ በፓንኬክ ቲዎሪ መሰረት የአግድም ብረት ደጋፊዎች (horizontal steel supports)ከቋሚ አምዶች በመላቀቃቸው/በመገንጠላቸው ነው ማማዎቹ ለመውደም የቻሉት ይላል፡፡ ይሁንና በወቅቱ የሆነው ይህ ቢሆን ንሮ፣ አሁንም ቢሆን ማህል ላይ የነበሩት 47 የማሀል ቋሚ አምዶቹ  በነበሩበት ይቆሙ ነበር፡፡ ይህን እክል/እንቆቅልሽ ያስተዋለው የ9/11 ኮሚሽን ሪፖርት በግልጽ የሚታይ መፍትሄ ይዞ ነበር የመጣው፣ እርሱም፡- መካድ፡፡ እያንዳንዱ ማማዎች በውስጣቸው 47 ቋሚ አምዶች እነደነበራቸው መካድ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ “የህንጻዎቹ ውስጣዊ ክፍል ባዶና (ቋሚ አምዶች የሌለበት) ረጃጅም ብረት ዘንግ (hollow steel shaft) ብቻ የነበራቸው ሲሆን፤ በውስጣቸው የአሳንስር እና ደረጃዎች ስብስብ ነበር” ይላል፡፡ (Kean and Hamilton, 2004, 541 note 1)
በተመሳሳይ ሁኔታ የኒስት ሪፖርት ይህንን እጅግ አስቸጋሪ የሆነው እክል በጥበብ ለመያዝ ሞክራል፡- ወለሎቹን ሲደረመሱ ቋሚ አምዶቹን መግፋት ጀመሩ፣ ይህ ደግሞ ወሰን ላይ የሚገኙት ቋሚ አምደቹ (perimeter columns) ሚዛናቸው እንዳይጠብቁ /እንዳይረጋጉ አደረጋቸው ይላል፡፡ ይህን አለመረጋጋት የማሀል ቋሚ ኣምዶች ላይ የስበት ግፊት (gravity load) እንዲጨምር አደረገ፤ ይህም የሆነው የማሀል ቋሚ ኣምዶች መሀል ላይ በነበረው እጅግ የጋለ የእሳት ቃጠሎ ተደክመው ስለነበሩ ሲሆን፤ ይህም፣ ኒስት እንደሚለው፣ የነበረው ሙቀት መጠን 1832°F ሊደርስ በመቻሉና እንዲሁም በወቅቱ የተከሰቱት ቅልቅል ምክንያቶች እንደምንም አጠቃላይ መደርመስ እንዲፈጠር አደርገዋል ይላል፡፡ (NIST, 2005, pp. 28, 143)
ይህንን ሓተታ ሁለት መስረታዊ እክሎች አሉት፡፡ የመጀመርያው ኒስት በህንፃዎቹ ማሀል ክፍልእጅግ የጋለ የእሳት ቃጠሎ ነበረ የሚለው ሙሉ በሙሉ በመረጃ ያልተደገፈ ነው፡፡ ከላይ እንዳየነው የኒስት የራሱጥናት የደረሰበት ግኝት በማንኛውም የማሀል አምዶች (core columns) ላይ 482°F (250˚C) ያህል የሙቀት መጠን እንኳን መድረሳቸው ምንም መረጃ የለም ይላል፡፡ ስለዚ ይህ ቲዎሪ መጀመርያ ካጠናው ከ1350°F  በላይ ግልጽ የሆን ግምታዊ ጭማሪ  አለው፡፡ ሀለተኛው፣ በውቅቱ ተከታታይ የሆነ ክስተቶች (ቅልቅል ምክንያቶች) ተፈጥረው ነበር ብንል እንኳ፣ ኒስት እነዚህ ተከታታይ ክስተቶች ያላቸው ለምን አጠቃላይ መደርመስ ሊፈጥሩ እንደቻሉ ማብራርያ አላቀረበም፡፡ የኒስት ሪፖርት የማሀልና የወስን (perimeter) “ቋሚ አምዶች መውደቅ” አረጋግጫለሁ ይላል፡፡ ይሁንና መግለጫው  በምንም ማብራርያ ያልተደገፈ ባዶ-መግለጫ ነው፡፡ በምን ምክንያት ቋሚ አምዶች ሊቆራረጡ አልያም ሊተጣጠፉ እንደቻሉ፣ በመሆኑም ለነጻ-አወዳደቅ አጠቃላይ መደርመስ ሊያስከትሉ እንደቻሉ ተአማኒነት ያለው  ምንም አይነት አሳማኝ  ማብራርያ አልቀረበም-ኒስት ያለው የሙቀት መጠን  መድረስ ቢችሉ እንኳን፡፡
ሰሜናዊው ማማ በግንባታ ወቅት ላይ እያለ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ሲሆን፤ የሕንፃው የማሃል ክፍል አሰራር በብዙ አግዶሞሽና ተቃራኒ መእዝን የተሳሰሩ ቋሚ አምዶች እንደነበሩት ያሳያል፡፡ ምስል፡ ከ9/11-Review.com
5.        የተቆራረጡ ብረቶች- Sliced Steel
ዙርያ-መለሽ ህንጻዎች ላይ ኮንትሮል ዲሞሊሽን ክንውን በሚደረግበት ወቅት፣ የሚፈነዱ መሳርያዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉት የብረት ቋሚ አምዶችና ተሸካሚ/ደጋፈ ርብራቦች (beams) በመቆራረጥ ወደ ትናንሽ ቁርጭራጭ በመቀየር ይሆናል፡፡ Controlled Demolition, Inc በማስታወቅያ ገፁ ላይ በከፍተኛ ፍንዳታዎች በብዛት ጥቅም ላይ ስለሚውለውRDX ብረት የሚቆርጥበት መንገድን ሲገልጽ “የምላጭ ስለት ልክ ቲማቲም በሚቆርጥበት መንገድ” በማለት ነበር የገለፀው፡፡ በተጨማሪ ብረት የሚቆርጥበት ሂደት ዝምብሎ ሳይሆን ለቁጥጥር የሚመቹ ቁርጭራጭ (manageable lengths) አድርጎ ነው፡፡ ይህም  በControlled Demolition, Inc ማስታወቀያ ላይ “Our DREXSTM systems . . . segment steel components into pieces matching the lifting capacity of the available equipment.”እንደሚለው መሆኑ ነው፡፡ የመንትያ ማማዎች የተደረመሱበት መንገድ ይህን የኮንትሮል ዲሞሊሽን ባህርይ የሚመሳሰል ነበራቸው፡፡ በ2004 ጂም ሆፍማን (Jim Hoffman) የተደመረሰው ቀጠና የተለያዩ ፍቶዎች ላይ ጥናት ካደረገ በኋላ፣ የኮንትሮል ዲሞሊሽን ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
6.        ኮንክሪት እና ሌሎች መሳርያዎች መድቀቅ
ሌላኛው የኮንትሮል ዲሞሊሽን ባህርይ ብዙ አቧራ (dust) መፍጠር ነው፤ ይህ የሚሆንበት ምክንያት ብረትን የመቁረጥ በቂ ሀይል ያላቸው “ፈንጂዎች” ኮንክሪትና ሌሎች ብረት ያልሆኑ ነገሮች/ዕቃዎች በማድቀቅ/በመፍጨት በጣም ትናንሽ ወደሆነ መጠን  መለወጥ ሰለሚችሉ ነው፡፡ ጂም ሆፍማን በ2003 እንደዘገበው “አብዛኛው ብረት-ያልሆኑት የማማዎቹ  ክፍሎች በመድቀቅ ወደ ዱቄት (fine powder) ተቀይረዋል፡፡ ይህንን ግንዛቤ የዩ.ኤስ ሰራዊትኢንጅነር የሆኑት ኮሎኔል ጆን ኦ’ዶውን (Colonel John O’Dowd)ንግግር ላይ ይገኛል፡፡ “በዓለም ንግድ ማእከል ሳይቶች ላይ” ይላል ጆን ኦ’ዶውን ለHistory Channel ሲያብራራ “የነበረው ሁሉም ነገር የደቀቀ(pulverized) ይመስላል፡፡ (History Channel, 2002) በማለት ነበር የተናገሩት፡፡ ይህንን እውነታ በወቅቱ የነበረው ብቸኛው ሓይል ስበታዊ ሓይል (gravitational energy)ነው ለሚለው ኦፍሻላዊው ቲዎሪ እክል ይፈጥራል፡፡
7.        የአቧራ / ጭስ ክምችት – Dust Clouds
ሌላኛው የኮንትሮል ዲሞሊሽን ባህርይ አቧራ/የጭስ -ደመና መፍጠር ሲሆን፣ ይህንን አቧራ/ጭስ የሚፈጠረው፣ ድማሚቶቹ ሲፈነዱ አቧራውን/ጭሱን በከፍተኛ ጉልበት ከህንፃው ገፍትረው ስለሚያስወጡት ነው፡፡ ማንም ሰው ቪድዮውን በኢንተርኔት በማየት ማነፃፀር የሚችለው ማማዎቹ ሲደረመሱ ያመነጩት ደመና ሌሎች ህንፃዎች (structures) በኮንትሮል ዲሞልሽን ካመነጩት የአቧራ/ጭስ ደመና በጣም ተመሳሳይ መሆናቸው ነው – እንደስያትል ኪንግደም እንደመሳሰሉት ህንፃዎች፡፡ ብቸኛው ልዩነት የሚሆነው ማማዎቹ ሲደረመሱ ያመነጩት ደመና በአንፃራዊ በጣም ትልቅ የነበረ በመሆኑ ነው እዚህ ጋር ወደ አቧራ የመጨረሻ መጠን ለመቀየር የሚስፈልገው የሓይልምንጭ የሚለው ጥያቄ በድጋሜ የሚነሳ ይሆናል፡፡ በ2003 ላይ ሆፍማን በሰሜናዊው ማማ በተስፋፋው የጭስ-ደመና (dust cloud) የሚስፈልገው የሃይል መጠን ያሰላው ሲሆን—ይህ ስሌት ብረቱን ለመቁረጥ እንዲሁም ኮንክሪትና ሌሎች መሳርያዎች ለመድቀቅ የሚያስፈልገው ሓይል ሳይጠቃለል ሲሆን—ግኝቱ ታዲያ በሰሜናዊው ማማ የተስፋፋው ጭስ-ደመና ከነበረው ስበታዊ ሓይል (gravitational energy)በትንሹ 10 እጥፍ የሚልቅ ሓይል ነበር፡፡ ስለዚህ የኦፊሻላዊው መግለጫ፣ መጠነ ሰፊ የሆነ የፊዚክስ ሕግጋት ጥስት በውስጡ ይዛል— (ብረቱን ለመቁረጥ የሚያስፈልገው ሓይል ይቅርና) ኮንክሪትን ለማድቀቅ (to pulverize the concrete) የሚስፈልገው የሓይል መጠን እንደመመዘኛ አድረግን ብንወስድ እንኳን እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የፊዚክስ ሕግጋት ጥስት እናገኛለን፡፡
8.        ወደጎን ገፍትሮ/አፈትልኮ መውጣት – Horizontal Ejections
ሌላኛው የኮንትሮል ዲሞሊሽን ባህርይ ያደቀቀውን  አቧራ/የጭሱን-ክምችት ውጪ ሌሎች ህንፃው ውስጥ ይገኙ የነበሩ ዕቃዎች፤ ፈንጂዎቹ በፈነዱበት አከባቢ ወደ ጎን/ደጅ ማስፈንጠር ባህርይ ነው፡፡ በማማዎቹ የነበረው ክስተት የሚያሳዩት ፎቶዎችና ቪዮዮዎች በሁሉም አቅጣጫ በተከታታይ የብረት ቁርጭራጭ ከማማዎቹ እስከ 500 ጫማ የሚደርስ ርቀት ላይ ተገፍትረው ይወጡ/ይወድቁ የነበረ ሲሆን፤ በአንፃሩ “የአልሚንየም ሽፋኖች” (aluminum cladding)ከማማዎቹ እስከ 700 ጫማ ርቀት ድረስ ይፈነዱ ነበር፡፡ (Paul and Hoffman, 2004, p. 7)
ህንፃው በሚፈራርስበት ሰከንዶች ውስጥ የህንፃው ጫፍ ወደ አመድ ክምረ ተቀይሮ 50 ጫማ በሰከንድ እየተወነጨፈ ከህንፃው ክፈፍ ውስጥና ውጪ ሲከንፍ ነበር፡፡
ይህ የሚያሳየው የፈረሰው የህንፃ ክፍል ህንፃውን ሊጥለው እንደማይችል ነው፡፡
9.        “የውድመት” ቀለበቶች – Demolition Rings
ሌላኛው በፍንዳታ አማካኝነት የሚደረመሱ ሕንፃዎች ላይ የሚኖር የተለመደ ባህርይ የውድመት ቀለበት ሲሆን ይህም አነስተኛ የሆኑ ተከታታይ ፍንዳታዎች በፍጥነት በአንድ ህንፃ ሲከናወን ይሆናል፡፡ ይህንን ባህርይ ማማዎቹ የተደረመሱበት መንገድ ላይ የተንፀባረቀ ነበር፡፡ ቪድዮዎች ጋዜጠኞችና ሌሎች የቀረፁትን ከኢንተርኔት ማየት ይቻላል፡፡
10.     ከፍንዳታ የመነጩ ድምፆች
ህንፃዎች ለማፈንዳት ጥቅም ላይ የሚውሉት ፈንጂዎች ሲፈነዱ የፍንዳታ ድምፅ ያስተጋባሉ፡፡ ከላይ ካየናቸው ባህርይዎች፣ የህንፃው ውስጣዊ የብረት ቋሚ አምዶች መቆራረጥከሚለው ውጪ፣ ይህንን ባህርይ እንደ ሌሎቹ በተግባር በአይን እማኞች የተረጋገጠ ነው፡፡ እነዚህ ድምፆች ማማዎቹ ከተደረመሱት በፊት ሆነ በኋላ መከሰታቸው ብዙ እማኞች ቃላቸው ሰጥተዋል፡፡
11.     የቀለጡ ብረቶች
የብረት ቋሚ አምዶች ለመቁረጥ የሚፈነዱ መሳርያዎች ጥቅም ላይ ከዋለ ብቻ የሚጠበቅ አስራ አንደኛ ባህርይ የሚሆነው የቀለጠ ብረት ሲሆን ይህንኑ ባህርይ በዓለም ንግድ ማእከል ሳይት እንደነበረ ብዙ የአይን እማኞች ተናግረዋል፤ (ግራውንድ ዜሮ ላይ የነበሩት የሕንፃው ቅሪቶችን) በማፅዳት ዋና ተዋናዮች የነበሩት የTully Constructionፕሬዝደንት ፒተር ቱለይ (Peter Tully) እና የControlled Demolition, Inc ፕሬዝደንት ማርክ ሎይዚአክስ ይገኙበታል፡፡ ቱልይ እንዳለው “በግልፅ የቀለጠ ብረት (literally molten steel)” ስብስብ በስፍራው (ማማዎቹ የተደረመሱበት በታ) እንዳየ ተናግሯል፡፡ (Bollyn, 2004)ሎይዚአክስ ከ9/11 ክሰተት ብዙ ሳምንታት ባኋላ እንደተናገረው  የህንፃው ሸክላዎቹ ከህንፃው እንደተወገዱ “የጋለ ሽፍታ ያላቸው የቀለጡ ብረቶች” በማማዎቹ የአሳንሰር ዘንጎች ስር፣ ከህንፃው ምድር ቤት[basement]  ሰባተኛው ላይ” አግኝተናልበማለትተናግሯል፡፡ (Bollyn, 2004)  
የመንትያ ማማዎች ዲዛይን ከሰራው የኢንጅነሮች ድርጅት አባል የሆነው ሌዝሊ ሮበርትሰን (Leslie Robertson) ሕንፃዎች ጥቃት ከደረሰባቸው 21 ቀናት በኋላም የእሳት ቃጠሎው ይቃጠል የነበር ሲሆን፤ ብረትም እንዲሁ ይቀልጥ ነበር ብሏል፡፡ የKnight-Ridderጋዜጠኛ ጀኒፈር ሊን (Jennifer Lin)ከጥቃቱ ባኋላ ለብዙ ወራት በማዳንና በማፅዳት ተጠምዶ የነበረው የእሳት ተከላካይ ወታደር ጆ “ቱሌ” ኦ’ቱሊ(Joe “Toolie” O’Toole) ጋር ውይይት ካደረገች በኋላ እንፃፈችው “ከምድር ቤቱ ስር የነበሩ እሳት ቃጠሎዎች ለወራት ይቃጠሉ ነበር፡፡ ኦ’ቶሊ በየካቲት ላይ፣ ክሬን ጥልቅ ከሆነው ግራውንድ-ዜሮ መካነ-መቃብር(catacombs) ውስጥ የብረት ተሸካሚ(steel beam) ወደ ላይ ሲያወጣ እንደተመለከት በማስታወስ ይወጣ ከነበረው የብረት ተሸካሚ “የቀለጠው ብረት (የብረት ተሸካሚ) ይንጠባጠብ ነበር ያለው፡፡ ሌላኛው የሰው አካል ቅሪት መኖሩ የሚለይ የኮምፒተር መሳርያዎች ያቀርብ የነበረው የsales for LinksPoint, Inc.,ም/ፕሬዝደንት ግሬክ ፉቼክ(Greg Fuchek) በስፍራው የነበረ የስራ ሁኔታ “ሊታገሱት የማይችሉት(“hellish”) በማለት ነበር የገለፀው፤ የዚህ ምክንያቱ በከፊል ለስድስት ወራት የሚያክል ምድርቤቱ ላይ የነበረው ሙቀት ከ600°F -1500°F እና በላይ በሆነ መጠን ይለዋወጥ ስለነበር ነው፡፡ በተጨማሪ “አንዳንድ ጊዜ ሰራተኞቹ ከስብርባሪው ውሰጥ የብረት-ርብራብ(steel beam) በሚጎቱትበት /በሚስቡበት ወቅት በብረት-ርብራብ የመጨረሻ አካል ላይ የቀለቱ ብረቶች ይንጠባጠቡ ነበር” ይላል፡፡ (Walsh, 2002) ከዚህ በተጨማሪ አሁንም ስለ ቀለጡ ብረቶች በተመለከተ የተናገሩ ብዙ እማኞች ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ እማኞች ንግግር ትልቅ ትርጉም አላቸው፤ ምክንያትም ከከባድ ፍንዳታዎች (high explosives) ውጪ ብረቶቹ ሊቀልጡ የቻሉበት ሌላ መንገድ ይሄ ነው ብሎ ለማሰብ በጣም ከባድ ስለሚሆን ነው፡፡ በነዳጅ ሊሆን እንደማይችል አይተነዋል፡፡
የምስክሮች ቃል
በ9/11 ለት ባደጋው ቀጠና አካባቢ ከነበሩት ሰዎች ማለትም፡በዜና ዘጋቢዎች፣ የእሳት አደጋ ተከላካይ ወታደሮች፣ ፖሊስ መኮንኖች፣ በማማዎቹ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ታዋቂ የፍንዳታ ባለሞያ የሆነው ቫን ሮሜሮ (Van Romero)ምስክር ከሰጡት ይጠቀሳሉ፡፡ ቫን ሮሜሮ ማማዎቹ በተደረመሱበት እለት ቪደዮውን ከተመለከተ በኋላ የወደሙበት ሂደት የሚመስለው በኮንትሮል ዴሞልሽን የሚፈጠሩ ዓይነት ብቻ አይደለም፣ ይልቁንስ  የግድ የተወሰኑ የሚፈነዱ መሳርያዎች (explosive devices) በሕንፃው ስር  በማጥመድ የፈነዱ መሆን አለባቸው ይላል፡፡ (Uyttebrouck, 2001)(ከግዜ በኋላ እንደ ሌሎች የሙያ አጋሮቹ የደረሰበት ጫና ቃሉን እንዲቀይር ቢያደርገውም፡፡) ይሁንና ይህ አጠቃላይ የፍንዳታ አመለካከት በሚገርም ሁኔታ የተቀየረበት አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ይህም የNew York Fire Department ከ500 የሚበልጡ የቃል/እማኞች ታሪኮች በወቅቱ ቀድቶ የነበረ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ እሳት አደጋ ተከላካይ ፈጥኖ ደራሾች (firefighters) እና የድገተኛ ጊዜ የህክምና ሰራተኞች ማማዎቹ በተደረመሱበት እለት የነበረው ሁኔታ የገለፁበት ይገኝበታል፡፡ ይሁንና የከንቲባው የብሉምበርግ አስተዳደር እነዚህ የተቀዱ ታሪኮች ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በዚህ ወቅት የቁንጮዎቹ መፅሄት ዘ ኒውዮርክ ታይምስ (ከህዝቡ “ጫና ሲበዛበት”) በዛ ያሉ የ9/11 ጥቃት ሰለባ የሆኑትን ቤተስቦች ጋር በመሆን ክስ በመመስረት ረጅም የሆነ ፍርድ መንገድ ከተጓዙ ባኋላ በመጨረሻ የኒውዮርክ ፍርድ ቤት በቃል የተቀዱት ታሪኮች/ሬከርዶች እነዲለቀቁ ውሳኔ ሰጠ፡፡ ይህ የሆነው በሐምሌ 2005 ነበር፡፡ ከዚህ ባኋላ ነበር የተቀዱ የቃል ታሪኮች ኒው ዮርክ ታይምስ ለሕዝብ ይፋ ያደረጋቸው፡፡
እነዚህ የቃል ታሪኮች በጣም ብዙ እማኞች ማማዎቹ ሲደረመሱ ፍንዳታዎችና የኮንተሮል ዴሞሊሽን የሚመስሉ ባህርያት እንደነበሩ የተናገሩት የያዙ ናቸው፡፡ ቀጥለን የተወሰኑትን እንመልከት፡-
የፍንዳታ-ድምፆች
ከመደርመሳቸው በፊት ከፍ ያለ ፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ ባካባቢው ይመሰክራሉ፡፡ ጦር አዛዥ ሻለቃ ጆን ሳድኒክ (Battalion Chief John Sudnik) “ከፍተኛ የሆነ የፍንዳታ ድምፅ የሚመስል …ከሰማን በኋላ ማየት ጀመርን፤ ማየት በምንጀምርበት ቅፅበት ሁለተኛው ማማ (WTC-2) ቁልቁል መውደቅ ሲጀምር ለማየት ቻልኩኝ፡፡” (NYT, Sudnick, p. 4) ፓራሜዲክ ኬቨን ዳርነውስኪ (Paramedic Kevin Darnowski)“ሶስት ፍንዳታዎች ሰማሁኝ፣ ከዛ ባኋላ…ማማ ቁጥር ሁለት ቁልቁል መውደቅ ጀመረ” ነበር ያለው፡፡ (NYT, Darnowski, p. 8) የእሳት አደጋ ተከላካዩ ቶማስ ቱሪሊ (Thomas Turilli) “ልክ ድማሚቶች ሲፈነዱ የሚያሰሙት ድምፅ ይመስል ነበር፤ ሰባት ወይም ስምንት ጊዜ ቡም፣ቡም፣ቡም የሚል አይነት ነበር”በማለት ተናግራል፡፡ (NYT, Turilli, p. 4)ክሬግ ካርልሰን (Craig Carlsen)እንዳለው እሱና ሌሎች የእሳት አደጋ ተካላካይ ወታደሮች ከደቡባዊው ማማ …የሚመጣ የፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ ….ወደ አስር የሚጠጉ ፍንዳታዎች  እንደፈነዱና… ከዚህ በኋላ ሕንፃውን መውደቅ እንደጀመረ ለመገንዘብ ቻልን” ብለዋል፡፡(NYT, Carlsen, pp. 5-6) የእሳት አደጋ ተካላካይ ጆሴፍ ሚኦላ (Joseph Meola) “ሕንፃው በሁሉም አራቱ አቅጣጫዎች የፈነዳ ይመስላል፡፡ በእርግጥ የ“ፍንዳታ ድምፆች” ሰምተናል፡፡”(NYT, Meola, p. 5) በተጨማሪ፣ የጤና ረዳት ዳኒኤል ሪቬራ (Paramedic Daniel Rivera)የ“ፍንዳታ ድምፆች” (“pops”) እንደሰማ ይናገራል፡፡ ደቡባዊው ማማ እንዴት ሊወድቅ/ሊደረመስ እንደቻለ ሲጠየቅ-እንዲህ ይላል፡- “እጅግ በጩኸት የተሞላ ነበር፡፡ የመጀመርያ ግምቴን የነበረው…የዴሞሊሽን ባለሞያ የሆኑት-እርግጠኛ በሆኑ ወለሎች ላይ ፈንጂዎች ሲያጠምዱና ከዛ ባኋላ የሚፈጠረው ፓፕ፣ፓፕ፣ፓፕ፣ፓፕ… የሚል ድምፅ ሰምተው ያውቃሉ?…ይሄው ነበር መጣ ያልኩት፡፡” (NYT, Rivera, p. 9)
ጥቃት ከተፈፀመበትና ቃጠሎ ከነበረበት ቦታ በታች የጀመረው መደርመስ
እንደ 9/11 ኦፊሻላዊ መግለጫ “አንዱ ወለል ባንዱ ላይ መውደቅ” “pancaking” የጀመረው በአውሮፕላን ጥቃት ምክንያት ክፍት ከሆነው ወለል በላይ ያሉት ወለሎች ከስራቸው የሚገኙት ወለል ላይ በመውደቃቸው ነው ይላል፡፡ ይሁንና፣ አንዳንድ የዓይን እማኞች እንደተናገሩት የደቡበዊ ማማ መደርመስ የጀመረው በአውሮፕላን ጥቃት ከደረሰበት ወለል ትንሽ ዝቅ ብሎ ነው ይላሉ፡፡ ቲሞቲ ቡርኬ(Timothy Burke) “ሕንፃው የፈነዳው፣ እሳቱ ከነበረበት በታች ሲሆን…ለሁለተኛ ጊዜ ሲፈነዳ የእግዜር ያለህ ነበር ያልኩት፡፡ ይህ ነገር ድማሚት መሆን አለበት ነበር ያልኩት፡፡ (NYT, Burke, 8-9)
የእሳት አደጋ ተካላካይ ወታደር ኤድዋርድ ካችያ Edward Cachia“በእርግጥ የፈነዳው በታችኛው ወለል ላይ እንጂ አውሮፕላን ከገጩው ወለል ላይ አልነበረም… በመጀመርያ የመሰለን ልክ ከውስጥ የሚፈነዱ ድማሚቶች ነው ምክንያቱም ፍንዳታው በተከታታይ “ቡም”፣ “ቡም”፣ “ቡም” የሚል ድምፅ በማሰማት በመጨረሻ ማማው ሊደረመስ ችሏል” ብሏል፡፡ (NYT, Cachia, p. 5) የእነዚህ ግንዛቤ አስፈላጊነት በኒስት ሪፖርት ጎልተው ይታያሉ፡፡ የሪፖርቱ ረቂቅ ለሕዝብ በተለቀቀበት ወቅት ቀጥሎ ያለው ዓ.ነገር በማጠቃለያ ፅሑፉ ይገኛል፡- ኒስት የዓለም ንግድ ማእከል ማማዎቹ በኮንትሮል ዲሞሊሽን፣ ከመስከረም 11፤ 2001 በፊት በተጠመዱ ድማሚት አማካይነት ነው የተደረመሱት ለሚለው አማራጭ መላምት ምንም ማረጋገጫ አላገኝም… ከዚህ ይልቅ/ በምትኩ፣ ከተለያዩ አቅጣጫ ፎቶዎችና ቪድዎች በግልፅ እንደሚያሳዩ መደርመስ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ ከተከሰተባቸው ቦታና ግጭት ከደረሰባቸው ወለሎች ክፍል ላይ ሲሆን፤ ከዚህ ወለሎች ወደ ታች ወድመቱ እድገት እያገኘ ለመምጣት ችሏል ይላል የኒስት የክህደት ቃል፡፡ እዚህ ጋር የእሳት አደጋ ተከላካይ ወታደሮች ብርኬና ካችያ ምናልባት ራሳቸውን ሊጠይቁት የሚፈልጉት ጥያቄ፡- ማንን ነው የሚያምኑት፣ ዓይንዎን ወይስ አፊሻላዊ የመንግስት (ሴረኞች) ሪፖርት? የሚለውን ይሆናል፡፡
ብልጭታና ውድመቱ ያስተጋባው ድምፅ – Flashes and Demolition Rings
በወቅቱ ስለ ብልጭታና የፍንዳታ ቶክስ ክስተት ጠቋሚዎች እንደነበሩ የተናገሩ የአይን እማኞች ይገኛሉ፡፡ ረዳት ኮሚሽነር ስቴቨን ግሪጎሪ“ቁጥር 2 መደርመስ ከመጀመሩ በፊት ዝቅተኛ መጠን ያላቸው ብልጭታ አየሁኝ…ብልጭ፣ ብልጭ፣ ብልጭ የሚል በታችኛው የሕንፃው ክፍል ተመለከትኩኝ፡፡ ልክ ሕንፃዎች የሚወደሙበት መንገድ ይመስላል፡፡ ካፕቴን ካሪን ዴሾር “በሕንፃው መካከለኛ ክፍል አከባቢ… ብርቱካንና ቀይ ቀለም ያለው ብልጭታ (flash) ከውስጥ ለጥቆ ይወጣ ነበር፡፡ ሲጀመር አንድ ብልጭታ ብቻ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ይህ ብልጭታ በሁሉም የሕንፃው ክፍል  በአጭር ፍንዳታ ድምፅ መታጀብ ሲጀምር ሕንፃው መፈንዳት የጀመረ ሲሆን…ይህም እያንዳንዱ ፍንዳታ ድምፅ ማሰማት ሲጀምር ብርቱካንማ ከዛም ቀይ ብልጭታ ከሕንፃው የወጣ ሲሆን፣ በመቀጠል እኔ ማየት እስከቻልኩበት ድረስ በሁለቱም የሕንፃ ሁለመና ገፅታ ላይ ይሰራጭ ነበር፡፡ እነዚህ የፍንዳታ ድምፆች፣ ድምፃቸው በእጅጉ እየጨመረ  ሲመጣ፤ ከላይ ሆነ ከታች እየተስፋፉ በመጨረሻ በሁሉም የሕንፃው ክፍል ለመዝመት ቻሉ፡፡” ይላል፡፡ (NYT, Deshore, p. 15) የእሳት አደጋ ተካላካይ ወታደር ሪቻርድ ባናሲስኪ (Richard Banaciski)እንዲህ ይላል “በወቅቱ ፍንዳታ ነበር፡፡ እነዚህ ፍንዳታ፤ ሕንፃዎች በቴሌቪዥን ምስል ላይ በፈንጂ አማካኝነት የሚወድሙ ይመስል ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ የፍንዳታ ድምፆች፣ ልክ በማሰርያ/መቀነት ሁለመና ዙርያው ላይ የሚካሄዱ ይመስሉ ነበር፡፡” (NYT, Banaciski, 3-4) ምክትል ኮሚሽነር ቶማስ ፊትዝፓትሪክ (Thomas Fitzpatrick)፡- “የሚያንፀባርቀው/ የሚያብለጨልጨው በአንድ የተወሰነ የሕንፃው ወገን (layer) ዙርያ ላይ ይመስል ነበር…የመጀመርያ ምላሼ የነበረው እነዚህ ክስተቶች በትክክል በቴሌቪዥን እንደሚታዩ የፍንዳታ (implosions) ትእይንቶች ይመስላሉ የሚል ነበር፡፡” (NYT, Fitzpatrick,13-14)
አግድማዊ (ጎንዮሽ) ማፈትለክ – Horizontal Ejections
አግድማዊ ማፈትለክ በማስመልከት ምስክርነት የሰጡ እማኞች ይገኛሉ፡፡ ቺፍ ፍራንክ ክሩዘርስ (Chief Frank Cruthers)“በወቅቱ የታየ…ፍንዳታ ነበር፡፡ ፍንዳታው የተከሰተው በሕንፃው የላይኛው መጨረሻ ክፍል ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ከአራቱ የሕንፃው ክፍል ‘የተለያዩ ቁሳቁሶች’ (materials)በአግድሞሽ አፈትልከው ሲወረወሩ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ የሕንፃዎቹ መውደም ከመጀመሩ በፊት ለአጭር ጊዜ የዘገየ ሂደት ነበር፡፡”(NYT, Cruthers, p. 4)  ይህ ማስረጃ ፋይዳው ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም ኦፊሻላዊው ቲዎሪ እንዲህ መወርወር የተፈጠረው ወለሎች በደርመሳቸው ነው በማለት ስለሚያስተባብል ነው፡፡ እስቲ የእሳት አደጋ ተከላካይ ወታደር ጄምስ ኩራን (James Curran) የሚለውን እናስብበት፡- “ወደ ኋላ ተመለከትኩኝ ከዛ…ልክ ሁሉንም ወለሎች ቹ…ቹ…ቹ በሚል ድምፅ መሰል ታጅበው ፈነዱ፡፡ እንደገና ስመለከት ከነበረው ጠንካራ ግፊት (pressure) የተነሳ ሕንፃው ከመደርመሱ በፊት ከወለሎቹ ላይ ይገኙ የነበሩ ማናቸውም ነገር እየፈነዱ ይወጡ ነበር፡፡” (NYT, Curran, pp. 10-11) የጦር ሻለቃው ቺፍ ብርያን ዲክሰን “በታችኛው ደቡባዊ ታወር የበታች ወለል ላይ የነበረው የእሳት ቃጠሎ የሆነ ሰው ፈንጅ ያጠመደበት ነበር የሚመስለው፣ ምክንቱም …ሁሉም ነገር በዚሁ [በዙርያው] ወለል ላይ ነው የፈነዳው፡፡” New York Times, Dixon, p. 15)
በጥምረት  (እኩል እንዲፈነዳ) የተካሄደ ስራ –Synchronized Explosions
ፍንዳታው በጥምረት በአንድ ግዜ እንዲፈነዳ ስለመደረጉ አንዳንድ የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ የእሳት አደጋ ተካላካይ ወታደር ኬንዝ ሮጀርስ (Kenneth Rogers)“በደቡባዊው ታወር ላይ ፍንዳታ ነበር…መመልከቴን ቀጠልኩን፡፡ አንዱ ወለል ቀጥሎ ካለው ወለል፤ ይህም ወለል ቀጥሎ ካለው ወለል፣ ከዛም ከስሩ ካለው ከዛም ተከታዩ ወለል በመከታተል…ሆን ተብሎ በጥምረት በአንዴ እንዲፈነዱ የተደረገ ይመስላል፡፡” (NYT, Rogers, pp. 3-4)
እነዚህ ንግግሮች ለምንድነው ሕዝቡ ያላወቃቸው?
እነኚህ ሁሉ የእሳት አደጋ ተካላካይ ወታደሮችና የሕክምና ሰራተኞች በወቅቱ የነበሩ ክስተቶች መንስኤ ኮንትሮል ዴሞሊሽን መሆኑን የሚጠቁሙ ንግግሮች እስካሁን ድረስ ለምን የዓለም ሕዝብ እንዳላወቃቸው ሊደንቃቹ ይችላል፡፡ ይሁንና፣ የዚህ መልስ የእሳት አደጋ ተካላካይ ረዳት መቶ አለቃ ፓውል አይዛክ (Auxiliary Lieutenant Fireman Paul Isaac) ይነግረናል፡፡ አይዛክ “በእርግጠኝነት በሕንፃዎቹ ውስጥ ድማሚት ነበር” ይላል፤  አይዛክ በመቀጠል “ሌሎች ብዙ የእሳት አደጋ ተካላካይ ስራተኞች በህንፃው ውስጥ ድማሚት እንደነበሩ ያውቃሉ፤ ሆኖም ግን ስራቸውን ላለማጣት ሲሉ አምነው ለመቀበል ወኔ ያጣሉ፤ ምክንያቱም “ከላይ ያሉት” ይህንን እውነታ የተመለከት ሓሳብ እንዳይንሸራሸር ይከለክላሉና፡፡” (Lavello, n.d) ሌላኛው መልስ የሚሆነው ጥቂት ሰዎች እንደ አይዛክና ዊልያም ሮድሪጌዝ ዓይነቱ የተናገሩት ንግግር የመገናኛ ብዙሃን ለመዘገብ ፍቃደኛ ስለማይሆኑ፣ ውድቅ ይደረግባቸዋል፡፡
የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ መደርመስ፡ የሴራው ሌላኛው ፈተና
“ሁለት ሲጋጩ፤ ሶስት ወደቁ – ትልቁ ውሸት” ሊይን ማርገሊስ
ይህን ፅሁፍ በስፋት ዴቪድ ሬይ “ግሪፍን፡ “The Mysterious Collapse of  World Trade Center 7: Why the Final Official Report about 9/11 Is Unscientific and False” ከሚለው የመረጥነው ሲሆን ሌላ ተጨማሪ ከወሰድን ይጠቀሳል፡፡ በ9/11 ጥቃት ውስጥ ከዓለም ንግድ ማእከል ሕንፃዎች አንዱ የሆነው የዓለም ንግድ 7 ሕንፃ (Building 7 / World Trade Center 7) 5:21 PM ላይ ፈረሰ፡፡ ይህ 47 ፎቆች ያሉት ግዙፍ ሕንፃ ሳይነካ ሙሉበሙሉ የፈረሰበት ሂደት አስገራሚ ክስተት ነው የነበረው፡፡ የዚህ ህንፃ መደርመስ በሚድያ የተሰጠው ሽፋን እጅግ እጅግ አናሳ ነበር-ይህም ከተሰጠው ነው፡፡  የዚህም ምክንያት ሽፋን ከተሰጠው በአልቃይዳ የተጠለፉ አይሮፕላኖች ከማማዎቹ በመላተማቸው የፈጠሩት ግፊትና አይሮፕላኖቹ ውስጥ የነበረው “ነጭ-ጋዝ” (Jet fuel) በመቀጣጠሉ ነው መንትዮቹ የፈረሱት የሚለው ኢ-ሳይንሳው አፊሻላዊ የመንትያ ማማዎቹ ቲዎሪ ተቀባይነት ስለሚያሳጣው ነው፡፡
ቅጥረኛ ኢንጂነሮች የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ ለምን ተደረመሰ ለሚለው ጥያቄ ምንም መልስ የላቸውም፡፡ ለዚህም ነው በነበረው ክስተት የተደመመው የNational Science winner አሸናፊዊው ሊይን ማርገሊስ (Lynn Margulis) ሁኔታው “ሁለት ሲጋጩ፤ ሶስት ወደቁ-ትልቁ ውሸት” – “Two hit, three down-the biggest lie” በማለት ክስተቱን የገለፀው::(Rock Creek Free Press, January 24, 2010 )
የዓለም ንግድ ማእከል 7 መፍረስን ማብራራት ለምን ዳገት ሆነባቸው?
1.        ታይቶ የማይታወቅ ክስትት
አንዱ ምክንያት የዓለም ንግድ ማእከል 7 በመፍረሱ የ9/11 ኦፊሻል መግለጫው በዚህ በምናውቀው ፍጥረት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ ህንፃ በእሳት አደጋ እንደ ሰም ቀለጠ የሚል የማይታመን ዘገባ ስለያዘ ነው፡፡ በብረት-ክፈፍ የተሰራ ሰማይ ጠቀስ ህንፃ? ነጭ ውሸት፡፡ ሳይንስ በዚህ ዘገባ ፊቷን አዙራ ወደ ሌላ አቅጣጫ ትመለከታለች እንጂ ይህ የቁሳዊ ህግን የጣሰ መግለጫ አትቀበልም፡፡ በፊዚክስ ፒ.ኤች.ዲ ያለው የኒውዮርክ ታይምስ ፀሐፊው ጄምስ ግላንዝ  (James Glanz) ሊሆን እንደማይችል የተናገረበትን ፅሁፍ ዘግቧል፡፡ ግላንዝ አንድ ስተራክቸራል ኢንጅነር በማጣቀስ ”በስትራክቸራል ኢንጅነሪንግ ክፍል/ዘርፍ፣ የዓለም ንግድ ማእከል 7 ለመረዳት በበለጠ አሰፈላጊ ነው [ከመንትየ ማማዎቹ ይልቅ] ”ምክንያቱም “ለምን  የዓለም ንግድ ማእከል 7 ወደቀ?” ለሚለው ጥያቄ ኢንጅነሮች መልስ የላቸውምና፡፡” ብሏል፡፡
2.        በምስልየተደገፈየፍንዳታማስረጃ
የዚህ ሕንፃ ከላይ ወደ ታች የተደረመሰበት መንገድ ነፃ አወዳደቅ ሊባል በሚችል (Virtual free fall) የነበረ ሲሆን፣ የሕንፃው አወዳደቅ “implosion,” ተብሎ የሚታወቀው የኮንትሮል ዴሞሊሽን ዓይነት ምሳሌ ሲሆን፣ ይህም ድማሚቶና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች የሕንፃዎቹ ቋሚ የብረት ደጋፊዎችን በመቁረጥ ሕንፃው ዱካው ስር እንዲወድቅ የሚደረግ ክንውን ነው፡፡ከዚህ ብዙዎች ከመሰከሩለት ትእይንት በተለይ በ2006 አንድ ፈልም ሰሪ በኔዘርላንድ የኮነትሮል ዴሞሊሽን ድርጅት ባለቤት የሆነው ዳኒ ጆዊንኮ (Danny Jowenko) መላምት ሳያስቀምጥ የህንፃ7መደርመስ የሚያሳየው የቪድዮ ምስል ላይ አስተያየት እነዲሰጥበት የተጠየቀው ይገኝበታል፡፡ የሚገርመው ምንም እንኳ በዘርፉ ሰፊ እውቀት ቢኖረውም ጀዊንኮ ይህንን ጥያቄ እስኪጠየቅ ድረስ፣ ልክ እንደተቀረው አብዛኛው የዓለም ህዝብ ስለዚህ ሕንፃ መደርመስ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ጆዊንኮ የቪዲዮ ፊልሙን ከተመለከተ በኋላ “ይህ የተከናወነው ቋሚ ዓምዶቹ በቀላሉ እንዲሰበሩ በማድረግ ሲሆን፣ በመቀጠል በቀላሉ የተቀረውን ተከትሎ እንዲወድቅ ሆነ … ይህ ኮንትሮል ዴሞለሽን ነው፡፡” ብሎ መልሶለታል፡፡ ኮንትሮል ዴሞለሽን እንደሆነ በእርግጠኝነት ሲጠየቅ “በመፈንዳት እንደተከናወነ ሙሉለመሉ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ይህንን በቅጥር የተከናወነ (hired job) ስራ ነው፡፡ ይህን የሰራው የባለሞያዎች ቡደን ነው” በማለት በልበ ሙሉነት ይ ናገራል፡፡ (Danny Jowenko on WTC 7 Controlled Demolition YouTube)
3.        ፍንዳታ እንደነበረ የተናገሩት ምስክሮች  
በውቅቱ ፍንዳታ ይሰማ እንደነበረ የተናገሩ ምስክሮች  ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ የNew York City’s corporation counsel እና በወቅቱ የኒው-ዮርክ ከንቲባ የነበሩት ሩዲ ጁሊያኒየቅርብ ጓደኛ ማይክል ሄስ ይገኝበታል፡፡ አደጋው በተከሰበት ቀን  ከጥዋቱ 11፡57 ላይ ሄስ ወደ ከተማው መሰብሰብያ አዳራሽ እየሄደ እያለ ቃለመጠየቅ ለመስጠት ይቆማል፣ በዚህቃለመጠይቅ ሄስ ምስክርነቱን ሰቷል፡ “23ኛው ፎቅ ወደ ሚገኘው the emergency management center (WTC 7) ላይ ነበረኩኝ፤ በሕንፃው ውስጥ ሁሉም በታ መብራት ሲጠፋ፤ አንድ ሰውና እኔ ፍንዳታ ወደ ነበረበት ስምንተኛ ፎቅ ወረድን ከዛም እዛው ስምንተኛ ፎቅ ላይ በጭስ-ቀጭን ጭስ ለአንድ ተኩል ሳዓታት ዙርያችን በሙሉ ተከበን ነበር፡፡ ይሁንና፣ እሳት አደጋዎች ደረሱልንና ለመውጣት በቃን፡፡Èይህ ማለት ፣ሄስ በጠዋት አጋማሽ ላይ የዓለም ንግድ ማእከል 7 ፍንዳታ ዘግቦ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ሌላኛው፣ ከሄስ የነበረው ሰው የከተማው ቤቶች አስተዳደር ሰራተኛ ቤሪ ጀኒንግስ (Barry Jennings) ሲሆንበተመሳሳይሁኔታመንገድላይቃለመጠይቅሲቀርብለትየሰጠውመልስሄስ ከተናገረው ቃል ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህም እሳቸው እና ሚር.ሄስ “ትልቅ በሆነ ፍንዳታ” ሲከበቡ ደረጃውን አንድ በአንድ መውረድ እንደጀመሩ ተናግሯል፡፡ ጄኒንግስ በተጨማሪ ከአደጋው የሚያተርፋቸው አካል እስኪያገኙ ድረስ ፍንዳታው ድምፅ ይቀጥል እንደነበረ ተናግሯል፡፡ ሌላው ከሰዓት ረፋድ ላይ፣ ልክ የዓለም ንግድ ማእከል 7መውደቅ በሚጀምርበት ወቅት የፍንዳታ ድምፅ በተመለከተ የቀረቡ ዘገባዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህ ውስጥ የNew York Daily News ሪፖርተር ፒተር ዲማርኮ ነበር፡፡ የከተማዋ ፖሊስኦፈሰር  ክሬይግባርቲመር (Craig Bartmer) “የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሲወድቅ በጣም በቅርብ ነበርኩኝ …አንድ ሕንፃ ወደ እኔ እንደሚወድቅ  ዓይነት ስሜት  አልነበረም የተሰማኝ…በወቅቱ የፍንዳታ ድምፅ የሰሙ ብዙ ምስክሮች ከስር በቅርብ ነበሩ…በድንገት…ተመለከትኩኝ፣ ከዛ…ነገርየው በራሱ ሰዓት ከፍተኛ የሆነ የፍንዳታ ድምፅ  ማሰማት ጀመረ…መሮጥ ጀመርኩኝ …ከዚህ በኋላ ሙሉበሙሉ የምትሰማው ‘ቡም፣ቡም፣ቡም፣ቡም’ የሚል ድምፅ ነው፡፡”
4.        አካላዊ ማስረጃ፡- የስዊዝ-አይብ ብረት / Swiss-Cheese Steel:
9/11 በተከሰተ በጥቂት ወራት ውስጥ ከዎርስስተር ፖሊቴክኒክ ኢንስቲትዩት (Worcester Polytechnic Institute /WPI) የመጡ ሶስት ፕሮፌሰሮች ከህንፃ 7 ስለመጣ ቁራጭ ብረት ላይ የሰሩት ሪፖርት አስደናቂ ነበር የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢዎች ጄምስ ግላንዝ እና ኤሪክ ሊፕቶን ሚስጥሩን ሁላ የፈታው ብለውታል፡፡ በህንፃው የነበረው እሳት ብረት ለማቅለጥ በሚችልበት ሁኔታ ባይግልም ብረቱ ግን የቀለጠ ነበር፡፡ ሌላው እንቆቅልሽ በብረቱ ያሉ አተሞች ከሰልፈር ጋር ተቀላቅለው ነበር ይህ መቀላቀልም በዝቅተኛ ሙቀት እንዲቀልጥ የሚያደርግ ሳይንስ ውጤት ነው፡፡ ሌላ ሪፖርቱን በስፋት የተነተነ ዘገባ ብረት በይዘቱ እንዲኮማተር/እንዲጨማደድ የሚያደርግ የብረቶች ማዋሃድ ጥናት (metallurgical studies) ጠንካራ የብረት ቋሚን (ፌሮን) እንደ ስዊዝ አይብ ማኮማተር…አንድ ኢንች ቋሚን ወደ ግማሽ ኢንች ማድቦልቦል እንደሚቻል ይጠቁማሉ፡፡ የተጠማዘዘና የተሰባበረ ብረት የጠበቁት የእሳት ጠበብት ፕሮፌሰሮች እንደ ስዊዝ አይብ ተኮማትሮ የተበሳሳ በረት ማየታቸው አስገርሟቸዋል፡፡ ቀዳዳው በሳልፈሩ የሚፈጠር ሲሆን አንደኛው ፕሮፌሰር እንዳለው ዋናው ጥያቄ እንዲህ ለማድረግ ምን ያህል ሳልፈር ያስፈልጋልና ማን አመጣው የሚል ነው? ይላል፡፡ (Joan Killough-Miller, “The ‘Deep Mystery’ of Melted Steel,” WPI Transformations, Spring 2002 )ብረትን እንደጧፍ የሚያቀልጠውና ያላካተትነው እንደ ፈሳሽ የሚያተነውን ሳይንስ በዝርዝር መዘገብ የራሱ መፅሃፍ ስለሚያስፈልገው በዚሁ ይብቃን፡፡
5.        በግልፅ የሚታይ ማስረጃ
ከነዚህም ሌላ የዓለም ንግድ ማእከል 7 የተደረመሰውበእሳትምክንያት ነው የሚለው ኦፊሻላዊው መግለጫ እውነት እንዳልሆነ በ2002 በFEMA አማካኝነት የወጣው  የዚህ ሕንፃ የመጀመርያው ኦፊሻዊ ሪፖርት ላይ እናገኘዋለን፡፡ በተጨማሪ በWPI ፕሮፌሰሮች ከዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ የተገኘው የብረት ቁራጭ ቅሪት ባደረጉት ጥናት ላይ እናገኘዋለን፡፡ በመጨረሻ፣ የFEMA ረፖርት (የመጀመርያው ኦፊሻላዊ ሪፖርት) የፃፉት ኢንጅነሮች የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ መደርመስ አስመልክተው ያቀረቡት “ምርጡ መላምታቸው” (“best hypothesis”) ሲያቀርቡ ያመኑት ነገር ቢኖር በተግባር “የመሆን እድሉ በጣም ትንሽ የሆነ” (“only a low probability of occurrence.”) መሆኑን ነው፡፡
በስፋት እንዳይታወቅ የገጠመው እከል
በግንቦት 2006 Zogby pollባደረገው የድምፅ ስብሰባ መረጃ መሰረት 43% የኤሜሪካ ሕዝብ (ምናልባትም 95% የዓለም ሕዝብ) የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ እንደወደመ አያውቅም፡፡ ከነዚህ ውስጥ የሚካተተው ከላይ ያየነው የኮንትሮል ዴሞሊሽን ባለቤት ኔዘርላንዳዊው ዳኒ ጀዌንኮ ስለዚህ ሕንፃ መውደም ምንም ዓይነት እውቀት አልነበረውም ምንም እንኳን ኮንትሮል ዴሞሊሽን የተሰማራበት የስራ ዘርፍ ቢሆንም፡፡ መልሱ ሊሆን የሚችለው የዚህ ሕንፃ ታሪክ ሆን ተብሎ እንዳይታወቅ በመደረጉ ነው የሚል ይሆናል (የዚህ ሕንፃ አወዳደቅ ተብጠርጥሮ ይቅርና በወፍበረር እንኳ ትእይንቱ ሽፋን አላገኘም፡፡) ይህ ድምዳሜ ቀጥለው በሚቀርቡ እውነታዎች የተደገፈ ነው፡፡
የመጀመርያ፡- ከ9/11 ጥቃት በኋላ የቲቪ ኔትዎርኮች በተደጋጋሚ ያሳዩ የነበሩ መንትያ ማማዎቹ በአይሮፐላን ሲገጩ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ብቻ ነበር፡፡ በአንፃሩ የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሽፋን ያገኘው ከስንቴ አንዴ ቢሆን ነው-እሱም ከታየ፡፡
ሁለተኛው፡- በ2004 የ9/11 ኮሚሽን ሪፖርት ሲወጣ፣ የዓለም ንግድ ማእከል 7 ስለ መደርመሱ የጠቀሰው ምንምነገር የለም፡፡
ሶስተኛው፡- ኒስት -the National Institute of Standards and Technology (NIST)የዓለም ንግድ ማእከል መደርመስ የማብራራት (የማጣራት) ሂደቱ ከFEMA ከተረከበ በኋላ የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሪፖርት በተደጋጋሚ እንዲዘገይ አድርጎታል፡፡ ኒስትበ2003 የዚህ ሕንፃ ሪፖርት ከመንትያ ማማዎች ጋር በጋራ እንደሚወጣ፤ ረቂቅ ሪፖርቱ ደግሞ  በ2004 እንደሚቀርብ ተናግሮ ነበር፡፡ ይሁንና በተባለው ቀን ሪፖርቱን ማቅረብ ባይችልም በ2005 ኒስትየዓለም ንግድ ማእከል 7 ሳያካትት የመንትዮቹ ማማዎች ሪፖርቱን አወጣ፡፡ በመቀጠል ኒስት የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሪፖርት በ2006  አቀርባለሁ አለ፡፡ ሓምሌ 2006 ቢደርስም አሁንም ረፖርቱ ሊቀርብ አልቻለም፡፡ይልቁንስ “የዓለም ንግድ ማእከል 7 ረቂቅ ሪፖርት 2007 መጀመርያ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል” በማለት ኒስት ማራዘሙን ቀጠለበት፡፡ አሁንም በ2007 በመጀመርያ ይሁን በመጨረሻ ወራት ላይ ሊቀርብ አልቻለም፡፡ “የዕቃ-ዕቃ ጨዋታ” ይመስል በታህሳስ  2007 ላይ ኒስት ረቂቅ ሪፖርቱ ሐምሌ 8፣ 2008 የመጨረሻ ሪፖርቱ ነሐሴ 8፣ 2008 ተጠናቆ እንደሚቀርብ እንደገና ገለፀ፡፡ ይሁንና አሁንም እንደተለመደው በሐምሌ 8፣ 2008 ረቂቅ ሪፖርቱ አልቀረበም፤ የመጨረሻ ሪፖርቱም ቢሆን እስከ ሕዳር 2008 አልወጣም፡፡ በዚህ ወቅት የቡሽና ዲክ ቼኒ አስተዳዳር የስልጣን ጊዜውን ጨርሶ ለመልቀቅ የሚሰናዳበበበት ወቅት ነበር፡፡
በ2008 የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሪፖርት እንዲዘገይ የተደረገው ሆንተብሎ ነው የሚለው ውንጀላ እያየለ የመጣበት ወቅት ነበር (ቀድሞውኑ የ9/11 Truth Movement ህንፃ 7 ለአፊሻዊው 9/11 መግለጫ ‘የእግር ቁስል’ (Achilles Heel) ወይም ወንጀሉ እጅ ከፈጅ የሚያስረግጥ (Smoking Gun) ማስረጃ ነው ካለው ቆይተል፡፡ ይሁንና ኒስት በመዋሸት የዓለም ንግድ ማእከል 7 ምርመራ ስራ የጀመርኩት ከ2005 ሲሆን፤ በስራው የቆየሁት ለ3 ዓመታት ብቻ ነው፤ ይህ ማለት ደግሞ የመንትየ ማማዎች ሪፖርት ለማቅረብ ከወስደብኝ ጊዜ ተመሳሳይ ነው በማለት ግልፅ በሆነ ውሸት ለማስተባበል ሞከረ፡፡ እውነታው ግን ኒስት የዓለም ንግድ ማእከል 7 በተመለከተ በሂደት ላይ የነበሩ ነበሩ የተጠናከሩ ሪፖርቶች (progress reports)በታሕሳስ 2002 እና በግንቦት 2003 ነበሩት፡፡ ይህ ብቻ አልነበረም ኒስት በ2004የዓለም ንግድ ማእከል 7 አስመልክቶ ጊዚያዊ ሪፖረት (Interim Report) ያሳተመ ሲሆን፣ ከዚህ በመቀጠል  በጥቅምት2005 የዓለም ንግድ ማእከል 7 አስመልክቶ የመጀመርያ ሪፖርት(preliminary report)ያወጣበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ነበር ኒስት በዓለም ንግድ ማእከል 7 ላይ ስራውን ያቆመው፣ ይህም በጥቅምት 2005 የመንትያ ህንፃዎች ሪፖርት እስካወጣበት ድረስ ነበር ለ6 ወራት ያህል መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ኒስት “በዓለም ንግድ ማእከል 7 መደርመስ የሚደረገው ምርመራ እንደገና ጀመሯል” ነበር ያለው፡፡ ስለዚህ እውነታው ኒስት በህንፃ 7 ሪፖርት ለመቅረብ የወስደበት ጊዜ 3 ዓመት ሳይሆን 6 ዓመት የሚጠጋ ነው፡፡ ይህ ሪፖርት በተቻለ መጠን ሆንተብሎ ነው እንዲዘገይ የተደረገው ብሎ ለመጠርጠር በቂ መክንያት ነበር፡፡
ኒስት በሪፖርቱ ሁሉንም ማስረጃዎችና ምስክሮች ያልተጠቀመ ከመሆኑም በላይ የሌለ ማስረጃም ፈጥሯል ለምሳሌ በህንፃው በደጋፊ ብረት የሚገናኙ መቆለፍያዎች/ ማሰርያዎች አልነበሩም በማለት፡፡ (No Girder Shear Studs)  በተጨማሪም ኒስት በ2004 የዓለም ንግድ ማእከል 7 ሕንፃ አስመልከቶ ባወጣው ጊዝያዊ ሪፖርቱ ላይ በ4:45 PM “በ12ኛው ወለል በእሳት ወድመዋል፣” የሚል ቢሆንም፤ በ2008 ሪፖረት መግለጫው ላይ በ5:00፤ ሕንፃው ከመደርመሱ 21 ደቂቃ በፊት በዚህኛው ወለል (12ኛው) የነበረ የእሳት ቃጠሎ አሁንም በሃይል ይቀጥል ነበር ይላል፡፡ በተጨማሪም ኒስት የህንፃ 7 አወዳደቅ እንደ ነፃ አወዳደቅ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ለዚህም ምክንያቱን መፍጠር ስለሚያስቸግርና በኮንትሮል ዲሞሊሽን ነው ብሎ ማመን ደሞ ደሞዝ ስለሚያስከለክል ኒስት ይህ “ስለዚ ተአምር ተፈጥሮ መሆን አለበት፡፡” / “Then a miracle happens.”ብሎ ሲያጓትት የነበረውን ሪፖርት ቋጭቶታል፡፡
የዚህ እንደምታው 
ከዚህ በመነሳት፣ በተዘዋወሪ መንትየ ማማዎቹ በተመሳሳይ መንገድ መደርመሳቸው መቀበሉን ያመለክታል፤ ምክንያቱም መንትያ ማማዎቹ በተደረመሱበት ወቅት የነበሩት የተደበቁ የኮንተሮል ዴሞሊሽን ምልክቶች በአብዛኛው በዓለም ንግድ ማእከል 7 በተመሳሳይ ሁኔታ በመኖራቸው ነው፡፡ በመንተያ ማማዎቹ በተጨማሪ ቋሚ የብረት አምዶች በአግድሞሽ አፈትልከው ከማማዎቹ 500 ጫማ በላይ በሚደርስ ርቀት ላይ ተገፍትረው ይወጡ ነበር (እነዚህ ማፈትለክ የተፈጠሩት ሕንፃው መደርመስ በሚጀምርበት ወቅት ሲሆን ከዚህ በኋላ ነበር ህንፃዎቹ ከላይ ወደታች የወደቁት፡፡)ይህ የሚያመላክተው የተከሰተው ውድመት የኮንትሮል ዴሞሊሽን መሆኑን ነው፤ ኒስት የአልቃይዳ 9/11 ቲዎሪ ለመፈተሽ ትኩረት አይሰጥበትም፡፡ ለምን?
መጀመርያ፡- የመንትያ ማማዎቹና ህንፃ 7 ከላይ ወደታች የወደቁበት የኮንትሮል ዴሞሊሽን ዓይነት ለሆነው “ኢምፕሎሽን” (“implosion”)ክንውን በአልቃይዳ አሸባሪዎች የተተገበረ ነው ሊባል እንደማይቻል ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ሁለተኛ፡- ህንፃዎቹ የዋይትሃውስ ፈጠራ የሆኑት አሸባሪዎች ቢጥሏቸው ወደ ጎን ወድቀው በዙርያው ለሚያደርሱት ውድመት ግድ አይላቸውም በር፡፡ ሆኖም ግን በዝቅተኛ ውድመት ከፍተኛ ቀውስ ማድረስ የፈለጉ ባካባቢው ጥቅም የነበራቸው የውስጥ አዋቂ ቁንጮዎች እንዳደረጉት ነው የኮንትሮል ዲሞሊሽኑ መጨመር የሚያመላክተው፡፡
ሶስተኛው፡- ሶስተኛውመመለስ ያለበት ጥያቄ የውጭ አሽባሪዎች ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እና ድማሚቶ ሕንፃዎቹ ላይ ለማጥመድ የሚፈጀው ብዙ ሰዓታት የማግኘት እድል አይኖራቸውም (እዚህ ጋር ፈንጂዎቹ የሚጠመዱት በሱማልያ፣ አፍጋኒስታን ወይም ፓኪስታን ዋሻዎች ሳይሆን በኤሜሪካ ያዉም በዓለም ንግድ ማእከል ሕንፃዎች ላይ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይህንን ሊያከናውኑት የሚችሉት የውስጥ አዋቂወች ብቻ ናቸው፡፡ ለዚህም ዌብስተር ግሪፊ ታርፕለይ Webster Griffin Tarplay : 9/11 Synthetic Terror Made in USA መፅሃፍ ላይ እንደጠቀሰው በሰፊ የእድሳት ስም ከጥቃቱ ሳመንታት በፊት በህንፃው ውስጥ እንግዳ እንቅስቃሴ የታዘቡ ሰዎች እንደመሰከሩ ልብ ይሏል፡፡ ጠንካራው ምስክርነት የመጣው በ9/11 እለት 87 ሰራተኞቹ ከሞቱበት የFiduciary Trustነው፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ በመስከረም 8-9 ከ50ኛው ወለል በላይ የሃይል መቋረጥ አጋጥሞ ነበር፣ ለ36 ሰዓታት መብራት አልነበረም፡፡ በኦፊሻል የተሰጠው ምክንያት የሃይል መስመሩ እድሳት እየተደረገለት ነበር የሚል ነው፡፡ የFiduciary Trustኮምፒውተሮች ሃላፊነት የተሰጠው የአይቲ ሙያተኛው ፎርቤስ የኮምፒተሮቹ ደህንነት ስለሚያሳስበው በሃይል መቋረጡ ግዜ ስራ በዝቶበት ስለነበር በደንብ ያስታውሰዋል፡፡ ከ50 ፎቅ በላይ መብራት በመጥፋቱም የደህንነት ካሜራዎችና ደህንነት ቁልፎች አይሰሩም ነበር፡፡ ከዚህም በላይ በሳምንቱ መጨረሻ ለት የደጅ የምህንድስና ሙያተኞች በስፋት በህንፃው ሲመላለሱ ነበር፡፡ ፎርቤስ የዓለም ንግድ ማእከል ሕንፃዎች ከቤቱ ሁኖ የሚታዩት ሲሆን ሲቃጠሉ ባያቸው ግዜ ወድያው ካለፈው ሳምንት መገባደጃ እንግዳ ገጠመኞች ጋር ነበር ያስተሳሰረው፡፡ (www.serendipity.li/wot/ forbes01. htm ታርፕሌ ላይ እንደተጠቀሰው፡፡)
ፔንታጎን-ላይ የደረሰው ጥቃት ያስነሳው ጥያቄ
9/11 ኮሚሽን እስከ 9፡36 ድረስ (ጥቃቱ ከመፈፀሙ ትንሽ ደቂቃ በፊት) አውሮንፕላንዋ ወደ ዋሽንግተን እየመጣች እንደሆነ ማንም አያውቅም ነበር ይላል፡፡ ይሁንና፣ በትንሹ ወደ ፔንታጎን ከመጠጋትዋ 10 ደቂቃ በፊት ስለጥቃቱ ያውቁ እንደነበር የሚገልፅ፤ ይህም ም/ፕሬዝደንት ዲክ ቼኒ ከሌሎች ባለስልጣኖች ጋር በመሆን ዋይትሃውስ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ (shelter conference room) ንግግር ያደርጉ እንደነበር  የሚያሚሳይ  የትራንስፖርት ሴክረተሪ ኖርማን ሚነታ (Norman Mineta) ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ምንም እንኳ ግልፅ በሆነ ማስረጃ ለኮሚሽኑ የኖርማን ሚነታ ሪፖርት ቢደርሰውም፤ በኮሚሽኑ ሪፖርቱ ወስጥ ግልፅ በሆነ መንገድ እንዳይካተት ተደርገዋል፡፡ አንዱ አከራካሪው ጥያቄ ፔንታጎን ጥቃት የደረሰበት ኦፊሻላዊ መግለጫ እንደሚለው የእውን በአሜሪካን አየር መንገድ በረራ 77 (American Airlines Flight 77)ነው የሚለው ነው፡፡ ዳኒኤሌ ኦብራያን (Danielle O’Brien)የተባለው አየር ትራፊክ ሙያተኛ የሰጠውን ቃል ከላይ የጠቀስነው የዌብስተር ታርፕለይ መፅሃፍ ይጠቅሰዋል፡ “ፍጥነቱ፣ ያካሄድ ዘዴው (ጀብዶው)፣ የተጠመዘዘበት ሁናቴ፣ እዛ ራዳር ክፍል ውስጥ የነበርን በጠቅላላ ወታደራዊ አየር ነው ብለን ነው ያሰብነው፡፡” በፔንታጎን ጥቃት ዙርያ ያለተፈቱ እንቆቅልሾች አሉ፡-
መጀመርያ፡- የኤሜሪካ ዋና ከተማ ድንገትከተዋጊ ጄቶች ሊሰነዘርባት ከሚችለው ጥቃት ለመከላከል፣ በየቀኑ በትንሹ ሶስት የአየር ሓይል ቡድኖች (squadrons) ይዞ የአሜሪካ ደህንነት ሁል ጊዜ በተጠንቀቅ ከሚጠብቀው አንድሬውስ የአየር ሓይል መቀመጫ በቅርብ ማይልስ ርቀት የሚገኝ በመሆኑ ነው፡፡ እርግጠኛ እንድንሆን የኦፊሻላዊው ክፍል የሆነው አንዱ መግለጫ በዛን ሰዓት አንድሬውስ አየር ሓይል በተጠንቀቅ የሚጠብቁ ምንም ዓይነት የሚከላከሉ ተዋጊ አልነበሩም ይላል፡፡ ይሁንና ይህ ውሸት ሙሉለሙሉ የማይታመን ነው፡፡ ( 9/11 CROD, 159-64.)
ሁለተኛ፡- የኤሜሪካ ጦር ሓይል በአለም ላይ ምርጥ የሆነ የራዳር ሲስተም አለው፡፡ ከሲስተሞቹ አንዱ “በኤሜሪካ አየር ላይ የሚያንዣብብ/የሚፈጠር ማናቸውም ነገር አያመልጠዉም፡፡” ከዚህ በተጨማሪ ይህ ሲስተም በተመሳሳይ ወቅት ለሚከሰቱ ብዙ ቁጥር ያላቸው ጥቃት አላማ ውስጥ በማስገባት በአንዴ የመቆጣጣር ብቃት እንዳለው ይነገርለታል -ይህም የተወንጫፊ መሣርያ ጥቃት(massive missile attack) ዐይነቱ በሚያጋጥም ወቅት አስፈላጊ ስለሚሆን ነው፡፡ (Thierry Meyssan, Pentagate (London: Carnot, 2002), 115, quoting “PAVE PAWS, Watching North America’s Skies, 24 Hours a Day” (www.pavepaws.org)ይህንን ዓቅም ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በአሸባሪዎች ወደ ፔንታጎን የበረረችው በረራ ቁጥር 77 ለ40 ደቂቃ የሚያህል ግዜ አልታየችም የሚለው ኦፊሻላዊ መግለጫ አሳፋሪ ነው፤ በተለይ ደግሞ የፔንታጎን አስተዳደር (የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር መቀመጫ) አገሪቱ በጥቃት ስር መሆንዋ እውቀት በነበራቸው ሳዓት መሆኑ እራሳቸው ከመሰከሩለት የራዳር ሲስተምስ አቅማቸው ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ ወደ ፔንታጎን የሚመጣ ማናቸውም እውቅና ያልተሰጠው በራሪ ነገር (ሚሳይልም ሆነ ወታደራዊ ወይም ሲቪል አየር) ወድያውኑ ገና ወደ ሕንፃው ከመጠጋቱ በፊት በርቀት እያለ ይለይ (detected)እና ይጨናገፍ/ይያዝ (intercepted) ነበር፡፡
ሶስተኛው፡- ፔንታጎን የታጠረው በከባድ ፀረ-ሚሳይል መሣርያዎች(anti-missile batteries) ሲሆን፣ እነዚህ ፀረ-ሚሳይል ዓላማቸውከአሜሪካ የጦር ሓይል እውቅና ውጪ የሚገቡ ማናቸውም አይሮፕላን ለማውደም ነው (Thierry Meyssan, 9:11: The Big Lie (London: Carnot, 2002), 112, 116. )፡፡በረራ ቁጥር 77 በሆነ አጋጣሚ እንኳን ወጥመዱን አልፋ ወደ ፔንታጎን የአየር ክልል ብትገባ፣ ከመመታት ልታመልጥ የምትችልበት አጋጣሚ የሚኖረው ፔንታጎን ላይ በነበሩ የስራ አመራሮች ፀረ-አውሮፕላኑ መከላከያ እንዳይሰራ ከተደረገ (deactivated)ብቻ ይሆናል፡፡ከነዚህ በተጨማሪ ኦፊሻላዊው መግለጫ እንዳንቀበለው የሚደርጉን ብዙ ምክንያቶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ፡-
·      ኮሚሽኑ አወዛጋቢው ፔንታጎንን የገጨው በረራ ቁጥር 77 አይሮፕላን ትመራ የነበረችው በሃኒ ሃንጆር (Hani Hanjour) ነው የሚለው ማንንም አላስማማም፡፡ የፔንታጎን ሕንፃ ምዕራባዊ ክንፍ ለይቶ ለመግጨት ወደታች ተጠማዞ በመሄድ ከመሬት በዝቅተኛ ርቀት  መምታቱ በጣም ብቁ ለሆኑ ፓይለቶች እንኳ የሚከብድ ነው፤ ሃንጆር ደግሞ በጣም ደካማ ፓይለት እንደሆነ ላጭር ግዜ በረራ ያስተማሩት መመስከራቸው ይታወቃል፡፡ ይህንን እውነታ በመላ ለመያዝ በአንዳድ የሪፖርቱ ገፆች ሃንጆር ችግር እንዳለበት የሚገልፅ ሲሆን (The 9/11 Commission Report ,225-26, 242) በተቃራኒው በሌላ የሪፖርቱ ገፆች ይህንን የስራ ድርሻ ለሃንጆር የተሰጠው ምክንያት “ተልእኮውን ሊወጣ የሚችልና ከሁሉም የላቀ ልምድ ያለው ፓይለት” ስለሆነ ነው ይላል፡፡ (The 9/11 Commission Report ,530n147) ባጭሩ ሃኒ ሃንጆር ያለምንም መረጃ ነው የተወነጀለው፡፡
·      አሸባሪዎች ከፍተኛ የሆነ የሰው እልቂትና ውድመት ለማድረስ ቢፈልጉ ኖሮ፣ የፔንታጎን ምዕራባዊ ክንፍ የመጨረሻ ምርጫቸው ይሆን ነበር፡፡ ይህ ክፍል በእድሳት ላይ የነበረ በመሆኑና በጥቃቱ የደረሰባቸው በውስጡ ይገኙ የነበሩት ወታደራዊ ሳይሆን ተራ የቀን ሰራተኞች ነበሩ፡፡ በተቀራኒው እንደፈጠራው የአሸባሪዎች አቅምና እውቀት ቢሆን ኑሮ በእርገጠኝነት የሚፈለጓቸው የመከላከያው ሚኒስትሩ ራምስፊልድ እና ሌሎች የፔንታጎን የበላይ ሽማምንቶችን ያነጣጥራሉ እንጂ ከላይ እንዲታይ ለእድሳት በሚል በትልቁ ምልክት የተደረገበትን ዒላማ አያደርጉም ነበር፡፡
·      ሌላኛው እክል ገጨ የተባለው አየር -ቦይንግ 757- የታለ የሚለው ነው፡፡ ከአደጋው በኋላ ወድያውኑ በአይን ምስክሮች እንደተገለፀውና የተነሱ ፎቶግራፎች እንደሚያሳዩት (ማለትም እንደማያሳዩት) ጠረጴዛና ወረቀት ተርፎ የተጋጨው ቦይንግ 757 አውሮፕላን ቅሪት ምኑም አልታየም፡፡
·      አውሮፕላንዋ ፔንታጎን ላይ ባለው ፀረ አውሮፕላን ራዳር ሲስተም አለመመታትዋ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር ፔንታጎን ላይ የተጋጨችው አውሮፕላን  የዩ.ኤስ.  ጦር ሃይል ንብረት መሆንዋን ነው፡- እነሱ ብቻ ናቸውና የማይመቱት፡፡
·      ፔንታጎን ላይ ጥቃት የፈፀመችው አውሮፕላን የእውነት ቦይንግ-757 መሆንዋን ወይም አለመሆንዋን የሚያሳዩ ቪድዮዎች አሉ፤ ይሁንና ከጥቃቱ በኋላ የነዚህ ቪድዮ ይዞታ መብት በብቸኘነት ኤፍ.ቢ.አይ እንዲይዛቸው ተደርጓል፡፡ ለህዝብም ይፋ አልተደረጉም- ለምን? ምክንያቱም ቪድዮዎቹ ፔንታጎን የመታው በራሪ ነገር ትክክለኛ ማንነት ስለሚያሳዩ ነዋ!
·      በጥቃቱ ግዜ ፔንታጎን ከሁሉም በላቀ መልኩ የተጠበቀ ቦታ መሆን ነበረበት ግን በ9፡43 AM ሲመታ በረራ ቁጥር 11 ግንኙነት ካቋረጠች (ከተጠለፈች) አንድ ሰዓት ከሃያ ዘጠኝ ደቂቃ በኋላ ወይም ሰሜናዊ ማማውን ከመታችው ከ57 ደቂቃ በውኋላ ነበር፡፡ የእውነት ምን እያሰቡ ነው ይህ ሊደርስባቸው የቻለው?
ተጨማሪ ጥያቄዎች
ብዙ ሃገሮች አሜሪካ ላይ ለመፈፀም እየታሰበ ስላለው ጥቃት መረጃ ሰጥተው ነበር፡፡ ሽብር ጥቃቱን ፈፅሟል የተባለው አልቃይዳን በማስጠለል የተወረረው ሃገር አፍጋኒስታን ሳይቀር የሽብር ሴራውን ለአሜሪካ መንግስት አሳውቆ ነበር፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረው ዋኪል አህመድ ሙታዋኪል(Wakil Ahmad Muttawakil) መልእክተኛ ልኮ ፓኪስታን ለሚገኝ የአሜሪካ ቆንፅላ ፅ/ቤት መረጃውን አስተላልፎ ነበር፡፡ ዛሬ ለዚህ ምግባሩ በማሰቃያ እስር ቤት ውስጥ እየማቀቀ ይገኛል፡፡ (Paul J. Watson: Order Out of Chaos)
ሌላው የጥቃቱ ለት የጦርነት ጨዋታዎች (war games) የሚባል የእውን የሽብር ጥቃት ቢፈፀም እንዴት አፀፋዊ ምላሽ እንደሚሰጡ የደህንነት ሃይሎች የተግባር ስልጠና ሲያደርጉ ነበር፡፡ መጀመርያ የጥቃቱ ለት የተግባር ልምምድ አልነበረም ተብሎ ቢካድም ካመት በኋላ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ የፀረ-ሽብር ሃላፊ የነበረው ሪቻርድ ኤ. ክላርክ (Richard A. Clarke) አምኖ ተቀብሏል፡፡ የተግባር ልምምዱ ከእውነተኛው ጥቃት ጋር በመደባለቅ ብዙ መደናገሮችን ፈጥሯል፡፡ ፶ አለቃ ላውሮ “ኤልጄ” ቻቬዝ (Army Sgt. Lauro “LJ” Chevez)የ9/11 ለት የተግባር ልምምድን በተመለከተ በሂወቱ ጥብቅ ሚስጥር በሚል የተሳተፈበት ብቸኛው ልምምድ መሆኑን ተናግሯል፡፡ (Jim Marrs: Above Top Secrete) ፶ አለቃው በዚህ አላበቃም ም/ፕሬዚደንቱ ዲክ ቼኒ በእለቱ የልምምድ መርሃ ግብር ከነበራቸው የደህንነት ተቋማት አንዱ የሆነው የNORAD [North American Aerospace Defense Command] ሃላፊ የሆነ የመጀመርያው ሲቪል እንደነበር አስታውቋል፡፡ (Jim Marrs: Above Top Secrete) ዲክ ቼኒ የNORAD የመጀመርያው ሲቪል ሃላፊ የሆነው ከ9/11 ጥቃት ከሳምንታት በፊት ነበር፡፡ በልምምዱ ወቅት የራዳር ንባቡ ላይ ያልተጠለፉ አውሮፕላኖች እንደተጠለፉ ተደርጎ እንዲታይ ይደረጋል፣ ይህ ከእውነተኛው የተጠለፉ አውሮፕላኖች ጋር ግጭት ሲፈጥር ነበር፡፡ የተጠለፉ አውሮፕላኖችን በመከታተል እርምጃ ለሚወስዱ ጀቶች ደሞ እንዳይቀሳቀሱ ትእዛዝ ተላልፎ ነበር፡፡ (Jim Marrs: Above Top Secrete) የ9/11 ኮሚሽኑ ሪፖርት ስልጠናዎቹን በግርጌ ማስታወሻ ጠቅሶ ብቻ ያልፋቸዋል፡፡ የሬድዮ ግንኙነት ያቋረጠ ወይም የተጠለፈ አየር አጃቢ ጀቶች ተልከውለት የሚሰጠውን ትእዛዝ የማይፈፅም ከሆነ የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት አየር ላይ እያለ ይመታል፡፡ ይህ ደንብ በጥቃቱ ለት ያልተተገበረበት ዋናው መነሻ ልምምዶቹ የፈጠሩት መደናገር በጥቃቱ ለት የአሜሪካ አየር ሃይል ሽባ ሁኖ የዋለበትን ምክንያት ያብራራል፡፡
ኤፍ.ቢ.አይ በአየር ጠለፋው ተጠያቂ ካደረጋቸው 19 ሰዎች መሃከል ቢያንስ ሰባቱ በሂወት ተገኝተዋል፡፡አብዱል አዚዝ ኦማሪ የተባለው ዴንቨር ላይ ፓስፖርቱ እንደተሰረቀበት አስታውቆ ነበር፡፡ ሳዒድ አል ጋምዲ የተባለው የሳውዲ አየር ፓይለት የነበረው ከጠላፊዎቹ ስሙ መጠራቱ በጣም እንዳበሳጨው ተናግሯል፡፡ ሳሌም አል ሃምዚ ወደ አሜሪካ ሂዶ እንደማያውቅ ተናግሯል፡፡ አህመድ አል ጋምዲ የበረራ ቁጥር 93 ጠላፊ የተባለው ፔንስለቫንያ የሚባል ቦታ ሰምቼም አላውቅም ብሏል እንኳን እዛ ሂዶ አየር ሊጠልፍ ይቅርና፡፡ ዋሊድ አል ሸህሪ ከሞሮኮ ሁኖ ንፅህናው እንዲታውቅለት በሂወት እንዳለ አሳውቋል፡፡ አብዱልራህማን አል ኦማሪ የዩ.ኤስ. ኢምባሲ በመሄድ ንፅህናው እንዲታወቅለት አመልክቷል፡፡ አሚር ቡካሪ የተሰኘው ከ9/11 ጥቃት በፊት ሂወቱ እንዳለፈች የሃሰት መመርመርያ መሳርያ (ፖሊግራፍ) ፈተና ያለፈው ወንድሙ መስክሯል፡፡ የነዚህ ሰዎች ቃል በሳውዲ ዓረቢያ መንግስት የተረጋገጠ ነው፡፡
በሰኔ 2006 የኤፍ.ቢ.አይ የምርመራ ውጤቶች ህትመት ሃላፊ የሆነው ሬክስ ቶምብ (FBI Chief of Investigative Publicity Rex Tomb)እንደገለፀው፡ “ኦሳማ ቢን ላደን በጥብቅ የሚፈለግ የሚለው ገፁ ላይ 9/11 ያልተጠቀሰበት ምክንያት ኤፍ.ቢ.አይ. ቢን ላደንን ከ9/11 ጋር የሚያገናኝበት ጠንካራ ማስረጃ ስለሌለው ነው፡፡” ብሎ ነበር፡፡ እንዲያውም ቢን ላደን እራሱ ኡማት ከተባለ የፓኪስታን ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ በ9/11 ጥቃት እጁ እንደሌለበት ገልፅዋል፡፡ ቢን ላደን እንደሚከተለው ብሏል፡-
ከዚህ ቀደምም ተናግሬያለው ዩናይትድ ስቴትስ በደረሰው የመስከረም 11 ጥቃት የለሁበትም፡፡ እንደሙስሊምነቴ ከውሸት ለመራቅ እሞክራለው፡፡ …ንፁሃን ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎች ሰዎችን መግደል እንደሚደነቅ ተግባር አልቆጥረውም፡፡ እስላም በጥብቅ ይከለክለዋል…፡፡ እንዲህ አይነት ድርጊት በጦርነት ግዜ`ኳ የተከለከለ ነው፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ነች የሌሎች እምነት ተከታዮች ሴቶች፣ ህፃናትና ተራ ሰዎች ጉስቁልና ተጠያቂዋ፡፡ የመስከረም 11 ጥቃትን ያደረሱት የአሜሪካ ህዝቦች ወዳጆች አይደሉም፡፡ ከዚህ ቀደምም ተናግሬአለው የአሜሪካ ስርአት አንፃር ነን እንጂ ህዝቡን አንፃረርም፣ በነዚህ ጥቃቶች ግን ተራ የአሜሪካ ህዝብ ነው የተጎዳው፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ የነዚህ ጥቃቶች ተጠያቂዎችን ከውስጧ ነው መፈለግ ያለባት፣ የአሜሪካ ስርአት አካል የሆኑና አንፃሩ የተነሱትን፡፡ ወይም ለሌላ ዓይነት ስርአት እየሰሩ ያሉ፤ ይህኛውን ክ/ዘመን የእስላምናና ክርስቲያን ግጭት ዘመን ማድረግ የሚፈልጉ፣ እናም የራሳቸው ስልጣኔ፣ ህዝብ፣ ሃገር፣ ወይም ርእዮተ አለም እንዲሰፍን የሚሹ ሰዎች፡፡
በተጨማሪም ደሞ በዩ.ኤስ የደህንነት ተቋማቱ አሉ፣ በየአመቱ ከኮንግረስና ከመንግስት በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ፈንድ የሚፈልጉ፡፡ ይህ [የፈንግ ጉዳይ] የቀድሞ ሶቭየት ዩኒየን እስካለች ድረስ አስቸጋሪ ጉዳይ አልነበረም ከዛ በኋላ ግን የነዚህ ተቋማት በጀት አደጋ ውስጥ ገብቷል፡፡ ጠላት አስፈለጋቸው፡፡ አንፃር ኦሳማና ታሊባን ፕሮፖጋንዳ ጀመሩ፣ ቀጥሎ ይህ [ጥቃቱ] ተከሰተ፡፡ አየህ የቡሽ አስተዳደር የ40 ቢሊዮን ዶላር በጀት አፀደቀላቸው፡፡…አሁን ይህን ገንዘብ ለመስፋፋትና ጥንካሬአቸውን ለመጨመር ይጠቀሙበታል፡፡ ምሳሌ እሰጥሃለው፡፡ ከመላው ዓለም የሚገኙ እፅ አዘዋዋሪዎች ከዩ.ኤስ የሚስጥር ተቋማት ጋር ግንኑነት አላቸው፡፡ እነዚህ ተቋሞች አደንዛዥ እፅ ማብቀልና ማዘዋወርን መቆጣጠር አይሹም፣ ያለበለዝያ አስፈላጊነታቸው ይቀንሳል፡፡ ጀነራል ኖሬጋ በሲ.አይ.ኤ ነው ያደንዛዥ እፅ ጌታ የተደረገው፣ አስፈላጊነቱ ሲያበቃ ደሞ ለሌላ ጉዳይ ማመኻኛ ተደርጓል፡፡
… ይህ ምን ማለት ነው? ይህ ታድያ በዩናይትድ ስቴትስ በመንግስት ውስጥ ሌላ መንግስት እንዳለ አያሳይም? ይህ የሚስጥር መንግስት ጥቃቶቹን ማን እንደፈፀመው መጠየቅ አለበት፡፡ (Ummat, Karachi, September 28, 2001)
ይህን ስናነብ ቢን ላደን ጥቃቱን ያመነበት ቪድዮስ ልንል እችላለን፡፡ ቪድዮው ግን የሐሰት (“ፌክ”) ነው፡፡ ለዚህም ማስረጃው በቂ ነው፡፡ ታህሳስ 14፣ 2001 ላይ በህዳር 9፣ 2001 ተቀረፀ የተባለ ቪድዮ ብቅ አለ፡፡ በዚህም ቢን ላደን ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ተረጋገጠ፡፡ ሆኖም ግን ሙያተኞች ቪድዮው የሃሰት ቅንብር መሆኑን አጋልጠውታል፤ ካከኙበት እንከን ውስጥ፡-
1.        ቢን ላደን ወፍሯል፡፡
2.        አፍንጫው አነስ ብሏል፡፡
3.        በቀኝ እጁ ተጠቅሞ ሲፅፍ ይታያል፤ በኤፍ.ቢ.አይ መረጃ መሰረት ግን ግራኝ ነው፡፡
4.        ለመጀመርያ ግዜ ወርቅ ቀለበት አድርጓል፡፡
5.        የቪዲዮው ጥራት እጅግ ደካማ ነው፡፡
6.        የቪድዮው አብዛኛው ክፍል የተጓደለ (ባዶ) ነው፡፡
7.        የቪድዮው ድምፅ ደግሞ የባሰውኑ ደካማ ነው፣ ጫጫታ የበዛበት ሲሆን የሚባለውን ባግባቡ መስማት አይቻልም፡፡
8.        ብዙ ጋዜጦች የንግግሩ ፍቺ ልክ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ወዘተ…
የአንትራክሱ ተውኔት
ሌላኛው 9/11 ጥቃት የመንግስት እጅ እንዳለበት ያረጋገጠው ተከትሎ የመጣው የአንትራክስ ጥቃት ነበር፡፡ መጀመርያ ሚድያዎች ከተንጫጩና ሽብር ከነዙ በኋላ በጉዳዩ ዙርያ ድምፃቸውን እንዲያጠፉ የሚያደርግ አዲስ ነገር ተከሰተ፡ ስሙን ያልጠቀሰ የሲ.አይ.ኤ አባል ለጋርድያን ጋዜጣ የህን ነገር በአፍጋን ዋሻዎች ማምረት እንደማይቻል እና ሌላ ማስረጃ እስካልተገኘ ድረስ የመንግስት የስለላ ተቋማት እጅ እንዳለበት የማያወላውል ማረጋገጫ መሆኑን ተናገረ፡፡ በ2008 የአንትራክሱ ባህርይ ረቂቅነት ከየትም ሳይሆን ከአሜሪካ ላቦራቶሪዎች ብቻ ሊወጡ እንደሚችሉ የተረጋገጠ ሃቅ ሁኗል፡፡ ከአንትራክስ ደብዳቤዎቹ በአንዱ ላይ አላህ ታላቅ ነው የሚል መልእክት የሰፈረበት ስለነበር የቁንጮዎቹ አሽከር ፖለቲከኞች ኢራቅን ለመውረር ውትወታ ጀመሩ፡፡ የአንትራክሱ ዘረ መል (ጀነቲክስ) ላይ በተደረገው ጥናት የአሜስ ዓይነት (Ames strain) መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፣ ይህ ደሞ ከአሜሪካ ወታደራዊ ላቦራቶሪዎች ብቻ ሊገኝ የሚችል ነው፡፡ ለጥቃቱ ወደ 10 ግራም የሚጠጋ አንትራክስ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ካለው ደህንነት አንፃር ይህን ያህል መስረቅ የማይታሰብ ነው፡፡ የአንትራክስ ጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የም/ቤት አባሎቹ ቶማስ ዳሽሌ(Thomas Daschle)እና ፓትሪክ ሌሂ (Patrick Leahy) እና የሚድያ ሰዎች ናቸው፡፡ ሁለቱም የም/ቤቱ አባሎች እንዲፀድቅ ሲመጣ የነበረው የአሜሪካን ሕገ መንግስት ባፍጢሙ የደፋውና የሽብሩ ውጤት የሆነው የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ማለትም የአርበኛ አዋጅ (PATRIOT Act) የተባለውን አጥብቀው ይቃወሙ የነበሩ ም/ቤት አባሎች ናቸው፡፡ ኤፍ.ቢ.አይ ተጠርጥረዋል ያሏቸውን ሰዎች ሲከታተሉ የነበር ሲሆን ከነዚህ ዋነኛው ስቲቨን ጄ. ሃትፊል (Steven J. Hatfill) ነው፡፡ ክሱ የትም ሳይደርስ 5.8 ሚሊዮን ካሳ ተከፍሎት መዝገቡ ተዘጋ፡፡ ከዚ ቀጥሎ ፊታቸውን ያዞሩት ብሩስ ኢቪንስ (Bruce Ivins) ወደተባለ የፎርት ዲትሪክ (የአሜሪካ ወታደራዊ ላቦራቶሪ) ሳይንቲስት ወደሆነው ነበር፡፡ ጥፋተኝነቱ ተረጋግጧል ተብሎ ብይን ሊተላለፍበት ሲል እራሱን አጠፋ፡፡ ሚድያዎች እንደአውሬ አርገው ሳይንቲስቱን ቢቀርፁትም የሚያውቁት ሰዎች በተቃራኒው ስለሞራሉና ቤተክርስትያን አዘውታሪነቱን መስክረዋል፡፡ መጥፎ ነው ብሎ የመሰከረበት የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኛ የሆነው ጂን ሲ. ዱሊ የወንጀለኛነት መዝገብ ያለውና ሁሌም የገንዘብ እጥረት የነበረው ሰው ነው፡፡ ኤፍ.ቢ.አይ ግን የአንትራክስ ምርመራውን በዚህ ዘጋ፡፡
የድርሻ ሽያጮቹ ቅሌት
የ9/11ጥቃትን ተከትሎ ትዝብት ውስጥ የገቡ አጠያያቂ የድርሻ ሽያጮች ተካሂደው ነበር፡፡ በቅናሽ መሸጥ የሚባሉ የድርሻ ንግድ ናቸው፡፡ በቅናሽ መሸጥ የሚባለው የድርሻ ንግድ የሚካሄደው በእጅህ ያልገባውን ድርሻ አሁን ካለው ዋጋ በቅናሽ እሸጥልሃለው ብለህ መዋዋል ገንዘብ መቀበል ማለት ሲሆን እንዲህ የምትዋዋለው በኋላ በእጅህ ስታስገባው ዋጋው እጅግ ይወርዳል በሚለው ስሌትህ ነው፡፡ በኋላ እጅግ በወረደ ዋጋ ገዝተህ ከዚህ ከፍ ባለው ማለትም ቀድሞ በቅናሽ እሸጥልሃለው ባልከው ዋጋ ታስረክባለህ፡፡ በሁለቱ ያለው ልዩነት ትርፍህ ይሆናል፡፡ ይህ ቁማር ቅድመ እውቀትን ይጠይቃል፡፡ በታሪክ ከፍተኛ የገበያ ቀውስ ቀደም ብሎ በቅናሽ መሸጥ ተጠቅሞ ትርፍ ያገኘ ሰው ካለ አስቀድሞ ስለ ቀውሱ መረጃ እንደነበረው ማስረጃ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ AMR Corp.እናUAL Corp ድርጅቶች ውስጥ ልክ ከ9/11 ጥቃት በፊት ያልተለመደ እንዲህ አይነተ ንግድ ሲደረግ ነበር፡፡ እነዚህ ሁለቱ ድርጅቶች አውሮፕላኖቻቸው በ9/11ለት የተሳተፉት ናቸው፡፡ ሌላው እንደዚህ አይነት ንግድ የታየበት በዓለም ንግድ ማእከል 22 ወለሎችን ይዞ የነበረው የሞርጋን ስታንሊ (Morgan Stanley) ድርጅት ነው፡፡Merrill Lynch & Co. ይህም ሌላኘው ድርጅት ነው፡፡
በተጨማሪም የአሜሪካ መንግስት የ5 አመት ግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭም ጨምሮ ነበር፡፡ የ5 አመት ሰነዶች መግዛት ለመንግስት ማበደር ማለት ሲሆን በቀውስ ግዜ ገንዘብህ እንዳይባክን አስተማማኝ ቦታ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ የነዚህ ነጋዴዎች ግንኙነት ሲፈተሽ ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር ሳይሆን ከሲ.አይ.ኤ ጋር ይሂናል፡፡ በቅናሽ የተሸጡትን የገዛው ድርጅት Deutsche Bank Alex. Brown መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በጀርመንና አሜሪካ ባንኮች ጥምረት በ1999 የተመሰረተ ነው፡፡ እስከ 1998 ድረስ የAlex. Brown (የአሜሪካው ክንፍ) ሃላፊ የነበረው ክሮንጋርድ (A.B. “Buzzy” Krongard) ነበር በጥር 26፣ 2001 (ከጥቃቱ አምስት ወር በፊት) የሲ.አይ.ኤ ዋ/ዳይሬክተር ሁኖ ተሹሟል፡፡ ከ1998 ጀምሮ የሲ.አይ.ኤ ዳይሬክተር ለነበረው ጆርጅ ቴኔት አማካሪ ነበር፡፡
የፓይለቶቹ ሴሚናር
የጥቃቱ ውስብስብነት የገረማቸው የሲቪልና የጦር አየር አብራሪዎች ደግሞ THE GRANDPRE SEMINARየተሰኘ ጥናታዊ ስብሰባ ጠርተው ጉዳዩን ተወያይተውበታል፡፡ 72 አዓታትን የፈጀ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጭራሽ አደረጉ የተባሉት ሰዎች ሊፈፅሙት እንደማይችሉ በሙሉ ድምፅ ተስማምተውበታል፡፡ “አሸባሪዎቹ” በአሜሪካ የአየር በረራ ትምህርት ቤቶች ሲሰለጥኑ ስለነበርና መምህራኖቻቸውም የተባሉት ሰዎች እጅግ ደካማ ተማሪዎችቸው እንደነበሩ ከመመስከራቸው አንፃርና አየር ከምትጓዝበት መስመር አውጥተህ ያለ ራዳር እርዳታ ከስር መልክአ ምድሩን እያየህ ከምትፈልገው ቦታ በመድረስ ዒላማውን ሳትስት ለመምታት ከፍተኛ ልምድ እና በቦታው በተደጋጋሚ በማብረር ልምድ በማካበት አካባቢውን ማወቅ በሚጠይቅበት ሁኔታ እነዚህ ለማጅ አብራሪዎች ሊያውም ሰነፍ ለማጆች ፈፀሙት ለማለት ይከብዳል፤ እንዲህ ለመፈፀም ከፍተኛ የበረራ ብቃትና ያካባቢ እውቀት ይጠይቃልና፡፡ የሴሚናሩ ተሳታፊዎች በመጨረሻም እንዲህ ዓይነት ብቃት ያለው ስራ ለመስራት አልያም አይምሮው የነሆለለ ልምድ ያለው ወታደራዊ አብራሪ ከጎናቸው ሲረዳቸው ነበር አልያም አየሮቹ በርቀት መቆጣጠርያ ጣብያ በተቀመጡ ሰዎች ቁጥጥጥር ስር ሲበሩ ነበር ብለዋል፡፡ (ስለማነሁለል ጥበብና ወታደራዊ ጥቅሙ በሌላ ምእራፍ እናየዋለን፡፡) ይህ ጠለፉ የተባሉት ሰዎች በሂወት የመገኘታቸውን እንቆቅልሽ የሚፈታ ነው፡፡ ሙያተኞቹ የጥናታቸውን ውጤት ለዋይት ሃውስ ሪፖርት የሰጡ ሲሆን መልስ አልተሰጣቸውም፡፡ (Portugal News, August 3, 2002 /Webster Tarplay፡ 9/11 Synthetic Terror Made in USA)
ቀጥሎ ኤንጅል ነች
ከዚህም በተጨማሪ የፕሬዚደንቱ አየር መጓጓዣ የሆነችው –ኤየር ፎርስ ዋን– በየእለቱ የኮድ ስሟ የሚቀያየር ሲሆን የሚያውቁትም በጣም ከጫፍ ያሉ ቁልፍ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሰማይ ላይ እያለ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ “Angel is next.” –“ቀጥሎ ኤንጅል ነች፡፡” የሚል ማስፈራርያ ደርሶት ነበር፡፡ የኤየር ፎርስ ዋን የእለቱ ኮዷ ኤንጅል የነበረ ሲሆን ይህን ኮድ ተጠቅሞ ማስፈራራት የውስጥ ሰዎች ፕሬዚደንቱን ለማዘዝ ማለትም በል ያሉትን መግለጫ እንዲሰጥ–ምንም ማስረጃ ሳይቀርብና ማንም ሃላፊነቱን ሳይወስድ አልቃይዳን እንዲያወግዝ የሰጡትን ትእዛዝ እንዲፈፅም ለመጨምደድ የተጠቀሙበት ስልት ነበር፡፡ ይህን ዛቻ መተላለፉ ከደጅ ሳይሆን 9/11 ከውስጥ እንደተሰራ ቁልፍ ማስረጃ ነው፡፡ (Webster Tarplay፡ 9/11 Synthetic Terror Made in USA)
መደምደምያ
ይህ የታሪኩ አጭር እይታ ነው፡፡ በ9/11 ዙርያ የተነሱ እንቆቅልሾች መልስ አላገኙም፡፡ ትላልቅ ሚድያዎችም ጉዳያቸው አይደለም –እንዲመረምሩና እንዲያሳውቁ አልታዘዙም፡፡ የየል ዩኒቨርሲቲ ስከልና ቦንስ ኦርደር አባል የሆነው ፕሬዚደንት ቡሽ ያቋቋመው ኮሚሽን National Commission on Terrorist Attacks Upon the United States-ወይም በስፋት 9/11 ኮሚሽን የሚባለው አጥጋቢ መልሶችን አልሰጠም፡፡ ቡሽ መጀመርያ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር አድርጎ ሊሾም የነበረው ሉላዊው የነሮክፌለር ተላላኪው ሄነሪ ኪሲንጀርን ነበር ሰፊ ተቃውሞ ሲገጥመው ም/ቤት አባሎቹን ሃሚልተንን እና ኪንን አደረገ፡፡ ይህም ቡድን በጠቅላላ ከቁንጮዎቹ ጋር የተሳሰሩና በጀርባ ታሪካቸው በተለያዩ የፖለቲካ ቅሌቶች መዝገብ ያለባቸው ናቸው፡፡
የ9/11እውነቱን ለማውጣት የተሰባሰቡ ነፃ ዜጎች በሴራው ሙሉ ገፅታ አይስማሙም፡፡ ግማሾቹ ሆን ብለው እያወቁ ጥቃቱ እንዲፈፀም ዝም ብለው ተመለከቱ ብለው የሚያምኑት ማለትም –LIHOP (Let It Happen On Purpose) የሚባሉት ሲሆኑ፤ ግማሾቹ ደግሞ አውቀው አስበውበት አደረጉት ማለትም –MIHOP (Made It Happen On Purpose)የሚሉት ናቸው፡፡ የመጀመርያዎቹ መንግስት ውስጥ ያሉ ሃይሎች የሽብር ጥቃቱ እንደሚፈፀም እያወቁ ለፖለቲካዊ ግባቸው ፀጥ ብለው እንዲሆን ተመለከቱት የሚል ሲሆን፤ የሁለተኛው ደግሞ ሲ.አይ.ኤ ከፅንፈኞች ጋር ያለውን ትስስር ከግምት በማስገባት ከጅምሩ ራሳቸው ያደረጉት ነው ይላል፡፡ በዚህ መፅሃፍ ከቀረቡት መረጃዎች አንፃር የመጀመርያውን ለማመን እጅግ ገራገር መሆንን ይጠይቃል፡፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s