ቅንጫቢ ፫ ኦሳማ ቢን ላደን (ካልታተመ መፅሃፍ የተወሰደ በግደይ ገ/ኪዳን እና ተክሉ አስኳሉ)

Posted: March 7, 2012 in ሽብር
11
ኦሳማ ቢን ላደን

 ኦሳማ ቢን ላደን በዚህ ውስብስብ ሰው ሂወት ታሪክ አስታከን የወንድማማችነቱና የምእራባውያኑ እጆች ስራን መዳሰስ እንቀጥላለን፡፡ ቢን ላደን ሁሉንም ነገር፡- የሚስጥር ውስጥ ሚስጥሮችን የሚያውቅ አይመስልም በውነቱም ንፁህ አማኝ ይመስላል፡፡ ጥፋት የለበትም ለማለት ሳይሆን በትክክልም የአሜሪካ ኢምፐርያሊዝም የሚለውን ማለትም የቁንጮዎቹን አጀንዳ ሲታገል የነበረ ነው፡፡ በዚህና በቀጣይ ምእራፎች ግልፅ ይሆንልናል፡፡
ኦሳማ በ1957 ከየመኑ የኮንስትራክሽን ስራ ከበርቴ የሆነው ሼክ መሀመድ ቢን አውድ ቢን ላደን 17ኛ ልጅ ሁኖ ተወለደ፡፡ ከሳውዲ ዓረብያ ንጉሳዊ ቤተሰብ የጠበቀ ግንኙነት የነበረው መሀመድ በመካና መዲና ቅዱስ ቦታዎችን እንዲያድስ የመካ ዋናው መስጊድን ጨምሮ ስራው ይሰጠው ነበር፡፡ በ1969 በየሩሳሌም የአል አቅሳ መስጊድን እንዲያድስ ኮንትራት ተሰጦት ነበር፡፡ በ1972 መሀመድ ቢን ላደን በሚሞትበት ግዜ በሳውዲ ዓረቢያ ንጉሳዊ ቤተሰብ ያልሆነው ሃብታም ሰው ለመሆን በቅቶ ነበር፣ ንብረቱንም ለሃምሳ አራት ልጆቹ አወረሰ፡፡ በ1979 የመካ ዋናው መስጊድ በፅንፈኞች ታግቶ ለማስለቀቅ የሳውዲ መንግስት ካቃተው በኋላ የፈረንሳይ ልዩ ሃይሎች ተጠርተው በኬሚካል መሳርያ አስለቅቀውታል፡፡ በዚህ አሸባሪዎች ጥቃት የኦሳማ ቢን ላደን ወንድም ማህሮስ ቢን ላደን እጅ አለበት ተብሎ ታስሮ ነበር፡፡ ማህሮስ ለንደን ዩኒቨርስቲ ተማሪ እያለ ነበር ሙስሊም ወንድማማችነት ጋር ግንኙነት የጀመረው፡፡ የሳዑዲ ደህንነቶች ማህሮስ ነፃ ነው ብለው ለቀውታል፡፡ በምርመራው አሸባሪዎቹ የማህሮስን የቀድሞ ጓደኞች ግንኙነትን በመጠቀም ያለ ፈቃዱ/እውቅና የቢን ላደን መኪኖችን በመጠቀም ጥቃታቸውን ለማስተባበር ተጠቅመውበታል፡፡ (In the Name of Osama Bin Laden, Roland Jacquard, 2001, pp.13-14) የቢንላደን ድርጅት የእድሳት ስራ እየሰራ ስለነበር መኪኖቹ ያለ ፍተሻ በነፃነት ይገቡና ይወጡ ነበር፡፡ አሸባሪዎቹ ይህን ክፍተት ተጠቅመው በመኪኖቹ መሳርያ ሲያስገቡባቸው ነበር፡፡ ማህሮስ ነፃ ቢለቀቅም ስሙ ግን ተበላሽቷል፡፡ የሌላ ቤተሰብ ልጅ ቢሆን ኑሮ እንደሌሎቹ በስቅላት ይቀጣ ነበር፡፡
ኦሳማ ቢን ላደን እንደ ወንድሙ ማህሮስ ፊቱን ወደ ፅንፈኞች አዞረ፡፡ የሂወት ታሪኩ ፀሃፊ የሆነው እንደሚለው በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ እያለ ኦሳማ የቅንጦት እና አለማዊ ሂወት ነበር የሚመራው፣ በተለይም በቤሩት ከ1973-1975 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በሚማርበት ወቅት፡፡ እስልምናን ሙሉ ለሙሉ መቀበል የጀመረው በጅዳ አብዱል አዚዝ ዩኒቨርሲቲ በሚማርበት ወቅት ነው፡፡ በዚህን ወቅት ወደ መካ የሃጅ ጉዞውን አደረገ፡፡ ከዚህ ልምዱ በኋላ ፂሙን ማሳደግ ጀመረ፡፡ ሮቢንሰን ያልዳሰሰው ክፍል ምንድን ነው በኦሳማ ሂወት እንዲህ ለውጥ ሊያመጣ የቻለውን ከሙስሊም ወንድማማችነት ጋር የፈጠረው ቁርኝትን ነው፡፡
መሀመድ ኩትብ፣ የሙስሊም ወንድማማችነት ዋና ንድፈ-ሃሳባዊ የሆነው ሰዒድ ኩትብ ወንድም የሆነው፣ በ1966 ናስር በሙስሊም ወንድማማችነት ላይ በወሰደው እርምጃ ምክንያት ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ተሰዶ ነበር፡፡ በተለያዩ የሳውዲ ዓረብያ ዩኒቨርሲቲዎች የማስተማር ሃላፊነት ተሰጥቶት ነበር፡፡ ሳውዲ ዓረቢያ እያለ መሀመድ ኩትብ የዓለም ወጣት ሙስሊም ጉባኤ (World Assembly of Muslim Youth) የተባለ ማህበር መመስረት ሲጀምር በቢንላደን ቤተሰብ ድጋፍ በ1972 እውን ሆነ፡፡ በወቅቱ የኦሳማ ወንድም የሆነው ኦማር ዳይሬክተሩ ሁኖ ነበር፣ ሌላ ወንድሙም አብዱላ ዳይሬክተር ሁኖ አገልግሏል፡፡ (Qutb- personal correspondence with the Italian Muslim Association, Omar and Abdullah – article) ማህበሩ የቡሽ አስተዳደር እስኪያስቆመው ድረስ በኤፍ.ቢ.አይ. አሸባሪዎችን በመደጎም ምርመራ ሲደረግበት ነበር፡፡
ማህበሩ በእስልምና ላይ ያለው እይታ ሉላውያኖቹ እንደሚወዱት አመለካከት እንደ ሙስሊም ወንድማማችነት አይነቱ ነው ማለትም፡- ምእራቡ ለእስልምና የስጋት ምንጭ ነው፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን መፀየፍ አለብንና ወደ ቀድሞ ሁኔታ እንመለስ የሚለውን፡፡ ቅርንጫፎች በመላው ዓለም አሉት፣ ዋና መቀመጫው ሪያድ ነው፡፡ በጅዳ ንጉስ አብዱል አዚዝ ዩነቨርስቲ በሚማርበት ወቅት ኦሳማ ቢን ላደን ከመሀመድ ኩትብ ጋር የጠበቀ ግንኙነት መሰረተ፣ የሙስሊም ወንድማማችነትንም ተቀላቀለ፡፡ የ“Islam In the World” ደራሲ ማሊሴ ሩዝቨን የቀድሞ የቢቢሲ ዓረቢኛ አርታኢ የነበረው እንዲያውም ኩትብ በወቅቱ የኦሳማ “ተቆጣጣሪ” /“mentor”/ ነበር ይለናል(The Guardian Malise Ruthven)
በኦሳማ የዩኒቨርሲቲ ሂወት ወሳኝ ቦታ የነበረው ሌላኛው ሰው ፕሮፌሰር የሆነው ሼክ አብዱላ ዩሱፍ አዛም ነው፡፡ (ከግብፁ የአዛም ቤተሰብ ግንኙነት የለውም፡፡) በዌስት ባንክ ንቁ የሙስሊም ወንድማማችነት አባል የነበረ ፍልስጤም የተወለደ የሃይማኖት መምህር ነው፡፡ ካይሮ እያለ ከሰዒድ ኩትብ ቤተሰብ ጋር ይገናኝ ነበር፣ ይህን ተከትሎ ከፅንፈኛ አማፅያን የግብፅ እስላማውያን ጋር ቅርርብ ፈጠረ፡፡ (Bin Laden: The Man Who Declared War On America, Yossef Bodansky, 1999, p. 11) ከዚህ በኋላ በንጉስ አብዱል አዚም ዩኒቨርሲቲ ሊያስተምር ተዛወረ፣ እዚህም ከመሀመድ ኩትብ ጋር ግንኙነት ፈጠረ፡፡ ኦሳማ በዚህን ወቅት ነበር የአዛም ፅንፈኛ ሃሳቦችን የተቀበለው፡፡
ዶ/ር አዛም የአፍጋን ጂሃድን በ1979 ከተቀላቀሉት የመጀመርያዎቹ ዓረቦች አንዱ ነው፡፡ ትንሽ ቆይቶ የ22 ዓመቱ ወጣት ኦሳማ ተከተለው፡፡ ትንሽ ቆይቶ ሁለቱ በፔሽዋር፣ አፍጋኒስታን መክታን አልኪዳማትን (ኤም.ኤ.ኬ.) ወይም ሙጃሂዲን አገልግሎት ቢሮን መሰረቱ፡፡ ድርጅታቸው ከፓኪስታን ሙስሊም ወንድማማችነት ወይም ጀማት-ኢ ኢዝላሚ ጋር ጥምረት ፈጠረ፡፡ ሙጃሂዲን አገልግሎት ቢሮ ጂሃድ መቀላቀል የሚፈልጉትን ይመለምል ነበር፣ በ1980ዎቹ በዓለም ዙርያ በ50 ሃገሮች አልኪፋ የተባለ ድርጅት ስም ቅርንጫፎችነበሩት፡፡ የሙስሊም ወንድማማችነት ከቢንላደን ቤተሰብ ገንዘብ ጋር ተጣምሮ የሙጃሂዲን አገልግሎት ቢሮን እጅግ ስኬታማ አደረጉት፡፡
ከአለም ዙርያ ፅንፈኞች ወደ አፍጋኒስታን ጎረፉ፡፡ የትጥቅና ስልጠና ችግሩን ለመቅረፍ አዛምና ቢንላደን ፔሽዋር፣ ፓኪስታን ውስጥ ማሳዳት አልአንሳር የተባለ ማእከላዊ የጦር ሰፈር፣ የስልጠናና የትጥቅ ማከማቻ መሰረቱ፡፡ (Bin Laden: The Man Who Declared War On America, Yossef Bodansky, 1999, p. 12) ይህ ነው በሺዎች ለሚቆጠሩት ጂሃዱን ለመቀላቀል ለሚጎርፉት ማረፍያ ሰፈር በዓረቢኛ አልቃይዳ (the base)የሆናቸው፡- ፔሽዋር፣ ፓኪስታን፡፡ በዚህ የፔሽዋር ሰፈር ካለፉት በርካታ ስዑዲያውያን አንዱ ዶ/ር ሰዓድ አልፋቂ ነበር፤ ለፒ.ቢ.ኤስ. በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ አልቃይዳ እንዴት እንደተፈጠረና ቢን ላደን የመሰረተው የአሸባሪዎች ቡድንን ለመጥራት ተብሎ እንዳልነበር ይናገራል፡-
“እንግዲህ ኤፍ.ቢ.አይ. ስለ አልቃይዳ ቢን ላደን የመሰረተው ድርጅት አድርጎ ሲያወራ ያስቀኛል፡፡ … ቀላል ታሪክ ነው፡፡ ቢንላደን…እንግዶቹን የሚቀበለው በፔሽዋር እንግዶች ማረፍያ ነው፡፡ ያለሰነድ ወደ ጦርነት ይሄዱና ይመጡ ነበር፡፡.. ማን ሄደ ማን መጣ ምን ያህል ግዜ ቆየ የሚል ሰነድ አልነበረም፡፡ ቆንጅዬ አቀባበል ብቻ ነበር የነበረው፡፡ ከዛም ወደዛ [ወደ ውጊያው] መሄድ ነው፡፡ …እንዲህ እያለ ብዙ ቤተሰቦች ስለ ልጆቻቸው በሚጠይቁበት ወቅት [ቢን ላደን] ህፍረት ውስጥ ይገባ ነበር፡፡ አያውቅም፡፡ ምንም መዝገብ የለምና፡፡ እናም አጋሮቹን በሱ ጥላ ስር የሚመጣውን እያንዳንዱን ዓረብ እንዲመዘግቡ ይነግራቸዋል፡፡…በዚህ ቀን መጥተው እዚህ ቤት ቆዩ የሚል መዝገብ ነው፡፡ አብዛኞቹ ለሁለት ሳምንት ለሶስት ሳምንት መጥተው ይጠፋሉ፡፡ ያ መዝገብ፣ ያ ሰነድ አልቃይዳ ይባል ነበር፡፡ ይህ ነው አልቃይዳ ማለት፡፡ አልቃይዳን በተመለከተ ምንም መጥፎ ነገር የለውም፡፡ ድርጅት አይደለም፡፡ በህቡእ ለሚያንቀሳቅሰው ቡድን ስም ሰጥቶት አያውቅም፡፡ ስም መስጠት ከፈለግህ “የቢን ላደን ቡድን” ማለት ትችላለህ፡፡ አልቃይዳ የሚለውን ቃል ከተጠቀሙ ግን … አልቃይዳ ዝም ብሎ ወደ ፔሽዋር መጥተው ወዲህና ወዲያ ተንቀሳቅሰው በእንግዳ ቤት የቆዩ ሰዎች መዝገብ ነው፡፡ በውኋላም ወደ አገራቸው የተመለሱ፡፡”(Al-Fagih interviewwith PBS)
ቢን ላደን በአፍጋን ጦርነት ወቅት ግዜውን በአብዛኛው ያሳለፈው በፓኪስታን ውስጥ ሁኖ ነው፣ ዋና ስራው ገንዘብ ማሰባሰብና ማደራጀት ነበር፣ ምንም እንኳ ከተቆጣጣሪው/መምህሩ/ጠባቂው “የጂሃድ ኢሚር” እየተባለ የሚታወቀው የሙጃሂዲኖችን ወኔ ማነቃቅያ ንግግሩ የሚታወቀው ሼክ አዛም ጋር በተደጋጋሚ አፍጋኒስታን ቢመላለስም፡፡ የኮንትራትነት ሙያው ቢንላደን በአፍጋኒስታን እጅግ ጠቅሞት ነበር፡- ከባባድ መሳርያዎችን በማስመጣት መንገዶችን በመጥረግና የሙጃሂዲኖችን ምሽግ በማጠናከር ስራ በመርዳት፡፡ በግንባር ጦርነት ውጊያ ላይ በእርግጥ ቢንላደንና አዛም ተሳትፈው ያውቃሉ ወይስ አያውቁም የሚለው እስካሁን አከራካሪ ነው፡፡ ሆኖም ግን ሁለቱም እንደ ንቁና ደፋር ተዋጊዎች ስማቸው ገኖ ይገኛል፡፡ ቢን ላደን አፍጋን በሚንቀሳቀስበት ወቅት ሙጃሂዲን አገልግሎት ቢሮ ከፓሽቱን የጦር ባላባትና ሙስሊም ወንድማማችነት አባል የሆነው ጉለቡዲን ሄክማትያር ጋር ዝምድና ፈጠረ፡፡ ሁለቱም አዛምና ሄክማትያር ፀረ-አሜሪካ ነበሩ፣ እንዲህም ሁኖ የሄክማትያር ቡድን ህዘብ-ኢ-ኢስላም በሲ.አይ.ኤና አይ.ኤስ.አይ. (የፓኪስታን ደህንነት) በኩል ለሙጀሃዲኖች ከሚሰጠው እርዳታ 40% ይደርሰው ነበር፡፡ (In the Name of Osama Bin Laden, Roland Jacquard, 2001, p. 57) በ1980ቹ አዛም በምድረ አሜሪካ ጉዞዎችን ያደርግ የነበረ ሲሆን ሙስሊሞችን እየተገናኘ ገንዘብ እያሰባሰበ ጂሃድ የሚዋጉ ይመለምል ነበር፡፡ በአትላንታ፣ ቦስቶን፣ ቺካጎ፣ ብሮክሊን ጀርዚ ሲቲ፣ ፒተረስበርግና ተክሰን ከተሞቻ ትላልቅ የአልኪፋ (የሙጃሃዲን አገልግሎት ቢሮ ቅርንጫፎች) የከፈተ ሲሆን፣ ሌሎችም ትናንሽ ቅርንጫፎችን በሌሎች የአሜሪካ ከተሞች ከፍቷል፡፡ ታዋቂ የፓኪስታን ጋዜጠኛ አህመድ ራሺድ ስለ ጂሃድ ተዋጊዎች ምልመላ የሚከተለውን ይለናል፡-
“ማንም ቢሆን መምጣትና ለሙጃሂዲኖች መዋጋት የሚፈልግ ካለ ያለምንም ጥያቄ ቪዛ እንዲሰጡ ውጭ ላሉት ኢምባሲዎቿ በጠቅላላ ፓኪስታን ቋሚ ትእዛዝ ሰጥታ ነበር፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ ኢክዋን ኡል ሙስሊመን (ሙስሊም ወንድማማችነት)፣ የሳውዲው የዓለም ሙስሊም ሊግ፣ የፍልስጤም ፅንፈኛ እስላሞች ምልምሎችን አደራጅተው ከአይ.ኤስ.አይ. ጋር ያገናኟቸው ነበር፡፡ አይ.ኤስ.አይ. እና የፓኪስታኑ ጀማት-ኢ-ኢዝላም ፓርቲ ለውጭ አማፅያን አቀባበል የሚያደር፣ ማረፍያ የሚሰጥና፣ የሚያሰለጥን ኮሚቴ አዋቅረዋል፡፡ ቀጥለውም ሁለቱ ፅንፈኞች ሙጃሂዲን ቡድኖችን እንዲቀላቀሉ ያበረታታሉ፣ በተለይ ህዘቢ ኢስላምን፡፡ የዚህ እንቅስቃሴ ገንዘብ የሚመጣው ከሳውዲ ስለላ ተቋሞች፣ ገንዘቡ በከፊል ፔሽዋር ተቀማጭነቱን አድርጎ በነበረው የሳውዲው ፅንፈኛ ኦሳማ ቢን ላደን በኩል ነበር ፈሰስ የሚደረገው፡፡ በወቅቱ የፈረንሳዩ ተመራማሪ እንቅስቃሴውን እንዲህ ሲል ገልፆት ነበር፡- “በአይ.ኤስ.አይ. በኩል የተቀናጀ የሳውዲዎች፣ የሙስሊም ወንድማማችነት፣ እና የጀማት-ኢ-ኢዝላሚ የጥምረት ስራ ነበር፡፡” ይለዋል፡፡” (Islam in Central Asia: Afghanistan and Pakistan, Ahmed Rashid, (online .pdf article), p. 214)
ሶቭየቶች ተሸንፈው አፍጋንን ለቀው ቢወጡም ጃላላባድ ላይ ግን ጠንካራ የኮሚኒስት መንግስት ነበር ትተው የወጡት፡፡ በአይ.ኤስ.አይ. እና ሳውዲ ምክር የአፍጋኒስታንን መንግስት ለመቆጣጠር ሙጃሂዲኖች ጃላላባድ ላይ የፈፀሙት ጥቃት ከሽፎ በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎቻቸው ሲሞቱ ቢን ላደን ለመጀመርያ ግዜ ፀረ-ሳውዲ መንግስት መግለጫ ሰጠ፡፡ በአሜሪካ ሴራ አሳልፈው የሰጡ ከሃዲዎች በማለት የሳውዲ መንግስትን ወነጀለ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አስተማሪው አዛምም ሞቱበት፡፡ ቢን ላደን በ1989 መጨረሻ ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ተመለሰ፡፡ የጀግና አቀባበል ተደረገለት፣ አፍጋኒስታንን በተናነቃት የርስ በርስ ጦርነት ግን እጅግ ይከፋ ነበር፡፡ ወደ ቤተሰቦቹ በመመለስ ለአጭር ግዜ በቢንላደን ቤተሰብ ድርጅት በመንገድ ኮንስትራክሽን ውስጥ ስራ ያዘ፡፡ 32 ዓመቱ ሲሆነው የአፍጋን የአስር አመት ጦርነት ያገለገለ ወታደር ሁኖ ነበር፣ የጂሃድ ቀናቶቹ ግን ቀና መቆጠር አልጀመሩም፡፡ የሙስሊም ወንድማማችነት ሌሎች እቅዶች ይዞለት ነበር፡፡
ለቢን ላደን ከዚህ የእረፍት ግዜ የሚያላቅቀው አዲስ ክስተት አጋጠመ፡፡ ኢራቅ ኩዌትን ወረረች፡፡ ወዲያውም በግል ጀቱ ከጅዳ ወደ ሪያድ በመብረር ንጉሱ ፋሁድን መገናኘት ቢፈልግም ከልኡል ሱልጣን ጋር በመገናኘት ይሁንታቸውን ከሰጡ 10,000 ሙጃሂዲን ሰራዊቶቹን ለማሰባሰብና ኢራቆችን ለመውጋት ድጋፍ እንደሚያደርግ ይናገራል፡፡ ከዛም ቤተሰቦቹ ሲናገሩ ቤቱ በመመለስ ከሞባይል ስልኩ ጋር በመጣበቅ እስኪጠራ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ሌላ ሰነዶች ደብዳቤዎችን ፋክስ ሲያደርግ ያደርግ ነበር፡፡ (Bin Laden: The Man Who Declared War On America, Yossef Bodansky, 1999, p. 130)በመሃል ያልተጠበቀ ነገር ተከሰተ የሳውዲ ንጉሳዊ ቤተሰብ የአሜሪካ ሰራዊት ድጋፍ ተቀበለ፡፡ ይህ ለቢን ላደን እጅግ የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ጦርነቱ ካለቀ በውኋላ የአሜሪካ ሰራዊት ከቀጠናው አልለቀቀም በዚህም ምክንያት ቢን ላደን በስብሰባዎችና በመስጊዶች ፀረ-ሳውዲ መንግስት ንግግሮችን ማድረግ ጀመረ፡፡ የሳውዲ ደህንነቶችም እሱን መከታተል ጀመሩ፡፡ (Bin Laden: Behind the Mask of the Terrorist, Adam Robinson, 2001, p. 132) ከዚህ በኋላ ቢን ላደን አገር ለቆ ወጣ፡፡ በወቅቱ አብዛኞቹ ፅንፈኛ እስላማውያን ወደ ለንደን ነበር የሚሰደዱት ወይም አዲስ ወደ ተመሰረተችው የሱዳን እስላማዊ ሪፐብሊክ እዚህም ቢን ላደን እንዲመጣ ግብዣ ተደረገለት፡፡
በሰኔ 30፣ 1989 ጀነራል ኦማር ሀሰን አልበሽር በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከያዘ በውኋላ ሱዳን በዓለም አቀፍ ሙስሊም ወንድማማችነት የነሐሴ ለንደን ስብሰባ ግዜ የሚኖራት ሚና ወሳኝ እንደሚሆን እውቅና ተሰጥቶት ነበር፡፡ በዚህ ስብሰባ ሱዳንን ወክሎ የተገኘው ሀሰን አልቱራቢ ነበር፣ ከሱዳን መንግስት በስተጀርባ ያለው የስልጣን ባለቤት ነው፣ ለኦሳማ ቢን ላደንም አስተማሪው ነበር የሆነው፡፡ ሀሰን አልቱራቢ በ1932 ተወልዶ በእንግሊዘኛ ከሚያሥተምረው ት/ቤት ነበር የተማረው፡፡ ብሪታንያውያን የሚያካሂዱት ካርቱም ከሚገኘው ጎርዶን ኮሌጅ በ1955 በሕግ ዲግሪ ተመረቀ፤ በዚህ ግዜ አካባቢ የሙስሊም ወንድማማችነትን ተቀላቀለ፡፡ ለንደን ዩኒቨርሲቲ እንዲማር የትምህርት እድል አገኘ፣ እዚህም በህግ ሁለተኛ ዲግሪውን ሰራ፡፡ ቀጥሎ ቱራቢ ከፈረንሳይ በ1964 ከሶርቦኔ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ዲግሪውን (ዶክትሬቱን) አገኘ፡፡ በሱዳን የእስላማውያን እንቅስቃሴና የሙስሊም ወንድማማችነት የሱዳን ቅርንጫፍ መሪ ሁኖ ብቅ አለ፡፡ ከዛም የአፍሪካ ጥቁሩ ፖፕ በመባል ይታወቅ ጀመር፡፡(Bin Laden: The Man Who Declared War On America, Yossef Bodansky, 1999, p. 32)
በ1989 የሙስሊም ወንድማማችነት የለንደን ስብሰባው ሱዳን ለእስላማዊ እንቅስቃሴው አዲስ ሰፈር እንደምትሆን ወስኖ ነበር በዚህም መሰረት ካርቱም ውስጥ 19 አባሎች ያሉትና በቱራቢ የሚመራ የመሪዎች መማክርት ተመሰረተ፡፡ ይህ መማክርት በአፍጋን እርስ በርስ ጦርነት ግዜ እስላማዊ እንቅስቃሴውን በማደራጀት ሲረዳ ነበር፣ በሚያዝያ 1991 ካርቱም የተካሄደው “እስላማዊ የዓረብ ህዝቦች ኮንፈረንስን” በማደራጀት ረድቷል፡፡ ይህ አሸባሪዎችን ከመላው አለም ያሰባሰበው ጉባኤ ሕዝባዊ ዓለምአቀፍ ድርጅት(Popular International Organization)የተባለውን እንዲመሰረት አድርጓል፡፡ ይህ ድርጅት ደግሞ ሃምሳ አባሎች ያሉት መማክርት በካርቱም የመሰረተ ሲሆን፣ እያንዳዳቸው ከተለያየ እስላማዊ ትግል ከሚደረግባቸው ሃምሳ አገሮች የተውጣጡ ተወካዮች ነበሩ፡፡ (Bin Laden: The Man Who Declared War On America, Yossef Bodansky, 1999, p. 37)
ዓለም አቀፉ የሙስሊም ወንድማማችነት የመማክርት መአት ከመመስረት ባሻገር ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡ “የዓለም አቀፍ እስላም ሊጅን” ወይም “እስላማዊ ሊጅን” ይቆጣጠራል፡፡ በ1980ዎቹ ብቅ ያለ ተቋም ሲሆን በቀዳሚነት በፓኪስታን፣ አፍጋኒስታንና ቴህራን ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነበር፡፡ (በነዚህ ሃገራት ሙስሊም ወንድማማችነት ያለውን ሚና ከዚህ በፊት ዳስሰነዋል፡፡) በ90ዎቹ ከካርቱም ሁኖ ስራውን ይሰራ ነበር፡፡ እስላማዊ ሊጅን ኦፊሻል ያልሆነ ዓለም አቀፍ ጂሃድን የሚያስተባብር ወታደራዊ ተቋም ነው፡፡ ዮሴፍ ቦዳንስኪ የአሜሪካ ምክር ቤት ያቋቋመው የሽብርና ያልተለመደ ውጊያ ስልት መርማሪ ኮሚቴ /Congressional Task Force on Terrorism and Unconventional Warfare/ ዳይሬክተርና የቢን ላደን ሂወት ታሪክ ፀሃፊ የሆነው ኢስላሚክ ሊጅኑን ታጣቂ እስላማዊ እንቅስቃሴ(Armed Islamic Movement /AIM)እያለ ነው የሚጠራው፡፡ እስላማዊ እንቅስቃሴው ክፉኛ የተጎዳው በእንግሊዝ ብሄራዊ ባንክ በሐምሌ 5፣ 1991 ባንክ ኦፍ ክሬዲት ኤንድ ኮመርስ ኢንተርናሽናል /ቢ.ሲ.ሲ.አይ./ እንዲዘጋ ከስንት ውትወታ በኋላ ሲስማማ ነው፡፡ ይህ ባንክ የአደንዛዥ እፅ ትርፍን እና ሕገ ወጥ የመሳርያ ግብይት ገንዘብን ለማዛወር ይጠቀሙበት የነበረ ነው፡፡ የዓለም አቀፍ እስላማዊ እንቅስቃሴ ፋይናንስ የጀርባ አጥንት ነበር፡፡
በ1999 የፈረንሳይ ፓርላማ ሃላፊነት የሰጠው ቡድን ስለ ዓለም አቀፍ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ጥናቱን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ የሪፖርቱ መደምደምያም ታላቋ ብሪታንያ ቀንደኛ ማእከላቸው መሆኗን ያስረዳል፡፡ ከዚህ የ400 ገፅ ሪፖርት ላይ “የኦሳማ ቢን ላደን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ” — “The Economic Environment of Osama bin Laden” የተሰኘ የ70 ገፅ ተጨማሪ ፅሁፍ፣ በተለይም የኦሳማ ቢን ላደን የፋይናንስ መርበብ የለንደን ማእከሉን ትኩረት ያደረገ ፅሁፍ ነበር፡፡ ሪፖርቱ እስከ አርባ የሚጠጉ የብሪታንያ ባንኮች፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ከቢን ላደን መርበብ ጋር የተሳሰሩ ነበሩ፡፡ የፈረንሳይ ፓርላማ አባል አርኖልድ ሞንትቦርግ (Arnaud Montebourg) ሪፖርቱን በሚያቀርብበት ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፡- “ቶኒ ብለየር እና አስተዳደሩ በአለም ዙርያ ስለ ፀረ-ሽብርተኝነት ይሰብካሉ፡፡ የራሱን ባንከኞች ቢሰብክ እና ቆሻሻ ገንዘብ ከማሳደድ እንዲቆጠቡ ቢጠይቃቸው ይመከራል፡፡ … ስዊዞች እንኳ ከእንግሊዞቹ በተሻለ ትብብር ያደርጋሉ፡፡” ብሏል፡፡ (“UK is money launderers’ paradise,”  BBC News article) ፈረንሳዊው ተመራማሪ ጄን-ቻርለስ ብሪሳርድ (በሪፖርቱ ላይ የተሳተፈ) “Forbidden Truth” በተሰኘ መፅሃፉ የሚከተለውን ይደመድማል፡-
“ኦሳማ ቢን ላደንን የከበበው የፋይናንስ መርበብ እና ኢንቨስትመንቶቹ ከዚህ በፊት እንደነበረው እንደ 1980ዎቹ ቢ.ሲ.ሲ.አይ. ጋር አንድ ነው፡፡ ሰራተኞቹ ሳይቀሩ አንድ ናቸው (የቀድሞ የቢ.ሲ.ሲ.አይ. ኤግዚኲቲቮች እና ዳይሬክተሮች፣ የነዳጅ እና መሳርያ አዘዋዋሪዎች፣ የሳውዲ ኢንቨስተሮች) አንዳንዴም አንድ አይነት ድርጅቶች እጅ አለበት (ኤን.ሲ.ቢ፣ አቶክ ኦይል(Attock oil)፣ ቢ.ኤ.አይ.አይ.)
ጥናቱ እንደሚያረጋግጠው የቢ.ሲ.ሲ.አይ. ፋይናንስ መርበብ አልጠፋም፣ ኦሳማ ቢንላደን ተመሳሳይ ድጋፍ ከፖለቲካዊ ወይም እስላማዊ ተፅእኖ ያለባቸው ሽብር እንቅስቃሴዎች ያገኛል፡፡
የፋይናንሳዊ ባለ ድርሻዎች እና የሽብር እንቅስቃሴዎች መጣመር፣ በተለይ በታላቋ ብሪታንያ እና ሱዳን ለእያንዳንዱ ቡድን እንቅስቃሴ እንቅፋት የሆነበት አይመስልም፡፡
የሽብርተኛ መርበብ ሰፊ በሆነ ፋይናንሳዊ ስርአት ሲደገፍ ማለት የኦሳማ ቢን ላደን እንቅስቃሴ አርማ ነው፡፡” (Forbidden Truth, Jean-Charles Brisard and Guillaume Dasquie, 2002, pp. 184-185)
በቀላሉ ኦሳማ ቢን ላደን የዚህ ህቡእ የፋይናንስ መርበብ መሪ አለመሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ኦሳማ ቢን ላደን በሙስሊም ወንድማማችነት የሚመራው የዓለም አቀፍ እስላማዊ እንቅስቃሴ መሪ አይደለም፣ ሁኖም አያውቅም፡፡ ኦሳማ ቢን ላደን ለሙስሊም ወንድማማችነት ወታደራዊ ቅርንጫፍ እንደ ተምሳሌት /figurehead/ነው የሚጠቀሙበት እንጂ የአጠቃላይ እንቅስቃሴውን ቀርቶ እርሱ እንዲመራ ወይም ሃላፊነት እንዲወስድባቸው የሚሰጠውን እንቅስቃሴዎች እንኳ በብልሀት የሚያቀናብር/mastermind/ አይደለም፡፡
በዚሁ ስሌት የሙስሊም ወንድማማችነት እራሱ ደግሞ ብሪታንያ ባሉ ሉላውያን ስር መጠቀምያ ነው፡፡ ዓላማቸውም ከዚህ በፊት ደጋግመን እንደተመለከትነው አሁን ያለውን የዓለም ስርአት በመገልበጥ አዲስ ሉላዊ አገዛዝን ማስፈን ነው፡፡ እስከሚዘጋበት ግዜ ድረስ ቢ.ሲ.ሲ.አይ.ን ዓለም አቀፉ ሙስሊም ወንድማማችነት እንቅስቃሴዎቹን ፋይናንስ ለማድረግ ተጠቅመሞበታል፡፡ በሐምሌ 1991 ከመዘጋቱ በፊት ከፍተኛ የእስላማያኑ ስብሰባበ ሱዳን ተካሂዷል፣ ኦሳማ ቢን ላደን ደግሞ መርበቡን እንዲያጠናክር ታህሳስ ላይ አስገብተውታል፡፡ ቢን ላደን ፔሽዋር ከሙጃሂዲኖች ጋር እያለ የማደራጀት ብቃቱ ተመስክሮለታል፣ እናም ለስራው ወሳኝ ሰው ነበር፡፡ የሚስቱ ወንድም ከሆነው የቢ.ሲ.ሲ.አይ ቁልፍ ሰው የነበረው ካሊድ ቢን ማህፉዝ ጋር የነበረው ትስስርም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ማህፉዝ ስለ ብሪታንያ ባንክ ስራ ከበቂ በላይ እውቀት ያለው ሰው ነው፡፡ ስለፈራረሰው መርበብ እንደገና ማንሰራራት ሮቢንሰን የሚከተለውን ይላል፡-
“በወራት ውስጥ ኦሳማ እጅግ በመደመም ለሚከታተለው አልቱራቢ “የወንድማማችነት ቡድኑ” የተሰኘውን ስራውን ያብራራለታል፡፡ ይህ የ134 ዓረብ የቢዝነስ ሰዎች መርበብ ሲሆን የንግድ ኢምፓየራቸው ዓለምን ዙሮ ደጋግሞ የሚጠመጠምባት ሰዎች መርበብ ነው፡፡ በሁሉም ሀገሮች ተቀማጭ ሂሳብ ያላቸው ሲሆን በህጋዊ ቢዝነሳቸው ስር በየቀኑ በቢሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ያዘዋውራሉ፡፡ ትክክለኛው /ፍፁሙ/ ግንባር ነበር፡፡ የወንድማማችነት ቡድኑ በዓለም ዙርያ ባሉ የሽብር ቡድኖች ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ፡፡ ኦሳማ የዚህ ኢንዱስትሪ ፅዋ ማንሻ ነበር፡፡”(Robinson, p. 139 በተጨማሪም Bodansky, p. 43)
ኦሳማ 50 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ የኤል ሻማል ኢስላሚክ ባንክ ኦፍ ካርቱምን ከመውደቅ አድኗል፡፡ ይህ ቢንላደን ከሱዳኑ ሙስሊም ወንድማማችነት ቅርንጫፍ ማለትም ብሔራዊ እስላማዊ ግንባር ጋር በጥምረት የያዙት ባንክ ነበር፡፡
የሙስሊም ወንድማማችነት ፋይናንስ መርበብን እንደገና በማስጀመር ከረዳ በኋላ በሱዳን እንደ ኮንትራክተርነቱ ከሞያው ጋር በተመሳሰለ ስራ ተጠምዶ ነበር፡፡ በቢንላደን፣ በሱዳን ወታደራዊ ተቋም እና የሱዳን ብሔራዊ እስላማዊ ግንባር በጋራ አል ሂጂራ –Al-Hijra for Construction and Development Ltd–የተባለ ድርጅት አቋቋሙ፡፡ በቀይ ባህር የሱዳን ወደብንና የሱዳን ወደብ አየር ማረፍያንና ሌሎች ትላልቅ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሰርተዋል፡፡ አል ሂጂራ በናይል ላይም ፕሮጅክቶችን ሰርቷል፡፡ የባቡር መንገድ ማደስና፣ ሌሎች ትናንሽ አየር ማረፍያዎችንና መንገዶችን ባገሪቱ ዙርያ ሰርተዋል፡፡ (Bodansky, p. 46, Robinson, pp. 139-140)ቢን ላደን የሱዳንን መሰረተ ልማት በመገንባት ተጠምዶ እያለ ዓለም አቀፉ ሙስሊም ወንድማማችነት በሶማልያ ከአሜሪካ ወታደሮች ጋር ለመጋጨት እየተዘጋጀ ነበር፡፡ የአሜሪካ ሰራዊት “ለሰብአዊ ዓላማዎች” ሲባል ሶማልያ ውስጥ እንደሚሰማራ እስከ 1992 መጨረሻ አካባቢ የማይታወቅ ጉዳይ የነበረ ሲሆን ሙስሊም ወንድማማችነት ግን የሶማልያ መንግስት እንደወደቀ ከመስከረም 1992 ጀምሮ የአሜሪካ መምጣትን ሲጠባበቅ ነበር፡፡ የአሜሪካ ሰራዊት በሶማልያ የነበረው ተልእኮ ሆን ተብሎ እንዲወድቅ የተቀናበረ ነበር የሚመስለው፡፡ (አሜሪካ ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በውኋላ ባደረገቻቸው ዘመቻዎች ሁላ በአንዲቱም አሸንፋ አታውቅም የዚህ ሚስጥሩ ሳይንሳዊ አምባገነንነት፡ የአይረን ተራራ ሪፖርት” በሚለው ምእራፍ ታነቡታላችሁ አንቻኮል ቅድምያ ይህን እንጨርስ፡፡)
በለንደን የዓለም አቀፉ ሙስሊም ወንድማማችነት ስብሰባ ወቅት ሱዳን የእስላማዊ እንቅስቃሴ ማእከል ለመሆን መወሰኗንና መስማማታቸውን አይተናል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደነሃማስና ሂዝቦላ ያሉ ድርጅቶች በካርቱም ፅህፈት ቤታቸውን ከፈቱ፡፡ ቀጥሎ ማሰልጠኛ ካምፖች ተከፍተው ቢን ላደን ተጠራ፡፡ በውኋላ በ1991 መጨረሻ አካባቢ ሱዳንና ኢራን ወዳጅነታቸውን ማጠናከር ጀመሩ፡፡ ይህ የወታደራዊ ሺአይት (ኢራን) እና በፅንፈኛ ሱኒ (ሱዳን) መካከል የተፈጠረው ወዳጅነት የግብፅንና የሳውዲ ዓረቢያ መንግስታትን ቀልብ ሳበ፣ ከዚህ በውኋላ ሱዳን አስጊ እየሆነች መምጣቷ ግንዛቤ ውስጥ ገባ፡፡ ሀሰን አልቱራቢ በምእራቡ አለም ዲፕሎማስያዊ ጉብኝቱን አካሄደ፡፡ የቢን ላደን ሂወት ታሪክ ፀሃፊው ሮናልድ ጃኲርድ እንደዘገበው ከሆነ ቱራቢ በ1992 ለንደንን የጎበኘ ሲሆን በሮያል ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢንተርናሽናል አፈየርስ Royal Institute of International Affairs– RIIA– ግብዣ ተደርጎለት ተገኝቷል:: (In the Name of Osama Bin Laden, Roland Jacquard, 2001, p. 32) ደጋግመን እንደተመለከትነው ይህ ተቋም የብሪታንያ ሉላውያን ዋና ሚስጥራዊ ተቋም ሲሆን የአሜሪካ መንግስትን እና ፖለቲካ ፓርቲዎችን (ሁለቱንም ሪፐብሊካንንም ዴሞክራቶችንም) የተቆጣጠረው የውጭ ግንኙነት መማክርት–Council on Foreign Relations –CFRአስመስራች ድርጅት ነው፡፡በሶማልያ ቱራቢ ከጦር ባላባቱ መሀመድ ፋራ አይዲድ ጋር ትስስርን መሰረተ፡፡ ቦዳንስኪ የሚከተለውን ይላል፡-
“በሶማልያ የነበሩት አሸባሪዎች ለሚመሯቸው ሚሊሻዎች የሚሆን ጥትቅና መሳርያ ሲሰጣቸው ነበር፡፡ ከሚሊሺያዎቹ አንዳንዶቹ በሶማልያ በዋና ፓርቲዎች ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው፣ ሌሎች ደሞ ሙሉ ለሙሉ ነፃ የሆኑና ተጠያቂነታቸው ቀጥታ ለካርቱም ብቻ የሆኑ ናቸው፡፡ ቴህራን እኚህ አሸባሪዎችን በሱዳን በኩል አድርጋ ስትመራ የነበረችዋ ልክ በ1980ዎቹ በቤሩት የተመድ ሰላም አስከባሪዎችን ኢራንና ሶርያ በህዘብአላህ አድርገው ለመውጋት እንደተጠቀሙበት በሶማልያም የዩ.ኤስ ሃይሎችን ለመውጋት ነበር የተጠቀሙባቸው፡፡ (Bodansky, p. 43)
በ1992 አለም አቀፉ ሙስሊም ወንድማማችነት ሼክ ታሪቅ አልፋድሊ በምቾት በግዞት ይኖርባት ከነበረችው ለንደን በመጥራት በየመን የአሸባሪዎች ህዋስ እንዲያደራጅና ወደ ሶማልያ የሚሄዱትን የአሜሪካ ሰራዊትን እንዲያጠቃ ስራ ሰጠው፡፡ ቢን ላደን አልፋድሊን ከአፍጋን ውሎው ጀምሮ ያውቀዋል፣ ቢን ላደን በሺዎች ከሚቆጠሩ ከአፍጋን የተመለሱ የመናውያን ጋር እንዲገናኝ ረድቶታል፡፡ ቦዳንስኪ እንደሚለው አል ፋድሊ የመን የደረሰው በህዳር አጋማሽ ላይ ነበር፣ በአሜሪካ የክሊንተን አስተዳደር ወታደሮቹን ወደ ሶማልያ እንደሚልክ ይፋ ያደረገው ግን በህዳር 28 ነበር፡፡(Bodansky, p. 71) እቅዱን አስቀድመው ያውቁት ነበር፡፡ አሁንም ከሲ.አይ.ኤ. ጋር አሸባሪዎች እጅና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩ አልተገነዘቡም? የአሜሪካ ሃይሎች ከሶማልያ ዳርቻዎች በታህሳስ 9፣ 1992 ደረሱ፣ ዳርቻው ላይ ጋዜጠኞች የተቀበሏቸው በሚገርም ሞቅታ ነበር፡፡ ሲጀመር ጀምሮ አሜሪካ ምን ልትሰራ እንደመጣች በተለይ አሜሪካውያን ግራ በመጋባት ነበር ሲመለከቱ የነበሩት፡፡
የመጀመርያው ጥቃት የተፈፀመው ታህሳስ 29፣ 1992 ላይ አልፋድሊ አዲስ ባሰባሰባቸው የየመን ኢስላማዊ ጂሀድ ቡድኖች ኤደን ሆቴል እና ጎልደን ሙር ሆቴል ላይ በፈፀሙት ጥቃት ነበር፡፡ አንደኛው ቦምብ ሶማልያ ሲሄዱ የነበሩ 100 የአሜሪካ ሰራዊት አባላትን ለጥቂት ነበር የሳታቸው፡፡ ሌላም ከባድ መሳርያ የታጠቀ ቡድን አየር ማረፍያ አካባቢ ለመፈፀም የሞከረው ጥቃት ከሸፈ፡፡ አልፋድሊ ከተወሰኑ የቡድኑ አባሎች ጋር በጥር 8፣ 1993 እጃቸውን ሰጡ፡፡ የተቀሩት በአየር በኦሳማ ቢን ላደን ወደ ሶማልያ ተወሰዱ፡፡ በኋላ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ቢን ላደን ይህ በአየር የማጓጓዝ ዘመቻው የራሱን3 ሚሊዮን ዶላር እንዳስወጣው ሲጀነን ገልጿል፡፡ (Bodansky, p. 74) በሰኔ 5፣ 1993 ሞቃዲሾ ውስጥ የጀነራል አይዲድ ሃይሎች 20 ፓኪስታናውያን የተመድን ባለ ሰማያዊ ኮፍያ ወታደሮችን በደፈጣ ጥቃት አጠፏቸው፡፡ በኋላ በሰኔ መጨረሻ አካባቢ አይዲድ ሶማልያን ለቆ ሱዳን ውስጥ ተከሰተ፣ የከፍተኛ እስላማውያን ስብሰባ ላይ ለመገኘት ነበር፡፡ ቱራቢ፣ ቢን ላደን፣ የኢራን ደህንነቶች፣ የግብፁ እስላማዊ ጅሃድ ቡድን መሪ አይማን አልዛዋሂሪ የተገኙበት ነበር፡፡ አሜሪካን ከሶማልያ የማስወጣት ጉዳይን የተመለከተ ነበር ስብሰባው፡፡ ቦዳንስኪ እንደሚለው ዘመቻው በቱራቢ እና አልዛዋሂሪ ከሌሎች የአፍጋን ተመላሾች ጋር ሁነው የሚመሩት ነበር፡፡ ቢን ላደን እንደሁል ግዜው ሎጂስቲክ ላይ ተሰማርቶ ነበር፡፡ በ1993 በልግ ወራት አልዛዋሂሪ ሶማልያ በመግባት ከአይዲድ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዘመቻውን ሲያስተባብር ነበር፡፡ (Bodansky, pp. 76-78) የተከሰተውን የአሜሪካውያን ውርደት ማንም የሚያውቀው ነው “Blackhawk Down”የተሰኘው ፊልም በትክክል ደግሞ ቀርፆ አቅርቦልናል፡፡ በውጊያው ቀን የአይዲድ ሃይሎች ሁለት ብላክሃውክ ሄሊኮፕተሮችን የጣሉ ሲሆን፣ ሰባ ስምንት የአሜሪካ ወታደሮችን አቁስለዋል፣ አስራ ስምንት ገድለው አንድ ይዘዋል፡፡ እስከ አንድ ሺህ የሚቆጠሩ የሶማልያ ታጣቂዎችና ተራ ዜጎች (ሲቪሎች) ሂወት ደግሞ አልፏል፡፡ በመጨረሻ በመጋቢት 1994 የአሜሪካ መንግስት ስልጣን ለእስላማውያን ሃይሎች አስረክቦ ወጣ፡፡ ቢን ላደን ይህ ለእስላም ድል አድርጎ ቆጠረው፡፡ መጀመርያ ሶቭየቶች ከአፍጋኒስታን ተሸንፈው ተባረሩ፣ አሁን ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ ከሶማልያ ተሸንፋ ተባረረች፡፡ ሁለት ልዕለ ሃያላን በእስላም ጥንካሬ ተንበርክከዋል፡፡ ቼክ ሜት! ጨዋታውን እየለመዱ ነው? ሮቢንሰን የሚከተለውን ቢን ላደን የሰጠውን ቃለ መጠይቅ ያስነብበናል፡-
“እኚህ ልዕለ ሃያል ተብዬዎቹ በከንቱ ባዶ ነፋስ ላይ ነው የጠፉት፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ከራሽያ የባሰ ደካማ ነች ብለን እናስባለን፡፡ ሶማልያ ላይ ጂሃድ ከተሳተፉ ወንድሞቻችን በሰጡን ሪፖርት መሰረት፣ የዩ.ኤስ. ወታደሮች ድክመት፣ ተሰባሪነት፣ እና ቦቅቧቃነትን ማወቅ ችለናል፡፡ 80 የዩ.ኤስ. ወታደሮች ብቻ ናቸው የሞቱት፡፡ የሆነ ሁኖ ስለ አዲስ የአለም ስርአት ብዙ ከለፈፉ በኋላ፣ በድቅድቅ ጭለማ በቀቢፀ ተስፋ አምልጠው ወጡ፡፡” (Bin Laden: Behind the Mask of the Terrorist, Adam Robinson, 2001, p. 153)
የዚህ መፅሃፍ አንባቢ ይህን ዓ.ነገር እንደማያደናግረው ተስፋችን ነው፡፡ ማን ማንን እንደሚረዳና ልእለ ሃያላኑ ለምን እንደሚሸነፉ አውቀናል፡- በዚህ መንገድ ብቻ ነው አዲስ የአለም ስርአት በአለም ላይ ማስፈን የሚችሉት፡፡ ቢን ላደን ደግሞ አዲስ የአለም ስርአታቸውን እየታገለ ሳይሆን የሚደጉሙት መሳርያቸው መሆኑን ተመልክተናል፡፡ ገና ተጨማሪም እንመለከታለን!!! እዚህ ጋር ማስረዳት ያለብን መላ ምት ይኖራል፡፡ ቢን ላደን ከሙስሊም ወንድማማችነትና ከምእራብ ደህንነት ተቋማት ጋር እንደሚሰራ ተመልክተናል፤ ሆኖም ግን ቢን ላደን እጅግ አወዛጋቢ ሰው ነው፤ አንዳንዴ ከነሱ ጋር ቢሰራም ልክ እንደ ሙስሊም ወንድማማችነት ለነሱ የሚሰራ ሰው ግን አይደለም፡፡ እነሱም ቢሆኑ አስፈላጊነቱ ሲያበቃ የሚያስወግዱት መጠቀሚያቸው እንጂ ወዳጃቸው አድርገው አይወስዱትም ይህን ለምን እንዳልን በቀጣዩ ምእራፍ ይደርሱበታል፡፡
ደ/ር ዴኒስ ኩዲ (Dr. Dennis Cuddy) : “The Power Elite And The Muslim Brotherhood” (NewsWithViews.com) በሚለው ፅሁፉ የሙስሊም ወንድማማችነት የቅርብ ግዜ ታሪክን ወይም አሁን እየሆነ ያለውን አሳጥሮ ያስነብበናል፡፡ ሙስሊም ወንድማማችነት አዲስ የአለም ስርአት አምጪዎቹ ኢሉሚናቲዎች ከመቶ ዓመት በፊት ባወጡት እቅድ እየተጠቀሙበት ያለና አይናችን እያየ እየተገበረው ያለ እስላማዊ ሳይሆን ሜሶናዊ-ኢሉሚናቲ ማህበር ነው፡፡ የኢሉሚናቲዎች እቅድ በቅርብ ግዚያት ውስጥ መካከለኛው ምስራቅን ሙሉ ለሙሉ በሙስሊም ወንድማማችነት እጅ ማስገባት ነው፡፡ ቀጥለውም ታላቁን የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ያስነሳሉ፡ ፅዮናዊት እስራኤል ከሙስሊም ዓለም ጋር በማጋጨት፡፡ እስኪ ምእራፍ 5 “እውነተኛው አዲስ የአለም ስርአት” ላይ ያጣቀስነውን የአልበርት ፒኬ የኢሉሚናቲ መሰስራቹ አዳም ዉሻፕት ምትክ ለአብዮታዊው ኢሉሚናቲ ጓዱ ጁሰፔ ማዚኒ በነሃሴ 15፣ 1871 የፃፈውን ደብዳቤ እናስታውስ፡-
“ሶስተኛው የአለም ጦርነት ደግሞ እሚመጣው በፅዮናውያን እና አረቦች መሃከል በኢሉሚናቲ ወኪሎች እንዲፈጠር በሚደረገው ልዩነት ነው፡፡ ይህም በአለም ዙርያ እንዲስፋፋ ይደረጋል፡፡”
ገራገር የዓለም ህዝቦች ዓለምን የሚገነዘቧት ኢሉሚናቲዎች ከፋፍሎ ለመግዛት በሚያመች መልኩ በቀረፁላቸው እይታ ነው፡፡ ከፅዮናውያን በስተጀርባ ያሉት ከፈጣሪ የተጣሉ ሴጣናውያን መሆናቸውንና ለአላማቸው አይሁዱንም አህዛቡንም ከመጨረስ ወደኋላ የማይሉ መሆናቸውንና በተመሳሳይም ከሙስሊም ወንድማማችነት በስተጀርባ ያሉት የነዚሁ የሚስጥር አጋሮች መሆናቸውን መገንዛብ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሄግሊያዊ ዲያሌክቲካቸው በተግባር ሲውል ነው፡- ችግር – አፀፋዊ-ምላሽ – መፍትሄ፡፡ ተሲስ – አንቲተሲስ – ሲንተሲስ የሚሰራው፡፡ ይህ እየመጣ ያለው 3የአለም ጦርነት የሚደመደመው እቅዳቸው ከተሳካ የሉሲፈር ዶክትሪንን በመጫን ነው፡፡
ሎርድ ኸርበርት ሳሙኤል ሴሲሊ ሮድስ ያቋቋመው የዓለም መንግስትን መቆጣጠር ዓላማው ያደረገው የሚስጥር ማህበር የክቡ ጠረጴዛ (ሮያል ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢንተርናሽናል አፈየርስ የመሰረተው ቡድን) አባልና ተላላኪ በፍልስጤም ሀጅ አሚን አልሁሴኒን ሙፍቲና የፖለቲካ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ፡፡ በሰኔ 23፣ 1923 በብሪታንያ ሀውስ ኦፍ ሎርድስ ውስጥ ፍልስጤምን በተመለከተ ባደረገው ንግግር፡ [ፍልስጤም] የአረብ ወይም የአይሁድ ሃገር መሆን የለባትም፣ መሆን ያለባት መላው ዓለም ልዩ ድርሻ ያለባት ዓለም አቀፍ ሀገር ነው…፡፡” ብሎ ነበር፡፡ አልሁሴኒ ፍልስጤም በነበረበት ወቅት ሙስሊም ወንድማማችነት እንደተመሰረተ ከፊት ገፆች ተመልክተነዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ሙስሊም ወንድማማችነት ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲገባ የናዚ ጀርመን ደጋፊ ሁኖ ነበር፡፡ በ1930ዎቹ ሙስሊም ወንድማማችነት የሂትለር ግለ ታሪክ መፅሀፍን “ትግሌ” “Mein Kampf” ያከፋፍል ነበር፡፡ በ1936 800 አባሎች ብቻ የነበሩት በ1938 200,000 ደረሱ፡፡ በ1933 ሂትለር በጀርመን ስልጣን ሲይዝ በግብፅ በአልሁሴኒ ተከታይ በነበረው አህመድ ሁሴን ወጣት ግብፅ (Young Egypt) ወይም አረንጓዴ ለባሾቹ (Green Shirts)  ተመሰረተ ልክ እንደናዚ ወጣት ጥቁር ለባሾቹ፡፡ አንዋር ሳዳት የነዚህ አባል ነበር በመስከረም 18፣ 1953 ለግብፁ Al Mussauar እለታዊ ጋዜጣ በላከው ፅሁፉ ለሂትለር ያለውን አድናቆት ገልፅዋል፡፡ ስልጣን ከያዘ በኋላ ከሙስሊም ወንድማማችነት ጋር እና ምእራባውያን እቅድ ጋር በፈጠረው ግጭት ተገሏል፡፡
በሁለተኛ ዓለም ጦርነት የአሜሪካው ፕ/ት ሮዘቬልትም ቢሆን ለአይሁዶች ደንታ አልነበረውም፡፡ ሴክሬታሪ ኦፍ ስቴት ኤድዋርድ ስቴቲኒየስ (Edward Stettinius) ወረቀቶች መሰረት በየልታ ኮንፈረንስ ግዜ ስታሊን ለሳውዲ አረቢያው ንጉስ ሳኡድ ምን እንደሚያደርግለት ሲጠይቀው አሜሪካ ያሉትን 6 ሚሊዮን አይሁዶች እሰጠዋለው ብሎ እንደመለሰለት ፅፏል፡፡ ሮበርት ድረይፈዝ (Robert Dreyfuss)፡- Devil’s Game: How the United States Helped Unleash Fundamentalist Islam  በተሰኘው መፅሃፉ በ1953 ፕሬዚደን አይዘንሀወር ከዋይት ሀውስ ቢሮው ኦቫል ኦፊስ ውስጥ የሙስሊም ወንድማማችነት መሪ እንዴት ተቀብሎ እንዳነጋገረ ያስነብበናል፡፡ ገማል አብደል ናስር የአሜሪካን እንቅስቃሴ በጥርጣሬ ነበር ሲመለከት የነበረው፣ በ1957 እንዲህ ብሎ ነበር፡-
“የናንተ አሜሪካውያን ብልሀታችሁ የምትሰሩት ጅላጅል ስህተት ግልፅ የሆነና የታወቀ ሳይሆን የተወሳሰበ ጅላጅል ስህተት የምትሩ መሆናችሁ ነው፣ ይህ ደሞ አንድ ያልደረስንበት /ያላወቅነው/ ነገር አለ ብለን ብዙ እንድናስብ ያደርገናል፡፡”
ናስር በ1970 ከሞተ በኋላ አንዋር ሳዳት ተተካ ሳዳትም መጀመርያ ከወንድማማችነቱ ጋር ሰላም ሊፈጥር ቢሞክርም ከእስራኤል ጋር በ1979 በፈረመው የሰላም ስምምነት ምክንያት አልተሳካም፡፡ ከሙስሊም ወንድማማችነት በወጣውና በአይማን አልዛዋሂሪ የሚመራው እስላማዊ ጅሀድ የተባለው ቡድን በ1981 ገደለው (ዛሬ አይማን አል ዛዋሂሪ የአልቃይዳ መሪ ሁኗል፡፡) ሳዳትን የተካው ደግሞ ሙባረክ ነው፡፡ ሙባረክም ከ2005 በኋላ ሙስሊም ወንድማማችነት ላይ ዘመቻውን የከፈተ ሲሆን በዚሁ አመት (2011) በዓረብ ምድር በተከሰተው ህዝባዊ አመፅ ከስልጣን ተወግዶ ለፍርድ ቀርቧል፡፡ ሙስሊም ወንድማማችነትም ሙባረክን የሚቃወም ብቸኛው የተደራጀ ሀይል እንደመሆኑ መንበረ ስልጣኑን ለመረከብ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡
የግብፁ አብዮት ለዘመናት በግዞት የነበረው የወንድማማችነቱ አማካሪ ዩሱፍ አልቃራዳዊ እንዲመለስ አስደርጓል፡፡ በታህሳስ 10፣ 2010 ቃራዳዊ እንደተናገረው ከሆነ፡ “ሙስሊም ወንድማማችነት በፍልስጤም የመስዋዕትነት ዘመቻዎችን ይደግፋል፡፡ …ፈንጅ ስለሌላቸው እራሳቸውን ወደ ፈንጅ ይቀይራሉ፡፡ ይህ ግዴታ ነው፡፡”
የካቲት 3፣ 2011 የውጭ ግንኙነት መማክርት “Egypt’s Muslim Brotherhood” በሚል ርእስ የሲ.ኤፍ.አር. ሲኒየር ፌለው ኤድ ሁሴን ያወጣው ፅሁፍ እንደሚያትተው በግብፅ ያለው አብዮት እንደ ኢራን መሆኑ አይቀርም፡፡ ተራ ግብፃውያን ተቃውሞ ሰልፍ በሚያደርጉበት ግዜ ሙስሊም ወንድማማችነት ከበስተጀርባ ሁኖ ይጠባበቃል፡፡ ግዜው ሲደርስ ተራው ዜጋ ተጠራርጎ ፅንፈኞቹ ስልጣን ይይዛሉ፡፡
በሰኔ 2011Al-Masry Al-Youm ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ በእስላማዊ እንቅስቃሴ አጥኚዎች እምነት መሰረት የእስላማዊ ንድፈ ሃሳባዊ የሆነው ሞሀመድ ሰሊም አልአዋ ቀጣዩ ያልታወጀው የሙስሊም ወንድማማችነት እጩ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪ እንደሚሆን ይገምታሉ፡፡ ከዚህ ጎን ደግሞ የሙስሊም ወንድማማችነት የግብፅ ዋና አለቃ/መሪ ሞሀመድ መኸዲ አኬፍ ለኒው ዮርክ ታይምስ እንደተናገረው ከሆነ ሙስሊም ወንድማማችነት የግብፅን ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ካሸነፈ በኋላና ሀገሪቱን ሙሉ ለሙሉ ከተቆጣጠረ መኋላ “ሙሉ አጀንዳውን” /“full platform”/ ይፋ ያደርጋል ብሏል፡፡ የግብፅን ቀጣዩን እጣ ፈንታ ለመቆጣጠር ሙስሊም ወንድማማችነት የተለያዩ ፓርቲዎች ጥምረትን እየመራ ይገኛል ሲልIsrael News Update (July 6, 2011) ዘገባ ያስረዳል፡፡ በመጪው የመስከረም 2011 ምርጫ ሙስሊም ወንድማማችነት በበላይነት የሚወጣ ይመስላል፡፡ የግብፁ እለታዊ ጋዜጣ Al-Masry Al-Youm  ሶቢ ሳሌህ የተባለ የሙስሊም ወንድማማችነት አባል ጠይቆ እንደዘገበው ዓላማቸው ለሙስሊሞችም ሆነ ላልሆኑ የሸሪአ ህግ ብቻ እንደሚበጃቸው ተናግሯል፡፡
በግብፅ፣ በቱኒዝያ፣ በሊብያ፣ በየመን፣ በሶርያ ወዘተ… ያሉ ህዝባዊ አመፆች ጠቅላላ አመፃ የበዛባቸው ክስተቶች ናቸው፡፡ ሙስሊም ወንድማማችነት ከእስራኤል ጋር ያለውን ስምምነት እንደሚያፈርስና እስራኤልን ከገፀ ምድ እንደሚያተፋና ሁሉም ሙስሊም ጦሩን እስራኤል ላይ እንዲያነሳ ጥሪ እያደረገ ይገኛል፡፡ የጀርመን ፖለቲካዊ ሳይንቲስቱ ማቲያስ ኩንትዜል (Matthias Kuntzel)Islamic Anti-Semitism and Its Nazi Roots በሚለው ፅሁፉ የፒ.ኤል.ኦ ፋታህ፣ አልቃይዳ፣ ሀማስ፣ ኢስላሚክ ጂሀድ እና ሌሎችም ፅንፈኛ ቡድኖች ፈጣሪ የሆነው ሙስሊም ወንድማማችነት ከናዚ ጋር ያለውን ዝምድና ያስረዳል፡፡ እንደሚያስረዳው ከሆነ ሙስሊም ባልሆኑት ላይ የሚደረግ እስላማዊ ጅሀድ የሚለው ጭብጥ እስከ 1930ዎቹ ድረስ በየትኛውም እስላማዊ ዶክትሪን መሰረታዊ ጭብጥ አልነበረም ይላል፡፡ አመጣጡም በወቅቱ ከተነሳው አደገኛ ፀረ-ሴማዊነት እንቅስቃሴ ጋር መዛመዱ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ (ፀረ-ሴማውነት ሲባል እንግዲህ ለፖለቲካዊ መሳርያነት የተፈጠረው ሴማዊ እና ፀረ-ሴማዊ በሚለው ፈጠራ መሰረት ማለታችን ነው፡፡) በግብፅ በ1930ዎቹ ሙስሊም ወንድማማችነት በሚያዘጋጃቸው ሰልፎች ከፍተኛ ፀረ-ሴም መፈክሮች ይደመጡ የነበር ሲሆን በፓለስታይን መሪ የነበረው አሚን አልሁሴኒ ጋር የሂትለር ወጣቶች ዩኒፎርም የሚያደርጉትና የናዚ ሰላምታ አሰጣጥ ከሚያሳዩት ተከታዮቹ ጋር ከፍተኛ ድጋፍ ያደርጉለት ነበር፡፡ አሁን ሙስሊም ወንድማማችነት በግብፅ መስጊዶችን የምርጫ መቀስቀሻ በማድረግ መልካም ሙስሊም ከሆናችሁ ድምፃችሁን ለሙስሊም ወንድማማችነት ትሰጣላችሁ የሚለውን አመለካከት እያሰረፀ ይገኛል፡፡ (Jerusalem Post, Caroline Glick, June 3, 2011 article) አሁን ግብፅ በሙስሊም ወንድማማችነት እቅድ መሰረት ሶስተኛው ደረጃ ላይ ትገኛለች የወንድማማችነቱ አደራጅ የሆነው ካይራት አልሻተርን (Khairat al-Shater) ጠቅሶ Al-Masry Al-Youmእንደዘገበው ከሆነ፡፡ 
በመጪው የመስከረም 2011 ምርጫ ሙስሊም ወንድማማችነት ካሸነፈ ግብፅ በቀጠናው የበላይ በመሆን ሱኒ ዓረቦችን በመምራት ፊት ልትቀመጥ ትችላለች፡፡ (Jerusalem PostEli Karmon, June 23, 2011) በሊብያምእየተካሄደያለውአመፅከሙስሊምወንድማማችነትናአልቃይዳጋርተሳስሯል፡፡የሚመራቸውምጀነራልካሊፋሂፍተርሲሆንሲ.አይ.. የመሰረተውንየሊብያብሔራዊመድህንግንባርን (Libyan National Salvation Front) በመጋቢት1987በመቀላቀልበ1991 ወደአሜሪካገብቷል፡፡ (በቅርቡጋዳፊንጥሎተቃዋሚዎቹንየተቀላቀለውከፍተኛአመራርአብደልዮኑስውጊያእየመራየተገደለሲሆንገዳዮቹቢያዙምማንነታቸውይፋአልተደረገም፤ሃይማኖታዊጀርባየሌለውእንደመሆኑፅንፈኞቹካለውሰፊተቀባይነትአንፃርጋዳፊንከጣሉበኋላስልጣንእንዳይቀናቀናቸውእንዳስወገዱትጥያቄየለውም፡፡) ካሊፋሂፍተርበአሜሪካለሃያዓመትየኖረሲሆንቤቱምከሲ.አይ.ኤ. ላንግሌቢሮ 5 ማይልብቻርቀትየነበረውእዚህምከሊብያብሔራዊጦርጋርይሰለጥንየነበረ ነው፡፡የሊብያሙስሊምወንድማማችነትሱሌማንአብዱልቃዲርየሊብያጠ/ሚኒስቴርአልባግዳዲአልመሀሙዲያቀረበላቸውየውይይትጥሪለመከፋፈልየፈጠሩትዘዴሲሆንእንደማይሳካናእንደማይቀበሉትገልፆነበር፡፡ (Asharq Al-Awsat, in late June 2011) ከዚህምበተጨማሪዌብስተርግሪፊንታርፕለይ (Webster Griffin Tarplay) በድህረገፁ TARPLAY.net ላይጋዳፊንእየተዋጉያሉናበአሜሪካየሚደገፉየአልቃይዳሃይሎችእንዳሉያብራራል፡፡በአፍጋኒስታንከኦሳማቢንላደንጋርየሰለጠነውአልሀሲዲናከጎኑያደረገውሱፍያንቢንኩሙ (Sufian bin Kumu) የቢንላደንሹፌርየነበረውአብነትሊሆኑየሚችሉትናቸው፡፡ሌላውበ2007 ከአልቃይዳጋርየተቀላቀለውየሊብያእስላማዊተዋጊቡድንአባልየሆነውአልባራኒነው፡፡እነዚህናቸውየሊብያውያንንየነፃነትጥያቄሊመልሱአመፁንእየመሩያሉት፡፡ በተጨማሪም የሚከተሉትን ማጣቀሻዎች ማንበብ ይቻላል፡- London Daily Telegraph, March 25, 2011: “Libyan rebel commander admits his fighters have al-Qaeda links: Abdel-Hakim al-Hasidi, the Libyan rebel leader, has said jihadists who fought against allied troops in Iraq are on the front lines of the battle against Muammar Gaddafi’s regime,” http://www.telegraph. co.uk/news/worldnews/africaandindianocean/libya/8407047/Libyan-rebel-commander-admits-his-fighters-have-al-Qaeda-links.htmlSee also Wall Street Journal, “Ex-Mujahedeen Help Lead Libyan Rebels,” April 3, 2011
በየመን የበላይነት ያለው ፓርቲ የሙስሊም ወንድማማችነት ቅርንጫፍ የሆነው ኢስላህ ፓርቲውን የሚመራው ሰው ወንድም ሳዲቅ አህማር የጠንካራው ሀሺድ ጎሳ መሪ ነው፡፡ ጀነራል አሊ ሞህሴን ቀንደኛ የኢስላህ ፓርቲ ደጋፊ ነው፡፡ ሌላው የፓርቲው ቀንደኛ ሰው ሼክ አብዱልመጂድ ዚንዳኒ ሲሆን እስላማዊ መንግስት መመስረትን እየወተወተ ይገኛል፡፡ ሼክ ዚንዳኒ ከአል ቃይዳ ጋር ባለው ትስስር ከአሜሪካ ማእቀብ የተደረገበት ሲሆን ከሃማስና ከሳላሳ አመት ግዞት በኋላ ወደ ግብፅ ከተመለሰው ሼክ ዩሱፍ አልቃራዳዊ ጋርም ግንኙነት አለው፡፡(Assyrian International News Agency (June 7, 2011))
ጆርዳንን በተመለከተ የሙስሊም ወንድማማችነቱ መሪ ሀማም ሳዒድ ነው፡፡ በቅርቡ ለህዝብ ባደረገው ንግግር ነፃነት ከፈለጉ እንዲነሱ የአመፅ ጥሪ አድርጓል፡፡
የኦባማ አስተዳደርንም በተመለከተ የቀድሞ የሙስሊም ወንድማማችነት አባል የነበረ ዋሊድ ሾይባት እንዳወጣው ከሆነ የኮንግረስማን አንቶኒ ዌይነር (Anthony Weiner) ሚስት እናት ሳሌሀ አብዲን የሙስሊም ወንድማማችነት ሸሪክ የሆነው ሙስሊም እህትማማችነት አባል ነች፡፡ ዌይነር ከብልግና ፎቶዎች ጋር በተያያዘ ምርመራ እየተደረገበት ያለ ሲሆን ሚስቱ ሁማ አብዲን የሂላሪ ክሊንተን ቢሮ ም/ሀላፊ ነች፡፡ ወንድሟ ሀሰን ከሙስሊም ወንድማማችነት ጋር ቁርኝት ካለው የኦክስፎርድ የእስላማዊ ጥናት ማእከል ነው የሚሰራው፡፡
ሂላሪ ክሊንተን ሳውዲ ዓረብያ ጉዞ ከማድረጓ ከአንድ ወር በፊት ታሪቅ ረመዳን ላይ የነበረውን እገዳ እንዲሰረዝ ትእዛዝ ፈርማለች፡፡ ታሪቅ ረመዳን የሙስሊም ወንድማማችነት መስራቹ ሀሰን አልበና የልጅ ልጅ ሲሆን ከእስላማዊ የሽብር ቡድኖች ጋር ግንኙነት እንዳለው የታወቃል፡፡
በሰኔ 30፣ 2011 ሂላሪ ክሊንተን ቡዳፔስት ሀንጋሪ ውስጥ በሰጠችው መግለጫ መሰረት የኦባማ አስተዳደር ከሙስሊም ወንድማማችነት አባሎች ጋር መወያየት እንደሚሻ ገልፃ ነበር፡፡ የሙስሊም ወንድማማችነት ቃል አቀባይ ሞሀመድ ጎዝላን ለዚህ በሰጠው ምላሽ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ የተጠላች እንደሆነችና ህዝቡ ለትክክለኛ ዲሞክራሲና ነፃነት ያለውን ምርጫ ማክበር እንዳለባትና የህዝቡን የመሪዎች ምርጫንም ማክበር እንዳለባት ለሲ.ኤን.ኤን. ተናግሯል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እስራኤል ዘመም የሆነው ስታንድዊዝአስ ድርጅት (StandWithUs Organization) የአሜሪካ መንግስት ከግብፁ ሙስሊም ወንድማማችነት ጋር እየፈጠረ ያለው ግንኙነት እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል፡፡ የግብፅ ሙስሊም ወንድማማችነት መሪ የአሜሪካ-እስላም ግንኙነት መማክርት (CAIR፡Council on American-Islamic Relations) ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ገልፅዋል፡፡(Global Muslim Brotherhood Daily Report, July 10, 2011) በ2009 ደግሞ የፌደራል ዳኛ ሀማስ እና መማክርቱ ግንኙነት እንዳላቸው በቂ ማስረጃ እንደቀረበ ብይን አስተላልፎ ነበር፡፡ በሚያዝያ 2011 የኦባማ አስተዳደር ፍትህ ዲፓርትመንት የመማክርቱን መስራች ላለመክሰስ ውሳኔ አስተላልፏል ምንም እንኳ ኤፍ.ቢ.አይ. ኤጀንቶችና በዳላስ የዩ.ኤስ. አቃቤ ህግ ቢሮ ክስ እንዲመሰረትበት አስተያየታቸውን ቢሰጡም፡፡ ሙስሊም ወንድማማችነት እስራኤልን ብቻ ሳይሆን አሜሪካንም የማጥፋት አላማ አለው፡፡ በመስከረም 2010 የሙስሊም ወንድማማችነት ዋና አለቃ Supreme Guide ሙሀመድ ባዲ የሙስሊም ጠላቶች በሆኑት እስራኤልና አሜሪካ ላይ የጂሀድ ጥሪውን አሰምቶ ነበር፡፡ በመጨመርም የሙስሊም ሀገራት ሊደርሱበት የሚፈልጉት ለውጥ ላይ መድረስ የሚችሉበት ብቸኛው መንገድ ጂሀድ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
አንዳንድ የዓረብ ሀገሮች ሙስሊም ወንድማማችነትን የሽብር ድርጅት በማለት የመዘገቡት ሲሆን አሜሪካ ግን ይህን አድርጋ አታውቅም፡፡ ምክንያቱም ለዘመናት ሲረዱት የነበረና ያለ፣ የሚስጥር ማህበር ቁንጮዎቹም ለወደፊት አንድ ሉላዊ መንግስት እቅዳቸው የሚፈልጉት በመሆኑ ነው፡፡ የምእራቡን ነፃ አለም ሉላዊ አገዛዝን እንዲቀበል የጋርዮሻዊ ፅንፍን እንደተጠቀሙ ሙስሊም ወንድማማችነትም እስራኤላውያንን (ተራው መስዋእት የሚሆነው ዜጋ ማለት ነው ቁንጮዎቹ ፅዮናውያን ከአንግሎ-አሜሪካ ነጭ ቤተሰቦች ጋር ነው ወዳጅነታቸው) እና ሙስሊሞችን ለማስጨነቅ ይጠቅማል፡፡
ቁንጮዎቹ ሱኒ የሆነውን ሳዳም ሁሴንን በኢራቅ ከተጠቀሙበት በኋላ አገልግሎቱ ሲያበቃ በሺአይቶች ተተክቷል፡፡ ሺአይቶችም ከኢራን ስለሚተሳሰሩ ይህን ለመቆጣጠር በግብፅ፣ ሊብያ ወዘተ. የሱኒ ሙስሊም ወንድማማችነት የበላይ የሆነበት አብዮት እየተካሄደ ነው፡፡ በቁንጮዎቹ እቅድ ማንም የበላይ መሆን የለበትም ሱኒዎችም ሺአይቶችም እኩል ሁነው ከትግል ሲደክማቸው አቋማቸውን በማለስለስ በጋራ የያዝዋቸውን እሴቶች መጋራት ይወስናሉ፡፡ ልክ በፕሮቴስታንት እና ካቶሊክ መሀል እያደረጉ እንዳሉት፡፡ ቁንጮዎቹ ሁሉንም በትግል እያደከሙ የዓለም ሀይማኖቶችን ወደ አንድ ማዋሀድ ይሻሉና፡፡ ይህ ልክ የምእራቡን ካፒታሊዝምና የምስራቁን ጋርዮሻዊነትን ወደ አንድ የአለም ህብረተሰባዊ መንግስት ማዋሀድ እንደሚሹት ማለት ነው፡፡ ጂሀድ በማወጅ በአለም ሙሉ የሸሪአ ህግ ማስፈን የሚመኝ ማህበር በቁንጮዎቹ ዓለም አቀፍ ቀውስ በመፍጠር እቅድ ውስጥ ሰፊ ሚና እንደሚኖረው ግልፅ ነው፡፡
የሃማስ -የሙስሊም ወንድማማችነት- አባሎች የናዚ ሰላምታ ሲሰጡ ከስራቸው ለማነፃፀር ናዚዎች ይታያሉ፡፡
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s